Get Mystery Box with random crypto!

እነሆ ተጉዘን ተጉዘን በጉጉት ከምንጠብቀው የታላቁ እንግዳ የወርሀ ረመዷን በር ላይ ደረስን፡፡ በእ | ABX

እነሆ ተጉዘን ተጉዘን በጉጉት ከምንጠብቀው የታላቁ እንግዳ የወርሀ ረመዷን በር ላይ ደረስን፡፡ በእጅጉ ደስም አለን፡፡ ይህ በርግጥም የአላህ ችሮታ ነው፤ እሱም ከችሮታው ለሚሻው ሰው ይሠጣል፡፡

ጌታዬ ሆይ!
የረመዷን ታላቅነት የምታውቅ ልቦና ስጠን፣ በዕድሉም ከሚጠቀሙት አድርገን፤ ከወንጀሎች ሁሉ ጠብቀን፡፡

ጌታዬ ሆይ! የሻከሩ ልቦችን አለዝብ፣ የተጣሉ ነፍሦችን አዋድድ፣ የተኳረፉትን አስታርቅ፡፡

ጌታዬ ሆይ!
አንተ ከወሰንክልን ዉጭ ምርጫ የለንም፤ አንተ ከፈቀድክልን ኑሮ ዉጭ ሕይወት የለንም፤ አንተ ከለገስከን ዉጭ ሀብት የለንም፣ አንተ የምትወደዉን ስጠን፣ የሠጠኸንንም የምንወድ አድርገን፡፡

አህለን ቢከ ወዳጄ!

እንኳን አደረሳችሁ!

http://t.me/MuhammedSeidABX