Get Mystery Box with random crypto!

M.O.R East Addis Ababa Branch

የቴሌግራም ቻናል አርማ moreastaa — M.O.R East Addis Ababa Branch M
የቴሌግራም ቻናል አርማ moreastaa — M.O.R East Addis Ababa Branch
የሰርጥ አድራሻ: @moreastaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.81K
የሰርጥ መግለጫ

East Addis Ababa Tax Payer Branch Office is one of many branches of Ministry of Revenues at Addis Ababa. Which are responsible for collecting revenue from customs duties and domestic taxes.

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-10 15:48:08
የሴቶችን ጥቃት መከላከል የዘወትር ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ

በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ “ሴቶችን አከብራለሁ! ጥቃታቸውንም እከላከላለሁ!” በሚል መሪ ቃል የጸረ- ጾታዊ ጥቃት ቀን ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ተከብሯል፡፡

ሴቶችና ህፃናት እየደረሰባቸው ካሉት ሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ጥቃቶች እና አካላዊም ሆነ ስነ-ልቦናዊ እንግልቶች የሚጠበቁበት በአመት አንድ ቀን ብቻ በማክበር ሳይሆን በዕለት ተዕለት ተግባራችን ልዩ ትኩረት መስጠት ሲቻል የጸረ- ጾታዊ ጥቃት ሊቀንስ እንደሚችል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተቋማዊ አቅምና ድጋፍ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሁዳ አሊ መድረኩን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር አመላክተዋል፡፡

ፆታን መሰረት አድርገው የሚፈፀሙ ጥቃቶች በተለይም ሴቶች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት ከማደናቀፉ በዘለለ በህይወት የመኖር መብታቸውን ጭምር እስከ መግታት የሚደርስ በመሆኑ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ሁሉም በሴቶች እና ህፃናት የሚደርስ ጥቃት የመከላከል ብሎም የማስቆም ኃላፊነቱ ሊወጣ ይገባል ያሉት ደግሞ የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ገነት ገዳሙ ናቸው፡፡

የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ድጋፍና ክትትል ቡድን መሪ ወ/ሮ ኑሪያ አሊ ዕለቱን አስመልክተው የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

በቀረበው ሰነድ ላይ የመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን የሰነዘሩ ሲሆን፤ በወ/ሮ ገነት ገዳሙ እና በወ/ሮ ኑሪያ አሊ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡
1.7K viewsMOR EAST, 12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 08:31:39
በሀገር ውስጥ ከሚፈፀሙ ክፍያዎች ላይ ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ግዴታ የተጣለባቸው ሰዎች/ድርጅቶች፡-
2.0K viewsMOR EAST, 05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 17:50:17
የመመዘኛ ፈተና
በምዕራፍ አንድ 15ኛው ዙር የሞጁላር ስልጠና ሲከታተሉ ለነበሩ ግብር ከፋዮች የመመዘኛ ፈተና ተሰጥቷል፡፡
2.4K viewsMOR EAST, 14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 08:48:19
ከሽያጭ ታክስ/ Turn over tax/ ክፍያ ነፃ ግብይቶች :-
3.0K viewsMOR EAST, 05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 18:03:29
የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ተጠቃሚዎች ማወቅ የሚገባቸው ነገሮች:-
3.0K viewsMOR EAST, 15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 17:34:16

3.4K viewsMOR EAST, 14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 17:29:02
በእውቀት ላይ የተመሰረተ የታክስ አከፋፈል ማስረፅ እንደሚገባ ተጠቆመ

በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅርብ ጊዜያት ውስጥ አዲስ የግብር መለያ ቁጥር አውጥተው ወደ ታክስ መረቡ በመቀላቀል ላይ ላሉ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የታክስ ህግ እና መመሪያ ዙሪያ ትኩረቱን ያደረግ የግማሽ ቀን ስልጠና ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በቅ/ጽ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሰጥቷል፡፡

የቅድመ ግብር ክፍያ ሥርዓት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 2/2011፣ የታክስ ከፋይ ምዝገባ እና ስረዛ የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2011 እንዲሁም የግብር ከፋዮች መሰረታዊ መብቶች እና ግዴታዎች በተሰኙ ርዕሰ ጉዳዮች የታክስ ትምህርት ባለሙያ አቶ እሸቱ ኢራጎ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው ወደ ስራ ከመግባታችን በፊት መሰጠቱ በይሆናል ሳይሆን በትክክለኛው እና በህጉ መሰረት ሥራችንን እንድንከውን ያስችለናል ያሉት አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎች፤ ስልጠናው በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የታክስ ህጉን ባለማወቅ ምክንያት ሊደርስ የሚችል ቅጣትን ለማዳን ቅ/ጽ/ቤቱ የተለያዩ የአጭር እና የረዣዥም ዕቅዶችን ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት በቅ/ጽ/ቤቱ የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዳዊት ጌታቸው በእውቀት ላይ የተመሰረተ የታክስ አከፋፈል ማስረፅ ለአንድ ሉአላዊት ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ስልጠናውን ብንቃት ተከታትለው የተጠየቁትን የታክስ ጥያቄ ለመለሱ አራት ሰልጣኞች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
3.0K viewsMOR EAST, 14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ