Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀት ላይ የተመሰረተ የታክስ አከፋፈል ማስረፅ እንደሚገባ ተጠቆመ በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ | M.O.R East Addis Ababa Branch

በእውቀት ላይ የተመሰረተ የታክስ አከፋፈል ማስረፅ እንደሚገባ ተጠቆመ

በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅርብ ጊዜያት ውስጥ አዲስ የግብር መለያ ቁጥር አውጥተው ወደ ታክስ መረቡ በመቀላቀል ላይ ላሉ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የታክስ ህግ እና መመሪያ ዙሪያ ትኩረቱን ያደረግ የግማሽ ቀን ስልጠና ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በቅ/ጽ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሰጥቷል፡፡

የቅድመ ግብር ክፍያ ሥርዓት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 2/2011፣ የታክስ ከፋይ ምዝገባ እና ስረዛ የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2011 እንዲሁም የግብር ከፋዮች መሰረታዊ መብቶች እና ግዴታዎች በተሰኙ ርዕሰ ጉዳዮች የታክስ ትምህርት ባለሙያ አቶ እሸቱ ኢራጎ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው ወደ ስራ ከመግባታችን በፊት መሰጠቱ በይሆናል ሳይሆን በትክክለኛው እና በህጉ መሰረት ሥራችንን እንድንከውን ያስችለናል ያሉት አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎች፤ ስልጠናው በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የታክስ ህጉን ባለማወቅ ምክንያት ሊደርስ የሚችል ቅጣትን ለማዳን ቅ/ጽ/ቤቱ የተለያዩ የአጭር እና የረዣዥም ዕቅዶችን ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት በቅ/ጽ/ቤቱ የታክስ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዳዊት ጌታቸው በእውቀት ላይ የተመሰረተ የታክስ አከፋፈል ማስረፅ ለአንድ ሉአላዊት ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ስልጠናውን ብንቃት ተከታትለው የተጠየቁትን የታክስ ጥያቄ ለመለሱ አራት ሰልጣኞች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡