Get Mystery Box with random crypto!

የሴቶችን ጥቃት መከላከል የዘወትር ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ | M.O.R East Addis Ababa Branch

የሴቶችን ጥቃት መከላከል የዘወትር ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ

በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ “ሴቶችን አከብራለሁ! ጥቃታቸውንም እከላከላለሁ!” በሚል መሪ ቃል የጸረ- ጾታዊ ጥቃት ቀን ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ተከብሯል፡፡

ሴቶችና ህፃናት እየደረሰባቸው ካሉት ሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ጥቃቶች እና አካላዊም ሆነ ስነ-ልቦናዊ እንግልቶች የሚጠበቁበት በአመት አንድ ቀን ብቻ በማክበር ሳይሆን በዕለት ተዕለት ተግባራችን ልዩ ትኩረት መስጠት ሲቻል የጸረ- ጾታዊ ጥቃት ሊቀንስ እንደሚችል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተቋማዊ አቅምና ድጋፍ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሁዳ አሊ መድረኩን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር አመላክተዋል፡፡

ፆታን መሰረት አድርገው የሚፈፀሙ ጥቃቶች በተለይም ሴቶች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት ከማደናቀፉ በዘለለ በህይወት የመኖር መብታቸውን ጭምር እስከ መግታት የሚደርስ በመሆኑ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ሁሉም በሴቶች እና ህፃናት የሚደርስ ጥቃት የመከላከል ብሎም የማስቆም ኃላፊነቱ ሊወጣ ይገባል ያሉት ደግሞ የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ገነት ገዳሙ ናቸው፡፡

የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ድጋፍና ክትትል ቡድን መሪ ወ/ሮ ኑሪያ አሊ ዕለቱን አስመልክተው የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

በቀረበው ሰነድ ላይ የመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን የሰነዘሩ ሲሆን፤ በወ/ሮ ገነት ገዳሙ እና በወ/ሮ ኑሪያ አሊ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡