Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስተር

የቴሌግራም ቻናል አርማ moe_ethiopia — ትምህርት ሚኒስተር
የቴሌግራም ቻናል አርማ moe_ethiopia — ትምህርት ሚኒስተር
የሰርጥ አድራሻ: @moe_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.03K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-09-16 12:41:48
ሚኒስቴሩ የ2015 የትምህርት ዘመን የፊታችን ሰኞ እንደሚጀመር ገለጸ

በሀገር አቀፍ ደረጃ የ2015 የትምህርት ዘመን የፊታችን ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀመር ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በ2015 በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆንም ተገልጿል።

ትምህረት ሚኒስቴር ከያዛቸው አዳዲስ አሠራሮችና ትግበራዎች መካከል ሥርዓተ ትምህርቱን ማሻሻል ዋነኛው እንደሆነ መጠቆሙን አሚኮ ዘግቧል።

ካሁን በፊት የነበረው ሥርዓተ ትምህርት አላስፈላጊ ነገሮቸ የታጨቁበት እና የይዘት ክፍተቶች ያሉበት መሆኑም ተነስቷል።

ሥርዓተ ትምህርቱ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችን በማካተት ገለልተኛ በሆኑ አካላት እንደተዘጋጀ ተነግሯል።

የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርትን በተመለከተ ከሆሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሙከራ ትግበራ እንደሚጀመር ተገልጿል

@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
8.4K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 21:26:17 ይህ document file ለ 12ኛ ክፍል ተፈታኞች የወጣ መብትና ግዴታ ነው
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
8.5K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 15:10:04 ብሔራዊ ፈተና!

የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ካላንደራቸው ላይ ማስተካከያ እያደረጉ ይገኛሉ።

ይህ እየተደረገ ያለው ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ወቅት በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መገኘት ስለሌለበት ነው።

በሌላ በኩል ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #ለሪፖርተር_ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፦

- ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምገባና መኝታ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቁሳቁሶችን እያሟሉ ነው።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተመድበዋል። ምደባው ሲዘጋጅ በተቻለ መጠን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲመደቡ ተደርጓል። በአቅራቢያቸው ያለው ዩኒቨርሲቲ በመኝታ ወይም በመፈተኛ ክፍሎች ብዛት ውስንነት ካለበት ወደ ሌላ ዞንና ክልል የመሄድ ዕድል ይኖራል።

- ገጠር አካባቢዎች ላይ ያሉ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመጓዝ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊገጥማቸው ስለሚችል ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመሆን ተማሪዎቹን ወደ ዩኒቨርሲቲ ይጓጓዛሉ።

- ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች በመፈተናቸው ምክንያት ግን ወደ ተማሪዎችም ሆነ ወደ ወላጆች የሚሄድ ወጪ አይኖርም።

- ተማሪዎቹ የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ አካባቢ እንዲላመዱት ለማድረግ ሲባል ፈተናው ከሚጀመርበት ቀናት ቀደም ብለው ወደ ዩኒቨርሲቲው ይጓዛሉ። ወደ ዩኒቨርስቲ ሲገቡ ድምፅም ሆነ ምሥል የሚቀዳና የሚቀርፅ አሊያም ሌላ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ይዘው መግባት አይችሉም።

- በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተፈታኞችም በዩኒቨርስቲው ውስጥ እንዲያድሩ ለማድረግ ታቅዷል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
12.2K viewsedited  12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 22:31:54
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የመጓጓዣና ሌሎች ወጪዎችን በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገለጸ።

ከመስከረም 2015 ዓ.ም. መጨረሻ አንስቶ በሁለት ዙር የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ አንድ ሚሊዮን ገደማ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የሚጓጓዙበትን የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎች በመንግሥት እንደሚሸፈኑ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማስታወቁን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምገባና መኝታ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቁሳቁሶችን እያሟሉ መሆኑን አስታውቆ፣ ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ለማከናወን የሚያስችለውን ወጪ ለመሸፈን ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድለት ንግግር ላይ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል። ፈተናው በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲዎች እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወሳል፡፡

ሼር እና ሰብስክራይብ በማድረግ ለሌሎች ተማሪዎች ያሳውቁ።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
11.1K viewsedited  19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 16:53:14
የ2014 ዓ.ም ክፍል ተፈታኞች በሙሉ የተፈታኞች መብትና ግዴታ!
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
11.3K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 10:09:08
ኢንትራንስ ተፈታኝ ተማሪዎች

ከመስከረም 03/2015 እስከ መስከረም 08/2015 ድረስ የማጠናከሪያ ትምህርት በየትምህርት ቤታቸው ይወስዳሉ

በግልም በመንግስትም ትምህርት ቤቶች ስትማሩ የነበራቹህ የአዲስ አበባ ከተማ ተማሪዎች ከመስከረም 03/2015 ጀምሮ የማጠናከሪያ ትምህርት በየትምህርት ቤቶቻቹህ እንዲሰጣቹህና እንድትዘጋጁም መመሪያ ወርዷል።

ለማጠናከሪያ ትምህርቱ ሲባል የ2015 የትምህርት ዘመን መጀመሪያ ቀን ላይ ማስተካከያ ተደርጓል።

ኢንትራንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ብቻ
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
14.4K viewsedited  07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:00:13
የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ #ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናው እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱን ገልፀዋል።

ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
15.0K viewsedited  06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:15:29
#የ12ኛ_ክፍል_ብሔራዊ_ፈተና

የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ምክክር ሲካሄድ ውሏል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ከየክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች እና የፈተና ጉዳይ አስፈጻሚዎችና ከትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ባለሙያዎች ጋር በፈተናው አሰጣጥ ላይ ምክክር ማካሄዱን አሳውቋል።

በውይይቱ ላይ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሠነዱ ዙርያ የተለያዩ አስተያቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው ግልጽነትና የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሁሉ ከሚመለከታቸው ባለሚና አካላት ጋር በመሆን እየተከናወነ እንደሚገኝ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
14.0K viewsedited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:24:13 የ8ተኛ ክፍል ውጤት እና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ! ውጤትዎን እና የማለፊያ ነጥቡን ለማየት JOIN የሚለውን ይጫኑ።
99 views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 17:12:45 የ8ተኛ ክፍል ውጤት እና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ! ውጤትዎን እና የማለፊያ ነጥቡን ለማየት JOIN የሚለውን ይጫኑ።
180 views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ