Get Mystery Box with random crypto!

የመስቀል ዓይነቶችና ስያሜያቸው የመስቀል ዓይነቶች 1. የመጾር መስቀል በቅዳሴ እና በማዕጠንት | ምን እንጠይቅሎ?

የመስቀል ዓይነቶችና ስያሜያቸው

የመስቀል ዓይነቶች

1. የመጾር መስቀል

በቅዳሴ እና በማዕጠንት ጊዜ ሠራዒው ዲያቆን የሚይዘው ነው።

2. የእጅ መስቀል

ካህናት ምእመናንን የሚባርኩበት በእጅ የምትያዝ የመስቀል ዓይነት ናት።

3. የአንገት መስቀል

ምእመናን ለአምላካቸው ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ ከማዕተባቸው ጋር በአንገታቸው የሚያደርጉት ነው።

4. እርፈ መስቀል

በማንኪያ ቅርጽ ተሠርቶ በእጅታው ላይ የመስቀል ምልክት ያለበት ነው፤ ሠራዒው ዲያቆን በቅዳሴ ጊዜ የአምላካችንን ክቡር ደሙን ለምእመናን የሚያቀብልበት ነው፤እንዲሁም ጌታችን በእለተ አርብ የተወጋበት ጦር ምሳሌ ነው።

መስቀል ከተለያዩ ማዕድናት ይሰራል። ከተሰራበትም አንጻር የተለያዩ ምሳሌ ሰጥተውታል።

1. የእንጨት መስቀል

ጌታችን የተሰቀለው በዕጽ በእንጨት ላይ መሆኑን ለማመልከት ነው።
አዳም ዕጽ/ እንጨትን በልቶ ሞትን በማምጣቱ ክርስቶስም በእንጨት ተሰቀሎ ህይወትን ሊሰጠን በእንጨት መስቀል ተሰቀለ።

2. የብረት መስቀል

ጌታችን በአምስቱ ቅንዋተ ለመቸንከሩ ምሳሌ ነው።

3. የብር መስቀል

ይሁዳም በሠላሳ ብር አሳልፎ ስለመስጠቱ፤ በተጨማሪም ከብር ቢሰራ ተስፋን ዕድልን ያመለክታል።
ይኸውም እርሱ ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ ሊሆን በደሙ ዋጋ ከፍሏልና ከእርሱ ተስፋ እንድናደርግ ያመለክተናል።

4. የወርቅ መስቀል

ከወርቅ ቢሰራ ወርቅ ንጹህ እንደሆነ ንጹሀ ባህርይ እድፈት የሌለው ጽኑ አንተ ነህ ብሎ ለመመስከር ነው።

5. የመዳብ መስቀል

መዳብ ቀለሙ ቀይ ይመስላል ጌታችን ለእኛ ብሎ ያፈሰሰው ደም ምሳሌ ነው።
ብዙዎች የመስቀል ጣላት ሆነው መስቀልን ጣኦት ነው ይላሉ ጣኦት ማለት ግን የሠይጣን ስም የሚጠራበት ፣የሚመለክበት ነው።

ከማዕዶት ዘተዋሕዶ ቻነል የተወሰደ
@mnenteyiklo @mnenteyiklo