Get Mystery Box with random crypto!

selam……… catolic ke ortodox yemileyebetn astemehero beteneger | ምን እንጠይቅሎ?

selam………
catolic ke ortodox yemileyebetn astemehero
betenegerugni?

1ኛ. የኦሬንታል (የተዋሕዶ) ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋሕዶ አንድ ባሕርይ ነው ሲሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባህርያት አሉት ይላሉ።

2ኛ. የኦሬንታል (ተዋሕዶ) አብያተ ክርስቲያናት መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ የሰረጸ ሲሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድም ሰረጸ ትላለች።

3ኛ. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሰዎች ለሰሩት ኃጢአት በመጸጸት ንስሐ ገብተው ሳይፈጽሙት በድንገት ሲሞቱ በመንግስተ ሰማያትና በገሃነመ እሳት መካከል ልዩ የሆነ ቦታ (መካነ ንስሐ-purgatory) ስላለ ነፍሶቻቸው ወደዚያ ሄደው ከኃጢአታቸው እስኪነጹ ድረስ መከራ እየተቀበሉ ቆይተው ኋላ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባሉ በማለት ስታስተምር የኦርየንታል ኦርቶዶክስ (ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ) ይህን ትምሕርት አትቀበለውም።

4ኛ. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሮም ፖፕ የክርስቶስ እንደራሴና የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የበላይ ስለሆነ በመንበሩ ተቀምጦ (ተሠይሞ) በሚወስነው ሁሉ አይሳሳትም ብላ በ 1870 ዓ.ም በቫቲካን አንድ ጉባኤ የወሰነችውን የኦርየንታል ኦርቶዶክስ (ኦርዶክስ ተዋሕዶ) ቤተ ክርስቲያን ግን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በጉባኤ ተሰብስበው በተገኙበት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተወሰነውና ለወደፊትም የሚወሰነው ውሳኔ (ድንጋጌ) ነው የማይሳሳት በማለት የአንድን ሰው የፖፑን አለመሳሳት አይቀበሉም። ፖፑ የሁሉ የበላይ ነው በማለት የአንድ ሰው የፖፑን አለመሳሳት አይቀበሉም።ፖፑ የሁሉ የበላይ ነው በማለት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረውንም ይቃወማሉ።

5ኛ. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሕጻናትን አጥምቃ ሜሮን የየምትቀባቸው ነፍስ ካወቁ በኋላ ነው። የኦርየንታል ኦርትዶክስ ግን ሕጻናትን አጥምቀው ወዲያው ሜሮን ይቀቧቸዋል።

6ኛ. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለቀዳስያን ካህናት ስጋ ወደሙን ስትሰጥ ለምዕመናን ብቻ አቀብላ ደሙን አታቀብልም ነበር። ነገር ግን በቫቲካን ሁለት ጉባኤ ለምዕናንም ሥጋ ወደሙ እንዲሰጣቸው ተፈቅዷል። የኦርየንታል ኦርቶዶክስ ግን ለካህናትና ለምዕመናን ሥጋ ወደሙን ይሰጣሉ። ከዚህም ጋር ኦርቶዶክሳውያን የምንቀበለው የክርስቶስ ሥጋና ደም ነፍስ የተለየው መለኮት የተዋሐደው ነው ስንል ካቶሊካውያን ግን ነፍስ ያለው መለኮት የተዋሐደው ነው ይላሉ።

7ኛ.በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሕጻናት ቅዱስ ቁርባን የሚቀበሉት ነፍስ ዐውቀው ሜሮን ከተቀቡ በኋላ ሲሆን በኦርየንታል ኦርቶዶክስ ግን ሕጻናት ከተጠመቁና ሜሮን ከተቀቡ በኋላ ወዲያው ይቆርባሉ።

8ኛ. እስፓኝ ውስጥ በተደረገችው በኤልቪራ ሲኖዶስ መሠረት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በመላ ሚስት አያገቡም። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (ኦርየንታል ኦርቶዶክስ) ካህናት ግን ከጳጳሳት በስተቀር ቀሳውስትና ዲያቆናት ከፈለጉ አንዳንድ ሚስት አግብተው ሥልጣነ ክህነት ተቀብለው ሊያገለግሉ ይችላሉ።

9ኛ. የካቶሊክ ካሕናት ጽሕማቸውን ሲላጩ የኦርየንታል ኦርቶዶክስ ካህናት ግን ያሳድጉታል።

10ኛ. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አብዛኛውን ጊዜ ከሥዕል በተጨማሪ ለጌታ ለእመቤታችን ለጻድቃንና ለሰማዕታት መታሰቢያ የድንጋይ ሐውልት ሲቀረጽላቸው በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ በሥዕል ይሳላሉ።

(የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሉሌ መልአኩ፤ ገጽ. 56-58)

@mnenteyiklo @mnenteyiklo