Get Mystery Box with random crypto!

እንደምን ሰነበታችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! ኦርቶዶክሳዊ ሆነው ሳይሆን መስለው ለማሳሳት የተነ | ምን እንጠይቅሎ?

እንደምን ሰነበታችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች!

ኦርቶዶክሳዊ ሆነው ሳይሆን መስለው ለማሳሳት የተነሱ ብዙዎች በመካከላችን አሉ። ሰይጣን ራሱ የሐሰት አባት የበጎ ነገር ሁሉ ጠላት ሆኖ ሳለ ሰውን ለማሳሳት ግን "ራሱን የብርሃን መልአክ አስመስሎ እንኳ ይገለጣል" እንዲህ በመገለጡ ግን የብርሃን መልአክ አይሆንም። ቅዱስ ጳውሎስ በዘመኑ የተነሱትን አሳሳቾች እንዲህ ይገልጻቸዋል።

2ኛ ቆሮ 11:13-15

" 13 እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ውሸተኛዎች ሐዋርያትና ተንኰለኛዎች ሠራተኛዎች ናቸውና።

14 ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።

15 እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም ፍጻሜያቸውም እንደ ሥራቸው ይኾናል።"


በቴሌግራም መማማርያ መድረኮች ውስጥም እኛን ሳይሆኑ መስለው ለማሳሳት የገቡ ብዙዎች አሉ። እንደምሳሌም ከቅዱሳን ሕብረት የሌለው ራሱን '"ጉባኤ ቅዱሳን'" ብሎ የሚጠራው የቴሌ ግራም ቻነልም የተሃድሶ መናፍቃን (Heretics) ትምህርቶችን እያሰራጨ ይገኛል። ባለማወቅ የገባችሁ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ልሳን አለመሆኑን ተገንዝባችሁ እንድትወጡ ስል እናሳስባለን! ከዚህና ይህን በመሰሉ አስመሳይ (በሐሰት ካልሆነ ራሳቸውን ችለው መቆም የማይችሉ) ስማቸው ኦርቶዶክሳዊ የሚመስል ሥራቸው ግን ፕሮቴስታንታዊ ከሆኑ ቻነሎች ራሳችሁንና ሌሎች ወንድም እህቶቻችሁም ወደ ነዚህ ቻነሎች ባለማወቅ ተቀላቅለው ከሆነ እንዲለዩ ያድርጉ!

ቤተ ክርስቲያን ስንዱ እመቤት ናትና ማወቅ የምንፈልገውን በመጠየቅ እንመላለስ!

ተጠበቁ ተጠንቀቁ! ዛፍ ከፍሬው እንዲታወቅ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ ትምህርቶችንም ከትምህርታቸው እየለየን ይሁን!