Get Mystery Box with random crypto!

እያንዳንዱ በምድር ላይ ያለ ሰው በተፈጥሮ ያገኘው ስጦታ አለው።ይህም ስጦታ በዓለም ላለው የሰው ል | ምክረ አበው

እያንዳንዱ በምድር ላይ ያለ ሰው በተፈጥሮ ያገኘው ስጦታ አለው።ይህም ስጦታ በዓለም ላለው የሰው ልጅ አንዱ ለአንዱ የሚያገለግልበት ነው።ይህ ስጦታ እያንዳንዳችን እንደየአቅማችን መስራት የምንችለውና የተለያየም ነው።በዚህች ምድር ላይ ያለው የሰው ልጅ ለሚገጥሙት እያንዳንዳቸው ችግሮች መፍትሔው በሌላው ሰው እጅ ላይ ነው ስለዚህ እርሱ ባደለን ተፈጥሯዊ ስጦታ አማካይነት ፍላጎቱንና ፈቃዱን ስለምንፈፅም ሰውን ማገልገል ፈጣሪን ማገልገል ነው።

ባለስልጣን ብንሆን ሐኪም፥መሃንዲስ ብንሆን ነጋዴ፥መምህር ብንሆን አማካሪ፥መንፈሳዊ አገልጋይ ብንሆን ፈላስፋ፥ዳኛ ብንሆን የፀጥታ አስከባሪ፥ገበሬ ብንሆን ተቀጣሪ ሰራተኞች፥ወላጆች ብንሆን የሃገር ሽማግሌዎች...ወዘተ ነገ ስጦታ በሚያድለው አምላክ ፊት ምን ሰራህበት ሌሎችን በማገልገል ምን አተረፍክበት ተብለን እንጠየቅበታለን!!ለሰው ልጅ ህይወት መቃናት በሞያችንና በአቅማችን መስራታችን ለእግዚአብሔር ክብር ነው።

ስጦታ + ሐላፊነት =ተጠያቂነት
ተፈጥሯዊ ስጦታ ሐላፊነት ነው ሐላፊነት ደግሞ የሚያሸልም ወይም የሚያስቀጣ ተጠያቂነት አለው። ሰውን በታማኝነት ማገልገል "አንተ የታመንክ አገልጋይ በትንሽ ታምነሀልና በብዙ እሾምሀለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ" የሚል የዘላለም የህይወት ቃል እንሰማበታለን።በአግባቡ የማያገለግል ግን አንተ ክፉ ሐኬተኛ የማይጠቅም አገልጋይ ተብሎ ወደ ጨለማ ይጣላል ስጦታውም ተቀምቶ ለሌላ በቅንነት ለሚያገለግል ትጨመርለታለች!!
በዚህ ሳምንት ስለ ስጦታና አገልጋይነት ይሄንን ነው የምንማረው።