Get Mystery Box with random crypto!

ክርስቶስን በማመን መዳን የተባለው የዘላለም ህይወት እንዲሁም ጽድቅንና ቅድስናን በነፃ ከተሰጡት፤ | ምክረ አበው

ክርስቶስን በማመን መዳን የተባለው የዘላለም ህይወት እንዲሁም ጽድቅንና ቅድስናን በነፃ ከተሰጡት፤ አማኙ እነዚህን ለመጠበቅ እንደየ አቅሙ በቻለው መጠን #መጋደል ይጠበቅበታል። ስጦታ እንደመሆኑ እኛም ለስጦታው ግብረመልስ መስጠት ያስፈልገናል። ተጋድሎአችንም ከስጋችንና ከሰይጣን ጋር ነው።

ስጋችን ከዚህ የእምነት ስጦታ እንዳይጎድል ክፉ መሻቱን በመግታት በጸሎት በመልካም ስራዎችንና እንደ ቃሉ ለመኖር ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግን እናለማምደዋለን እያለማመድንም ህብረቱ ን እናሳድገዋለን።

ሰይጣንን ደግሞ በስጋ ዝለን ደክመን ይህን ስጦታ እንድንጥል ስለሆነ የሚዋጋን በአግዚአብሔር ቃል እየተቃወምነው እንዋጋዋለን።

ይህን ስጦታ ለመጠበቅ እየወደቅክም እየተነሳህም ከስጋዊ ድካም እስክታርፍ (እስክትሞት) ድረስ ተጋድሎው ይቀጥላል።ተጋድሎው መገዛት ነው መገዛትም ፍቃዱን ማገልገል ነው። መልካምና ክፉ አገልጋይ የሚያስብለንም የጸጋ ስጦታውን ለመጠበቅ ለራሳችን ምን ሰራን የሚል ነው።