Get Mystery Box with random crypto!

#finding_of_the_true_cross ሮማውያን ወንጀለኛን በተለያየ ቅርፅ የተመሳቀለ እንጨት | ምክረ አበው

#finding_of_the_true_cross
ሮማውያን ወንጀለኛን በተለያየ ቅርፅ የተመሳቀለ እንጨት ግንድ ላይ ሰቅለው ይገድሉ ነበር።ቅርፆቹም

አንድ ወጥ ግንድ ፦ ሁለት እጆቹ ተደራርበው ወደ ላይ ወጥረው ሁለት እግሮቹም ደራርበው በሚስማር ይቸነክሩበታል

ተቃራኒ አቅጣጫ የሚመሳቀል ሁለት ግንድ፦ እጆቹና እግሮቹ እያንዳንዳቸውን ለየብቻ በተቃራኒ አቅጣጫ ወጥረው ይቸነክሩበታል

#T ወደ ታችና ወደ ጎን የሚመሳቀል ሁለት ግንድ፦ ይህ የተለመደ መስቀያ ነበር ሁለት እጆቹና እሮቹ በሚስማር ይቸነክሩበታል ወይም ሁለቱ እጆቹ ወደ ተቃራኒ ኣቅጣጫ ኣስረው እግሩን ይቸነክሩበታል

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ለ288 ዓመታት አይሁድ ቀብረውት ስለነበረ እስከ አራተኛው መቶ ክ/ዘ የነበሩት ክርስቲያኖች፥ክርስቶስ በየትኛው የመስቀል(መስቀያ) ግንድ ዓይነት እንደተሰቀለ ትክክለኛና አንድ አይነት መረጃ አልነበራቸውም።የንጉስ ቆስጠንጢኖስ(ኮንስታንቲኖፕል) እናት የሆነችው ቅድስት ሄለና(ኤለና:ኢለኒ) ባየችው ራዕይ መሰረት የክርስቶስን መስቀል የተቀበረበትን ቦታ ፈልጋ አግኝታና አስቆፍራ ካስወጣችው በኋላ ግን እውነተኛው የክርስቶስ መስቀል ታወቀ።

በምዕራብና ምስራቅ በሮም መንግስት ግዛቶች ውስጥ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ነፃነትዋን በንጉስ ቆስጠንጢኖስ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶም
የምዕራብና የምስራቅ አብያተ ክርስቲያን ይህንን ቀን "የእውነተኛው መስቀል መገኘት-finding of the true cross" ብለው ያከብሩታል።በኛ መጋቢት 10 ይከበራል።