Get Mystery Box with random crypto!

#ትንሣኤ_ዘጉባኤ የክርስቶስ መምጣት ቀርቧልና አለም ትገለበጣለች “ከበረሃ የመጣን ባሕታውያን ነን | ምክረ አበው

#ትንሣኤ_ዘጉባኤ
የክርስቶስ መምጣት ቀርቧልና አለም ትገለበጣለች “ከበረሃ የመጣን ባሕታውያን ነን” የሚሉ ብዛታቸው... እውነተኛው በመፃሕፍት ያለው ሳይሆን ተለምዷዊው የሙታን ትንሣኤ ትምህርት “ #ሁሉም ሰው ሞቶ ይነሳል” የሚል ትምህርት በር ከፍቶላቸዋል።ስለዚህ ሲያስተምሩ “አለም ግልብጥብጥ ትልና ሁሉም ሰው ይሞታል ከዛ ክርስቶስ ይመጣል፡ክርስቶስ እንዲመጣ በአለም ያለው ሁሉም ሰው መሞት ግድ ነው ሞት መቅመስ አለበት!!” ይላሉ።
መድረክ ያገኘ እንደራሱ እሳቤ ብዙ ያልተፃፈ መናገር ልማድ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ግን እንዲህ አላስተማረችም!!ታድያ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ምን ይላል የሚለውን ስናይ:-

በርግጥ ጌታችን ኢየሱስ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ድርቅ፣ወረርሺኝና ጦርነት ለመምጣቱ #ምልክት እንደሆኑ ተናግሯል። በነዚህም ክስተቶች ሰው እንደሚሞትም የታወቀ ነው ነገር ግን ሁሉም ሰው ሞቶ ያልቃል አላለም።ይልቁን ክርስቶስ መጥቷል በዚህ አለ ቢሏችሁ እንዳታምኑ የመብረቅ ብልጭታ ለሁሉም እንደሚታይ እኔም ለሁሉ በግልጥ እየታየሁ በብዙ ክብር በደመና ነው የምመጣው ነበር ያለው። (ማቴ 24፥24-31)
ስለዚህ ጌታችን ክርስቶስ ዳግመኛ እኪመጣ ድረስ የሰው ልጅ እየተባዛና እየሞተ ኑሮው ይቀጥላል። ሲመጣም ሞት ያቆማል የሞቱም ሰዎች ይነሳሉ በሕይወት የነበሩትም የማይሞቱ በአንድነትም ዘለአለማውያን ወደመሆን ይለወጣሉ።ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን የጌታችን ኢየሱስ መምጣትና የሙታን ትንሣኤ በሁለት መልእክታት አጠር አድርጎ በደምብ ገልፆታል።

1ኛ ቆሮንቶስ 15
⁵¹-⁵² እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን #አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው #ይነሣሉ እኛም #እንለወጣለን ።
⁵³ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።
⁵⁴ ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ፦ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።

በተጨማሪም የተሰሎንቄ መልእክቱም ይህንን ያጠናክራል
1ኛ ተሰሎንቄ 4
¹⁶ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
¹⁷ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
¹⁸ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።

መደምደሚያ:- የቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ትምህርት በአጭሩ ይህ ነው።ምድርና ሰማይ የሚጠፉት ከተነጠቅን በኋላ ነው።እስከዛው ፍጥረት ሁሉ እንዲህ አሁን እንዳለው ይቀጥላል።
“በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።”