Get Mystery Box with random crypto!

'መዳን በሌላ በማንም የለም' ✞Share ያድርጉና ለሌሎችም ያካፍሉ✞ 'መዳን በሌላ በማንም የለም | ምጥን ቅመም (Mitin Kimem)

"መዳን በሌላ በማንም የለም"
✞Share ያድርጉና ለሌሎችም ያካፍሉ✞
"መዳን በሌላ በማንም የለም" የሚለውን የቅዱስ መፅሀፍን ቃል ለምንፍቅናና
ለጥርጥር ትምህርት በማዋል የእመቤታችንና የቅዱሳንን ማዳን በይፋና በስውር ለሚቃወሙ የተሀድሶ መናፍቃን የተሰጠች አጭር ምላሽ፡፡
እንዲህ በክፋትና በተንኮል አጥማጅና አሰናካይ ርኩሰታዊ ፈተና ሊጥለን ዛሬም
የሚታገለን አስቀድሞ በገነት ዛፎች መካከል በእባብ ገላ ተሰውሮ
ከአምላካችንና ከአባታችን የለየን ድያብሎስ ነው፡፡ እርሱን የምታገኙት በነዚህ በመናፍቃን ልቡና ተሰውሮ ነውና፡፡ ሰይጣን በተንኮሉ ሄዋንን እንዳሳታት በጣም የዋሃን የሆንነውን፡
መንፈሳዊ ጥበብንና መዳን የሚገኝበትን ትምህርት ከአባቶቻችን እግር ስር
ተቀምጠን ያልተማርነውን ብዙዎቻችንን እንዳያቆሽሸን ፡ እምነታችንንና ለክርስቶስ
ማደሪያ የሚሆን ልቡናችንን እንዳያረክስብን በብርቱ መጠንቀቅ ይገባል፡፡
እንግዲህ ወደ ባላጋራችን የማጥመጃ ሀሳብ እንመለስ ፡ ጠላት ወጥመድን
እንደሚያጠምድ ፡ ቢቻለው ብዙዎችን ለመያዝና ከህይወት ለመለየት እንቅልፍ
የሌለው መሆኑን ቅዱሳት መፃህፍት ያስረዳሉ፡፡ እኛ የምናምነውን መጠየቅ
ያለብን እኛው ነን፡፡ እራሳቸው ለራሳቸው ስለኛ እምነት ተናጋሪዎች ፡ ወሳኞች ፡
ተቺዎችና ነቃፊዎች ሆነው በሚነሳው ግርግር እንደለመዱት ነብሳትን ለመዝረፍ
የሚያደርጉት ክፋት ግን የበለጠ የሰይጣን አገልጋይ መሆናቸውን
ይገልጥባቸዋል፡፡

እስቲ ጥቂት ሰይጣን ከላይ ያነሳውን የተንኮል ሀሳብን የሚያሳፍር አጭር ምላሽ እንናገር፡፡ ለዚህ ርካሽ ሀሳብ መቼም ሊቃውንት መጠራት አለባቸው አንልም፡፡ እንደ አንድ ምዕመን ይህቺን እንበል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት እግዚአብሔር በባህርይው አዳኝ ነው፡፡ በባህርይው አዳኝ ነው ስንል፦ ማዳንን ከማንም ያልተዋሰው ያልተቀበለው ፡ በራሱ ለራሱ ያለው ፡ ለወደደው ፡ ለፈቀደው በስጦታ የሚሰጠው ማለታችን ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ማዳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን ሌላ ምንጭ የለውም፡፡
ለማንም ማዳን ግን ምንጩ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ስለዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል ስንልና ቅዱሳን ያድናሉ ስንል ከዚህ ከአለት ከሚፀና እምነትን መሰረት አድርገን ነው፡፡

ይህንን አባቶቻችን በምሳሌ ሲያስረዱ እሳት በባህሪው ያቃጥላል እሳት የሚያቃጥለው ማቃጠልን ከሌላ ነገር ወስዶ አይደለም፡፡ መቼም
የማያቃጥል እሳት የለም፡፡ እሳት ከሆነ እርሱ ያቃጥላል፡፡ ማቃጠል የግል ገንዘቡ ነው በራሱ ያቃጥላልና፡፡ ብረትና እንጨት ደግሞ በተፈጥሮ አያቃጥሉም፡፡ ነገር ግን እንዲያቃጥሉ ማድረግ ይቻላል፡፡ እንዴት? ብረቱን ወስደን : እንጨቱን ወስደን ከእሳት ውስጥ ብንጨምረው ፍም ሆኖ ይግልና ከዛ ያቃጥላል፡፡ መቼም እሳት ውስጥ ገብቶ የማያቃጥል ብረትም ሆነ እንጨት አለ የሚል እምነት ያለው ሰው አለ የሚል እምነት የለኝም፡፡ እሳት ውስጥ
ገብቶ ብረቱ ወይም እንጨቱ ካላቃጠለ አለማቃጠሉ ችግሩ የብረቱ ወይም
የእንጨቱ ችግር አይደለም፡፡ እሳቱ ራሱ አያቃጥልም ማለት ነው፡፡ አሁን
ከመናፍቃን በቀር ስለምን እያወራን እንዳለ ሁሉም የክርስቶስ ቤተሰብ ይረዳል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የድንግል ልጅ ወልድ ዋህድ ክርስቶስ በባህሪው አዳኝ ነው፡፡ ቅዱሳን ደግሞ ወዷቸው ፡ መርጧቸው ፡ ለይቷቸው ፡ ሾሟቸው በፀጋ ያድናሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አንድነቱ የተጠበቀ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ፃድቅና ሰማዕት የማያድንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ካላዳነ ግን አለማዳኑ የፃድቁ ወይም የቅዱሱ ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱ ማዳን ትቷል ማለት ነው፡፡ ወይም ያ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትና ህብረት የለውም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ቅዱሳን ፃድቃን ሰማዕታ ሁሉ ያድናሉ፡፡ ይሁዳ ግን አያድንም፡፡ ሐዋርያ ነበር ከግንዱ ከክርስቶስ ተቆርጦ ወደቀ፡፡ ሰይጣንም አያድንም ለራሱም አይድንም፡፡ መልአክ ነበር ከምንጩ ከክርስቶስ ተቆርጦ ወደቀ፡፡ ነገር ግን አለምን የካዱ ፡ የአለምን ነገር ስለ ክርስቶስ የሰቀሉ ፡ በተጋድሎ የፅድቅ ፍሬን ያፈሩ ቅዱሳን ፡ ፃድቃን ፡ ሰማዕታት ግን ያድናሉ፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ይናገር ካልን ደግሞ በድን የሆነ የፊደል ችርቻሮን ከሚነግዱትና ቅዱሱን ቃል በከንቱ ተሸክመውት ከሚዞሩ መናፍቃን በቀር ሁሉም ክርስቲያን እንደሚያስተውለው በሐዋርያት ገድል ላይ ተመስርቶ የተፃፈው የሐዋርያት ሥራ እንደሚያስተምረን በቅዱሳን እጅ ድንቅ
ተዓምር እንደሚደረግ እናስተውላለን፡፡ አባታችን ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው ሙት
እንዳስነሳ ፡ ለምፅ እንዳነፃ ፡ ድውይ እንደፈወሰ ፡ ሽባ እንደተረተረ ፡ አጋንንትን
እንዳሳደደ ፡ አባታችን ቅዱስ ጳውሎስም በጥላው ብዙዎችን እንደፈወሰ
ተመዝግቧል።
/ሐዋ 5፥15, ሐዋ 19፥11/
የአባቶቻችን ቅድስናና ስልጣን ከነሱ
አልፎ ለልብሳቸው ዘርፍና ለጥላቸው ፡ ለረገጡት አፈር ሁሉ መትረፉን ቅዱስ
መፅሀፍ ያስተምረናል፡፡ እኛም የክርስቶስ ልጆች የድንግል ማርያም ወዳጆች
በእውነት እናምናለን፡፡ ብዙ ድንቅ ነገርም ተደርጎልናል፡፡ በመጨረሻው ቀንም
የክርስቶስ ቅዱሳንን የሚያሳድዱና በቅዱሳን ደም በሰከሩ በመናፍቃን ላይ ቃሉ ይፈርዳል፡፡ በንስሀ እስካልተመለሱ፡፡

አባቶቻችን ቅዱሳን በብርሃን ከተማ
ከክርስቶስ ጋር ለመኖር ከሄዱ በኃላም የረገጡት አፈር ፡ የፀለዩበት በዓታቸው ፡
የሰገዱበት ስፍራ ፡ ያረፋበት መቃብራቸው እኛ የሥላሴ ልጆችን ያድናል፡፡ ለኛ የተደረገልንን ትተነው የሉተር ልጆች በከንቱ ተሸክመውት ከሚሄዱት በአዳራሽም ሽለላና ቀረርቶ ከሚያሰሙበት ከመፅሃፍ ቅዱስ ከመፅሃፈ ነገስት ላይ አባታችን
ኤልሳ ከተቀበረበት መቃብር አፈር ላይ የወደቀ አንድ የሞተ ሰው አፈፍ ብሎ
መነሳቱን እንዲያነቡት እንጋብዛቸዋለን።
/2ነገ 13፥31/፡፡
ለማስተዋልና ለማመን የሚያስችላቸውን የእምነት ብኩርናን በምስር ወጥ አስወስደው ዛሬ የቀደመች
እምነታቸውን ለመሳደብ ፡ ለመራገም ፡ በእርሷ ላይ ለመሳለቅ ተፈረደባቸው
እንጂ፡፡ እግዚአብሔር ይምራቸው ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን ሁሌ ወደ
እግዚአብሔር ትማልዳለች፡፡ ሌላም ካሻቸው ፀበል እንደሚያድን ሶርያዊው
ንዕማን በፍርድ ቀን ይመሰክራል፡፡ መስቀሉ እንደሚያድንና የእሳት ባህርን
እንደሚያሻግር ፡ አጋንንትንም ከጥልቁ እንደሚያወርድ ቅዱሳኑ ሁሉ በአለም ላይ
ይመሰክሩበታል፡፡
ታዲያ አብረውት ለሶስት አመት ከሶስት ወር የተመላለሱት ቅዱሳን ሃዋርያት
ጥላቸውና የልብሳቸው ዘርፍ ካዳነ በማህፀኗ ያደረባት ፡ ከስጋዋ ስጋን ከነብሷ ነብስን የነሳባት ፡ በክንዶቿ እቅፍ ያረፈባት ፡ ጡቶቿን ጠብቶ ያደገባት ፡ በጀርባዋ ታዝሎ በበረሃ የተሰደደባት ፡ እናቱ ፡ እናቱ ፡ እናቱ ድንግል ማርያምማ እንደምን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነብስ አታድን??!! ከእግዚአብሔር ከተሰጡት ፀጋዎች ከእመቤታችን የሚጎድልባት የትኛው ነው፡፡ የራማው ልዑል ቅዱስ ገብርኤል ይመስክራ ፡ ሀሰት በአንደበቱ ያልተገኘበት በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው መልአኩ ገብርኤል ይመስክራ። ይቀጥላል።