Get Mystery Box with random crypto!

መሄዷ ላልቀረ ከቤቴ በራፍላይ ስታንጃብብ ውላ ከጣራውም በላይ ትንሽ ከፍ በላ እንደዛው ስታድር ሳ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

መሄዷ ላልቀረ

ከቤቴ በራፍላይ ስታንጃብብ ውላ
ከጣራውም በላይ ትንሽ ከፍ በላ
እንደዛው ስታድር ሳትጠጣ ሳትበላ
ተመልክቻታለው አዎ አይቻታለው
እሷ ኩርምት ብላ


ከቤቴ ስወጣ እሷ ትሸሻለች
ያላየዋት መስሏት እሩቅ ትበራለች
ማባራት ይመስል ሳትዞር ትሄዳለች
እኔ እንደራኩኝ እሷ ትመጣለች

ሄጄ እንደተመለስኩ ወደላይ አያለው
አይኔን እያንከራተትኩ እፈልጋታለው
ፈልጌፈልጌ ሁልጊዜ አጣታለው
ያኔ እንደገባኝ እንደተደበቀች ትቻት እገባለው
ልክእንደገባው በመስኮት አያለው
ቤቱን ስታንጃብብ ሽቅብ አያታለው

ልክ በዚሁኔታ ጊዜውም ይነጉዳል
ከጊዜያቶች ውስጥ ክፉ ቀንም መቷል
ከመስኮቴ በኩል እንደተለመደው ስትዞር ይታያል
አንድ የሆነ ፍጥረት ከሷጋር ይዞራል
ፈጥኜ ስወጣ ይዟት ተሸብልሏል
ላትመጣ እንደሄደች እንባዋ ያሳብቃል
እሷ ጥላኝ ሄዳ ትዝታዋ ቀርቷል
ለትዝታ ብቻ መሄዷ ላልቀረ ባትመጣ ይሻላል
ልቤ እንዲያ እያለ ያለፈውን ጊዜ ሁሉንም ይረግማል