Get Mystery Box with random crypto!

ህልምህ ይፈትንሃል! ከማንም ተለይቶ ወዳንተ የመጣ ህልም በቀላሉ ህልምና ተልቁ የህይወትህ ስ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ህልምህ ይፈትንሃል!

ከማንም ተለይቶ ወዳንተ የመጣ ህልም በቀላሉ ህልምና ተልቁ የህይወትህ ስንቅ አይሆንም ። ይፈትንሃል ፤ ዋጋ ያስከፍልሃል ። አቅምና ብርታትህን በእራሱ መንገድ ይለካል ። ለህልምህ እንደሞትገባውና የእርሱ እንደሆንክ ማረጋገጡ ያንተ ድርሻ ነው ። ውሎህ ሌላ ስራህ ሌላ ቢሆን ለህልምና ራዕይ የመታመን ሁኔታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይገባል ። የትኛውም ህልመኛና ባለራዕይ ይፈተናል ፤ መከራ ውስጥ ይወድቃል ፤ ይታመማል ፤ ይሰቃያል ። በቀላሉ ትልቅነት አይገኝም ፤ እንዲሁ በዋዛ ፈዛዛ ተፅዕኖ ፈጣሪነት አይመጣም ። እጩነቱን መሻገር ፣ ህልምን በእጅ ማስገባትና በእርግም እውነተኛ ህልመኛና ባለራዕይ መሆን ይጠበቅብሃል ። ዋጋ የሌለው ፣ መሱዓትነት የማያስከፍል ነገር ቀላልና የወረደ ነገር ብቻ ነው ። ትልቅ ነገር ስታስብ ክፍያህም ያድጋል ፤ የሚጠበቅብህ ግዴታም እንዲሁ ይጨምራል ።

አዎ! ጀግናዬ..! ህልምህ ይፈትንሃል! ዋጋህን በምትከፍለው መሱዓትነት ይወስናል ፤ አቅምህን በምትወጣው ሃላፊነት ልክ ይመዝናል ። አንዳንዴ የምትችለውን ብቻ ማድረግ ህልምህ የሚጠብቅብህ ላይሆን ይችላል ። ከምታስበው በላይ ከወዳጆችህ ይለይሃል ፤ በሰው ያስተችሃል ፤ ከመንጋው ይነጥልሃል ፤ ውሎህን ያስለውጥሃል ፤ መጥፎ ልማዶችህን ያስተውሃል ፤ ወሬህን ያስቀይርሃል ፤ ዙሪያህን ያጠራዋል ። የህልምህን ትልቅ መሆን በሃሳብህ ትልቅነት ታረጋግጣለህ ። የራዕይህን ሁለተናዊነት በምትፈጥረው የተለያየ ግንኙነት ትለየዋለህ ። ሹመት ያለፈተና አይሰጥምና ያንተ በህልምና ራዕይህ ላይ መሾም በፈተና ይሆናል ፤ ተገቢነትህን በማረጋገጥ ይሆናል ። የፈለከውን እያደረክ ፣ የፈለክበት እየተገኘህና ያሰኘህን እየፈፀምክ ስለ ህልምና ራዕይህ እውንነት አትናገርም ። ህልመኛ የሚያደርግህ የእራስህ መንገድ አለህ ፤ ህልምህን እውን የሚያደርግና የሚያሳካም ትክክለኛ ጎዳና አለ ።

አዎ! ያንተ የሆነው ህልም ላንተ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ይፈልጋል ፤ በእርግጥም አንተ እንደምትገባውና እንደምትመጥነው መታወቅ ይኖርበታል ። ትልቅ ህልም አለኝ ስላልክ ብቻ ህልመኛ አትሆንም ፤ ደጋግመህ ስለ ህልምህ አመጣጥና እውንነት ስላወራህ ብቻ ህልምህን የትም አታደርሰውም ። ህልሜ የምትለው ነገር የሚፈልገውን አይነት ሰው ሆነህ የመገኘት ግዴታ አለብህ ፤ የእርሱን አቅጣጫ መምረጥም ይኖርብሃል ፤ መስፈርቱን ማሟላት ይጠበቅብሃል ። ህልምህ ችግር ፈቺና ለሰው የማይደርስ ከሆነ ገና ወደ ህልምነት አላደገም ማለት ነው ። ራዕይህ ሁሉን አካታችና አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያራምድ ካልሆነ ራዕይነት ላይ አልደረሰም ማለት ነው ። በገዛ ህልምህ ተፈትነህ ፣ ባንተው ራዕይ ተመዝነህ አልፈህ ከሆነ ወደኋላ የምትመለስበት ምክንያት የለህምና ፈተናህን ተሻገር ፣ ምዘናውንም አልፈህ ተገኝ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q