Get Mystery Box with random crypto!

ለቀንም ቀን አለ! ብርሃን ሲኖር ጨለማ አይኖርም ፤ የብረሃን መጥፋትም ጨለማን ይፈጥራል ። | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ለቀንም ቀን አለ!

ብርሃን ሲኖር ጨለማ አይኖርም ፤ የብረሃን መጥፋትም ጨለማን ይፈጥራል ። ጥፋት ጥፋትን እስኪወልድ መጠበቅ ከአጥፊነት አይተናነስም ። እሳት በጊዜ ካልጠፋ የሚያጠፋው ጥፋት ይበዛል ፤ አደጋው በሒደት እያየለ ይመጣል ። ዝምታም እንደ እሳት ነው ፤ የሚታይ ግልፅ ተቃውሞና ትቺት ባይኖር እንኳን ዝምታን የመረጠ መቀጣጫ በምንም አይመለስም ። አምላክ ስራውን በሚሰራበት ሰዓት እራስን እንደ አምላክና ፍፁም አድርጎ መመልከት ማንነትን መዘንጋት ፣ ሰውነትንም መርሳት ነው ። ሌትና ቀንን የፈጠረ አምላክ የረዘመውን ለሊት ፣ አላልቅ ያለውን ጨለማ ማሳጠር አያቅተውም ። ሁሉም ማለፉ ላይቀር ሰንፈን ከብርቱ ፣ ጥሬውን ከብስሉ ፣ ገፊውንም ከደጋፊው ለይቶ ያሳያል ። እምነት ያለው ትውልድ ፣ የምርም አምናለው ፣ አምላኬን አውቃለሁ ፣ በእርሱ እታመናለሁ ፣ በእርሱ እመካለሁ የሚል አማኝ ከማንም እምነቱን ይወዳል ፤ ከምንም እምነቱን ያስቀድማል ።

አዎ! ጀግናዬ..! ለቀንም ቀን አለ! ለጨለማም ነጉሱ ብረሃን ይመጣል ፤ ለምድር ሹማመንትም የሰማዩ ገዢ የምድሩ አለቃ ይወርዳል ። ሰላም አለ ፣ ፍቅር አለ ፣ መተሳሰብ ፣ መዋደድ ፣ መከባበር አለ አንድና አንድ አምላክን ማክበር ሲቻል ብቻ ። የሰው ልጅ ታመህ ብታለቅስ ለመረበሽ ያለቀስክ ይመስለዋል ፤ ስቃይህ ቢያስነባህ ለፌዝ ምታነባ ይመስለዋል ። የሰማይ አምላክ ግን እንባ ያቀረረ አይንን ይረዳል ፤ የባባ ሆድን ያውቃል ፤ የሚያዝን አንጀትን ይመለከታል ። ምድር ትሳቅብህ ፤ ፍርዷን ትንሳህ ፣ መከራውን ታብዛብህ ፣ አንገትትሀን ታስደፋህ ፣ ታሳፍርህ የምታምነው አምላክ ግን እውነተኛ ፍርድን ይሰጥሃል ፤ እንባህን ያብሰዋል ፤ ከሳሾችህን ይከሳል ፤ ፈራጆችህንም ይፈርድባቸዋል ።

አዎ! አምላክን ከያዝክ ፅና ፣ ተስፋ አድርግ ፣ ታገስ ፣ ጠብቅ ። መጥፎ ጊዜ እህሉ ከእንክርዳድ የሚለይበት ወቅት ነው ። እንክርዳዱ በምክንያት ይጣላል ፤ ሰብሉም በጊዜው ይለመልማል ፣ ፍሬንም ያፈራል ። ፀሎትህ ወደ አምላክህ ይሁን ፤ ጩሀትህ ወደ ሰሚው ፈጣሪ ይሁን ። አምላክ አብሮህ ካለ ፣ እርሱ ከቀደመልህ የማትወጣው መከራ ፣ የማታልፈው ስቃይ የለም ። እውነት ጊዜ አላት እስከዛም ውሸት ምድርን ትዞራለች ፤ በመድሎና በፍረደ ገምድል ትከበባለች ። እውነት በነገሰች ወቅት ግን መኖሯም ይዘነጋል ። አመፅ ይነሳል አምላክህን ይዘህ ታገል ፤ ፍርድ ይዛባል ፈጣሪ እንዲፈርድ ተማፀን ፤ በደል ይደርስብሃል አምላክ እንዲያበረታህ ጠይቅ ። ሰው ይስታል ፣ ሰው ይሳሳታል መታረም ቢፈልግም ይታረማል ፤ አውቆና ፈቅዶ ካደረገው ግን ስህተት ሳይሆን አቋሙ ነውና ለእራስህ አቋም ታማኝ ሁን ። የተስፋዋ ቀን ትመጣ ዘንድ ፅና ፤ ሰላምን ታገኝ ዘንድም አምላክህን ያዝ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q