Get Mystery Box with random crypto!

ባልሰራሀው አትናደደ! ውጤት እንዳልመጣለህ ታስባለህ ፣ በጠበከው ልክ የፈለከው ቦታ እንዳልደ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ባልሰራሀው አትናደደ!

ውጤት እንዳልመጣለህ ታስባለህ ፣ በጠበከው ልክ የፈለከው ቦታ እንዳልደረስክ ይሰማሰሃል ፣ እርካታ ርቆሃል ፤ መረጋጋት ተስኖሃል ፤ የምትችለው ያክል እንዳላደረክ ይሰማሃል በዚህ ምክንያት በእራስህ ትናደዳለህ ? በእራስህ ታዝናለህ ? እራስህን ትወቅሳለህ ? አስታውስ ፤ ሳትሰራ ይመጣል ብለህ በምትጠብቀው ውጤት ፣ ምክንያት አልባና ያለ በቂ ጥረት የሚመጣ አይደለም ። ውጤትን ብቻ እየጠበክ ብታደርግ ያለህን ታጣለህ እንጂ የምታተርፈው ነገር የለም ። ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንተባለው ምንም ሳትለፋ ፣ ሳትተጋ ፣ ሳትደክም እንደማንኛውም ሰው በማቀድና በማሰብ ብቻ ጊዜህን እያራዘምክ ፣ እቅድህን እያደስክ ፣ ሰበብህን እያሳመርክ ብትቀጥል ጊዜውም ይሔዳል ፤ ያንተም ሃሳብና እቅድ እንዲሁ እየተነነ ይመጣል ።

አዎ! ጀግናዬ..! ባልሰራሀው አትናደድ! ምንም ሳትሞክር በማይታይ ውጤት እራስህን አታጨናንቅ ፤ ዋጋ ሳትከፍል በማታየው ለውጥ አትረበሽ ፤ ሳትሞክር በማይመጣ ለውጥ አትደናገጥ ። ምንም ሳታደርግ ምንም እንደማይፈጠር እወቅ ። ምክንያት መደርደር ላይ ብትጀግን፣ እቅድ ማውጣት ላይ በርትተህ ትግበራውን ወደጎን ብትለው ፣ ከትጋትህ በላይ ሃሳብ ላይ ብታተኩር ፣ ከስራው በተሻለ ውጤቱን በጉጉት ብትጠብቅ አንዳች ነገር አይመጣም ። የጠበከው ይርቅሃል ፤ የተመኘሀው ይሸሽሃል ፤ ያሰብከው ይበተናል ፤ ያቀድከው መና ይቀራል ። ለትግበራው ዛሬ ነገ ብትል ውጤቱ እንዲሁ ዛሬ ነገ ማለቱ አይቀርም ። መሬት ላይ ያልወረደ ሃሳብ ሃሳብ ብቻ ነው ፤ ያልተኖረ እውቀት ባዶ እውቀት ነው ፤ የማይተገበር እቅድ የውድቀት ማበረታቻ ነው ።

አዎ! ውጤቱን ባለማየትህ ፣ የጠበከው ባለመሆኑ ፣ የተመኘሀው ባለመፈፀሙ ቅንጣት ብስጭት ውስጥ አትግባ ። ዋጋውን ካልከፈልክ ዛሬም ነገም እንዲሁ ውጤት እየናፈክ ፣ የተሻለ ህይወት እንደተመኘህ ትቀጥላለህ እንጂ ምንም የሚመጣልህ አዲስ ግኚት አይኖርም ። ችግርህ የጥረትህ ማነስ ፣ የተግባርህ መድከም ፣ የልፋትህ ዋጋ ማጣት ከሆነ ጥረቱን መጨመር ፣ ክፍያውን ማሳደግ በተቃራኒውም የምትጠብቀውን ውጤት ማሳነስ ይኖርብሃል ። በባዶ ሃሳብ ታላቅነትን ማሰብ ሌሊት የሚታየውን ህልም ጠዋት በድጋሜ ለማየት እንደመንደርደር ነው ።

አዎ! ተናደድክ አልተናደድክ ፣ ተበሳጨህ አልተበሳጨህ ፣ አዘንክ አላዘንክ ስራህ ለውጤት የሚያበቃህ ፣ ልፋትህ የምትመኘው ቦታ እንደሚያደርስህ በሚገባ ታውቀዋለህ ። በምታውቀው ጉዳይ ንዴታና ብስጭትም አያስፈልግም ። ካልሰራህ ውጤት የለም ፤ ሌት ተቀን ካልተጋህ ጠብ የሚል ነገር አይኖርም ። ህይወት ውጣውረድ አላት ወቶ መውረድም ያንተ ድርሻ ነው ። የሚጠበቅብህን ሃላፊነት በበቂ ሁኔታ ሳትወጣ ፣ አቋራጭ መንገድን እንደ ዋንኛ አማራጭ እየተመለከት ፣ ከስራና ጥረት ባላይ ውጫዊው ተግባሮች ላይ ተማምነህ ፣ እንኳን የጠበከው ትልቅ ውጤት ይቅርና ከጠበከው በታች ተስፋ ሰጪ የሚያበረታታ ነገርም ላይመጣ እንደሚችል አስብ ። ውጤቱን ከፈለክ ትጋቱን እኩል በእኩል ፈልገው ፤ ስራው ላይም በርትተህ ተገኝ ። ያልሰራ ውጤት የለም ፤ ያለልፋት ከፍታ አይመጣም ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q