Get Mystery Box with random crypto!

#_ስትሞቺ_እሞታለሁ ደስታሽ ከፊትሽ ላይ ተነጥሎ ካየሁ ባንቺ ማዘን ብቻ እኔም ብዙ አዝናለሁ አንዲ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

#_ስትሞቺ_እሞታለሁ
ደስታሽ ከፊትሽ ላይ ተነጥሎ ካየሁ
ባንቺ ማዘን ብቻ እኔም ብዙ አዝናለሁ
አንዲት ዘለላ እንባ ከአይኖችሽ ካገኘሁ
የጎርፍ ያህል እንባ እኔም አነባለሁ

ታመሽም ከሆነ ተኝተሽ ከአልጋ ላይ
እኔንም ይመመኝ ስቃይሽን እንዳይ
አንቺን ደስ ካለሽ ሀሴት ከተሰማሽ
አንዲት ክፉ ነገር ፈፅሞ ካልነካሽ

እኔም ደስ ይለኛል ባንቺ ደስታ ብቻ
የህይወት ቁልፌ ነሽ የልቤ መክፈቻ
ይህንን ልንገርሽ እንዳትረሺ ፍቅሬ
አንቺ ስትኖሪ ነው በደስታ መኖሬ

የማያት ሻማዬ ጨርሳ እንዳትጠፋ
ብርሀን የያዘች የመኖሬ ተስፋ
አንቺ ነሽ ምክንያቷ የነብሴ መለምለም
እሩቅ አሻግሬ ህይወትን እንዳልም

ህመምሽ ህመሜ እንባሽ ነው እንባዬ
ቃልኪዳን አለብኝ ልኖር አንቺን ብዬ
ፈጣሪ ከጠራሽ በአይኔ ሞተሽ ካየሁ
እወቂልኝ ፍቅሬ ስትሞቺ እሞታለሁ
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q