Get Mystery Box with random crypto!

ስም ይጥልሃል! ስምህን ለማሳመር ፣ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ፣ ከላይ ከላይ ጎልቶ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ስም ይጥልሃል!

ስምህን ለማሳመር ፣ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ፣ ከላይ ከላይ ጎልቶ ለመታየት ፣ ለመወደድ ፣ ለመደነቅና ለመሞገስ የምታደርገው የትኛውም ጥረት ጥፋትን ሊያስከትልብህ እንደሚችል እወቅ ። ሰዎች ተቀብለውህ አንተ እራስህን ባትቀበል ምን ይጠቅምሃል ? ሰዎች በሚያዩት ነገር ቢያጨበጭቡልህና አንተ በምታውቀው ነገር ብታዝን ምን ታተርፋለህ ? አንድ ቀን የሚፈርስ ጥሩ ስም ከመገንባት ይልቅ ሁሌም አብሮ የሚቆይ ፅኑ ማንነትን መገንባት ይሻልሃል ። አንተነትህን ስትገነባ ፣ ብቁ ለመሆን ስትተጋ ፣ እራስህ ላይ ስትሰራ ተቀባይነት ማግኘት ፣ መወደድ ፣ መደነቅ ፣ መሞገስ ዋናው መስፈርትህ አይደለም ። ትልቁና ዋነኛው ምክንያትህ ለውጥና እድገትህ ነው ፤ ስኬትና ተፅዕኖ ፈጣሪነትህ ነው ። ማንም ነገ የሚለቅ የተቀባባ ፣ የተሽሞነሞነና ለጊዜው የሰዎችን ትኩረት ብቻ ሊስብ የተዘጋጀን ነገር የመጀመሪያ ምርጫው ሊያደርግ አይችልም ። ወርቅ ቅብ ነሐስ እውነተኛው ነሃስነቱ ሲታወቅ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አይከብድም ።

አዎ! ጀግናዬ..! ስም ይጥልሃል! ስምህን ለመገንባትና ክብርን ለማግኘት ያልሆንከውን ነኝ ፣ ያሌለህን አለኝ ፣ ያልሰራሀውን ሰርቼያለው ፣ ያንተ ያልሆነውን የእኔ ነው ብትል ለጊዜው የምትገነባው ጥሩ ስም ሊኖርህ ይችላል በሒደት ግን የሚፈርስ ማንነት ይኖርሃል ። ማንም ሰው ውሸትን አይወድም ፤ መታለልን አይፈልግም ፤ በሌለ ማንነት መተዋወቅም አይመቸውም ። በምላስ የተሽሞነሞነና በማንነት የሚታወቅ ሁለት ገፅታ የውድቀት ሁሉ መሰረት ነው ። እራስህን የጠቀምክ እየመሰለህ ሰዎችን ለማስደመም ብቻ ወጪህን ብታበዛ ፣ ለታይታ ደስተኛ ብትመስል ፣ ለይስሙላ እንደ ሃብታም ብትንቀሳቀስ ውጫዊ ገፅታህን እያስዋብክ እራስህን ትጥላለህ ። ያንተ ለብሶ መታየት ፣ ደምቆ መገኘት ፣ እንዳለው ለማሳየት ደረቱን ነፍቶ መሔድ የሚያሳስበው ሰው ያለ ይመስልሃል ? በፍፁም ።

አዎ! ማንነትህን በስምህ ለመገንባት አትሞክር ፤ እራስህን በምታገኘው ተቀባይነት አተለካ ፤ ሰውነትህን በውጫዊ ሙገሳና አድናቆት አትመዝነው ። ሊቀይርህና ሊታወቅ የሚገባው ከላይ በወሬና በጌጣጌጥ የደመቀው ገፅህ ሳይሆን በውስጥ የተደበቀው እውነተኛ አንተነትህ ነው ። የምታገኛቸው ሰዎች ነገ አብረውህ አይኖሩም ፤ የሚያውቁህ ሰዎች ዘወትር አብረውህ አይኖሩም ። ሰዎችን ለማታለል ትጥራለህ እንጂ የምታታልለው የገዛ እራስህን ነው ፤ ሰጣ ገባ ውስጥ የምትገባው ፣ ሃሳብህን የምታጋጨው አንተው ነህ ። ገፅህን አይተው ፣ ዝናህን ሰምተው ፣ ለእራስህ በሰጠሀው ሃሰተኛ ስም ተታለው የሚመጡ ሰዎችም ሆኑ ሌሎች ጥቅማጥቅሞች በእርግጥም ሊቀይሩህና ሊያሳድጉህ ሳይሆን ሊጥሉህና ማንነትህን ሊያጎድፉ ነው ። ከስምህ ማንነትህን አስቀድም ፤ ከገፅህ ስብዕናህን አሳውቅ ፤ ከውጫዊው ከበሬታ ውስጣዊውን የእራስህን ክብር ጠብቅ ፣ አስጠብቅ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q