Get Mystery Box with random crypto!

የቱ ይበልጥ ያስተምራል? ደጉ ጊዜ ወይስ መጥፎው ? ትርፉ ወይስ ኪሳራው ? ስኬቱ ወይስ ውድ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

የቱ ይበልጥ ያስተምራል?

ደጉ ጊዜ ወይስ መጥፎው ? ትርፉ ወይስ ኪሳራው ? ስኬቱ ወይስ ውድቀቱ ? ማግኘቱ ወይስ ማጣቱ ? መወደዱ ወይስ መገፋቱ ? መሞገሱ ወይስ መነቀፉ? የቱ ይበልጥ ያስተምራል ? በእርግጥም መጥፎ የተባሉት የህይወት አጋጣሚዎች ከጥሩዎቹ የተሻለ ያስተምራሉ ፤ ምክንያቱም መከራን ስለሚያስከትሉ ፣ ለስቃይ ስለሚያበቁ ፣ ፈተና ውስጥ ስለሚጥሉ ። መጥፎ ቀናት ማንነትን ይሰራሉ ፤ ያጠነክራሉ ፤ ያበረታሉ ፤ ለተሻለ ደረጃ ያበቃሉ ። በእያንዳንዱ ከባድ አጋጣሚ አንድ የምትረዳው ነገር ይኖራል ። ውድቀት ውስጥ ትልቁ ትምህርት ይኖራል ፤ በመገፋት አንተነትህ ይገባሃል ፤ ስትገለል ለብቻህ መፍጨርጨር ትጀምራለህ ። ማንነትህን የሚፈትን የትኛውም አጋጣሚ የማታውቀውን ሊያሳውቅህ ፣ ያላየሀውን ሊያሳይህ የሚመጣ ነው ።

አዎ! ጀግናዬ..! ቻይ ልብ ስላለህ በመከራ ትማራለህ ፤ በመጥፎ ቀን አዲስ ተሞክሮን ትወስዳለህ ፤ የተለየ እውቀትን ትቀስማለህ ። በህይወት እስካለህ ድረስ ጫናዎች ይኖሩብሃል ፤ ተሯሩጠህ ሰረትህ ፣ ለፍተህ የመግባት ግዴታ ይኖርብሃል ። የህይወት ሩጫው በእራሱ ለከባድ ውጣውረድ ይዳርግሃል ። ፈታኙ ወቅት ግን የታላቅነትህ መሰረት ነው ። ለመቸገር አልተፈጠርክምና ተቸግረህ እየኖርክ እንደተቸገርክ አትሞትም ። ችግርህ የጥንካሬና እድገትህ ቁልፍ ነው። ምቾት ከሚያስተምርህ በተሻለ ማጣትና ጉስቁልና የሚያስተምርህ ይበልጣል ። ስኬትን ይበልጥ የምትናፍቀው የከፋ አጣብቂኝ ውስጥ በሆንክ ጊዜ ነው ። በረከት ይዞ የሚመጣ ስቃይ አይገፋም ፤ የአካልና የመንፈስ ጥንካሬን የሚወልድ ፈተና ለለቅሶና ምሬት አይዳርግም ።

አዎ! ከተማርክ ትቀየራለህ ፤ አዲስ ነገር ካወክ የተሻለ ደረጃ ትደርሳለህ ፤ በሚገባ ከተፈተንክ ለላቀው ከፍታ ትበቃለህ ። አውላላ ሜዳ የትም አያደርስህም ፤ ለምንም አያበቃህም ፤ አካልህን አይፈትንም ፤ አቅምህን አያጎለብትም ። አቀበት ቁልቁቱ ፣ እሾህ ጋሬጣው ፣ አለቱ የመንፈስ ጥንካሬህንና የአካል ብቃትህን የሚፈትን ነው ። በቻልከው መጠን በፈተና ውስጥ እራስህን አጠንክር ፤ በስቃይህ እራስህን ገንባ ፤ በመከራህ ማንነትህን አንፅ ። መጥፎ በሚባሉ አጋጣሚዎች ውስጥ የተሻለውን የፈጠራ አቅምህን ተጠቀም ፤ የችግርህ ብቻ ሳይሆን የመሰናክልህም መፍትሔና ድልድይ ለመሆን ሞክር ። ቻይ ነህ ፤ ችግርን ፣ መከራን ፣ ስቃይን ቻይ ነህ ። እንዲሁ ብርታትና ጥንካሬን ፤ ስኬትና ከፍታንም ማምጣት ትችላለህ ። ከሚያስተምህ እየተማርክ ፣ ከሚጠቅምህ እየተጠቀምክ ሙከራህን ቀጥል ፤ ጥረትህን ግፋበት ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q