Get Mystery Box with random crypto!

ልብሽ አይከፈል! ወደፊት ምን ይታይሻል ? ደጋግሞ በሃሳብሽ የሚመጣው ነገር ምንድነው ? ከእ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ልብሽ አይከፈል!

ወደፊት ምን ይታይሻል ? ደጋግሞ በሃሳብሽ የሚመጣው ነገር ምንድነው ? ከእቅድሽ ጋር የሚሔድ ፣ ሃሳብሽን የሚደግፍ ፣ ብትወድቂ እንደሚያነሳሽ የምትተማመኚበት ሰው አብሮሽ አለን ? ታላቅና ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን ከፈለግሽ ጥንቃቄሽ የህይወት አጋርሽን ከመምረጥ ይጀምራል ። በሁለት ሃሳብ ፣ ባልተረጋጋና ባልፀና እምነት የምትቆዪበት ግንኙነት አጥፍቶሽ የሚጠፋ መሳሪያ ሊሆን እንደሚችል አስተውይ ። ተግባቦት የሌለው ፣ ያልተረጋጋ ፣ ያልሰከነ ፣ የማይታመን የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ያለ ሰው ትልቅ ዳገት አፋፍ ላይ እንደቆመ ሰው ነው ፤ አንድ ነገር ቢፈጠር ወደ ጥልቁ መውደቁ አይቀሬ ነው ። ምርጫሽን የማጥናት ፣ ስለራስሽ ህይወት የመወሰን ፣ ባመንሽው መንገድ የመጓዝ ሙሉ መብት አለሽ ። ያነሰውን ፣ የጎደለውን ፣ ክፍተቱን በሚገባ ታውቂያለሽ ።

አዎ! ጀግኒት..! ልብሽ አይከፈል! በሃሳብ አትዋጪ ፣ ግራ አይግባሽ ። ነገሮችን ግልፅ አድርጊ ፤ በጊዜ መንገድ አስይዢያቸው ። ያለሽበትን ግንኙነት ዘላቂነት እርግጠኛ ለመሆን ሞክሪ ። ያለፈው ካለፈ በኋላ ፣ የሆነውም ከሆነና ከተፈፀመ ቦሃላ ማልቀስና ማንባቱ ፋይዳ የለውም ። መጠንቀቅ ካለብሽ ከመጀመሪያው ተጠንቀቂ ፤ እራስሽን አሳልፈሽ ከሰጠሽና ማንነትሽን ካሳወቅሽ ቦሃላ ለእራስሽ የምታደርጊው ጥበቃ አያዋጣሽም ። ያልጣመሽ ነገር ቢቀር ብታተርፊ እንጂ አትጎጂም ። ሁለት ሃሳብ ሆነሽ የምትቆይበት ግንኙነት ሰላምሽን እንደሚነሳሽ እወቂ ። የዛሬው በትኩስ ፍቅር ተሸፍኖ ያልፍ ይሆናል ነገ ግን የሚያልፍበትም መንገድ አይኖረውም ። የትኛውም ክፍተት የሚሞላው በጊዜው ነው ።

አዎ! ጀግናዬ..! ህመምን ያተረፈልህ ፣ በስቃይ የሞላህ ፣ ሌላውን የህይወት ዘርፍ ያወከብህ ግንኙነት ዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገም እንደማይጠቅምህ ተረዳ ። ሰላም የሚነሳ ፣ የሚያስጨንቅ ፣ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ፣ በተከፈለ ሃሳብ እረፍት የሚነሳ ፍቅር ፍቅርነቱ ቀርቶ በህመም መልኩ መገለጡ አይቀርም ። ልውጣ ልቆይ ፣ ላቁመው አላቁመው ፣ ልተወው ልቀጥል እያልክ የምትቆይበት ግንኙነት አንደ የጠራና የተስተካከለ ውሳኔ እስካላስተላለፍክበት ድረስ ከባድ በሆኑ የስሜት መወዛወዝ ውስጥ ያስቀምጥሃል ።

አዎ! ግንኙነትህን መዝን ፤ ለምን ፍቅር ጀመርክ ? ከብዙ ሴቶች ለምን እሷን መረጥክ ? ልትደሰት ፣ ልትረዳዱ ፣ አብራቹ ትልቅ ቦታ ልትደርሱ ፣ የጋራ ህልምና ራዕይ ልትቀርፁ ፣ ለእውንነቱም በተመጣጣኝ ወኔ ልተተጉ አይደለምን ? አሁን ምን እየተካሔደ ነው ? በሃሳብ አብራቹ ናቹን ? ምንያክል ትግባባላቹ ? ትረዳዳላችሁ ? ትደጋገፋላቹ ? ምንያክልስ ድክመቶቻችሁን ትሸፋፈናላችሁ ? ፍቅራቹስ ከቃል በላይ ምድር ላይ ምን ይመስላል ? ፍቅርህን መዝን ፤ ግንኙነትህን አጥና ማስተካከል ያለብህን ጉዳይ በጊዜ አስተካክል ፤ ለህይወትህም ሰላም ስጥ ፣ መረጋጋትን አድል ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q