Get Mystery Box with random crypto!

ስንት ይሆን ኪሎዬ? በኑሮዬ መስመር ላይ በህይወት ጎዳና ጉዞዬ ከሆነ ውሃ አልባ ደመና ፍቅር ካል | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ስንት ይሆን ኪሎዬ?

በኑሮዬ መስመር ላይ በህይወት ጎዳና
ጉዞዬ ከሆነ ውሃ አልባ ደመና
ፍቅር ካልቋጠርኩኝ በልቤ ስልቻ
ዘግይቼ ከወጣው የምግባር እንጎቻ
ተስተካክሎ ቢቆም ልብስና ስጋዬ
በነፍስ ሚዛን ላይ ስንት ይሆን ኪሎዬ?