Get Mystery Box with random crypto!

የማንቂያ ደውል

የቴሌግራም ቻናል አርማ mhretab — የማንቂያ ደውል
የቴሌግራም ቻናል አርማ mhretab — የማንቂያ ደውል
የሰርጥ አድራሻ: @mhretab
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.86K
የሰርጥ መግለጫ

👉 የማንቂያ ደውል በመምህር ምህረታብ አሰፋ የሚቀርብላችሁ የቴሌግራም ቻናል ነው ቻናሉን በዚ ያገኙታል👉 @mhretab ለሌሎችም share ያድርጉ።
በቻናሉ ላይ ያላችሁን ማንኛውም አስተያየት ወይም ጥያቄ በዚህ bot ላይ 👉 @mhretabbot ወይም https://t.me/mhretabgroup group ላይ መጠየቅ ትችላላችሁ።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-06-20 11:27:32
የማንቂያ ደወል በቤቴል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ዝናብ የማይበግረው የቤተል ምዕመናን

@mhretab
1.7K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 11:53:57
ሰኔ 12 በቤቴል ቅዱስ ሚካኤል እንገናኝ:: ሼር በማድረግ ላልሰሙት እናሰማ

@mhretab
2.1K viewsedited  08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 18:55:59
ጾመ ሐዋርያት መጣልን።አባቶቻችን የሆኑት ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው፣ የመንግሥቱን ወንጌል ዞረው ለዓለም ከማስተማራቸው በፊት፣ጾም አውጀው ጾመዋል፣ በጸሎትም አምላካቸው ፊት ተንበርክከዋል። በጾምና በጸሎት የተጀመረው አገልግሎታቸውም የተሳካ ሆኖ አልጫውን ዓለም በወንጌል ጨውነት አጣፍጠዋል። ሥራችን የተሳካ ይሆን ዘንድ አምላካችን ፊት በጾምና በጸሎት ተንበርክከን እንለምን።ላሞቻችን ቀንድ
አላቸው እኛም ልብ አለን ብሎ ለውጊያ መነሳት ሞኝነት ነው።ምክንያቱም የላሞች ቀንድ የራሳቸውና የራሳቸው ነው። ልባችንም ብቻውን ጉልበት ሊፈጥር አይችልም።ሁሉን ይኑረን ለማለት ደግሞ ሰው ነንና የማንችላቸው ነገሮች አሉ። ስለዚህ ሁሉን ወደሚችለው ወደ እግዚአብሔር እንንበርከክ። "አልችልም" ማለት እምነት ነው።አለመቻልን በእግዚአብሔር እችላለሁ ማለትም እምነት ነው ።አልችልም ስንል አንድ ክንፍ
አብቅለናል።ያልቻልኩትን በእግዚአብሔር እችላለሁ ስንል ደግሞ የእምነትን ሁለተኛ ክንፍ አብቅለናል።ለእግዚአብሄር የችግራችንን ትልቅነት ከመንገር ይልቅ፣ለችግራችን የእግዚአብሔርን ትልቅነት
እንንገረው።መልካም የበረከት ጾም ይሁንልን።
2.0K viewsedited  15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 22:08:29
እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ። በቅድስት ሀገር እየረሳሌም ባሳለፍኩት የአስራ ሁለት ቀናት ቆይታዬ ከጎበኘዋቸው የተቀደሱ ሥፍራዎች መካከል አንዱ፣ ጌታ ከሞት ከተነሳ በ50ኛው ካዐረገ በ10ኛው ቀን መንፈስ ቅደስ የወረደበትን ሥፍራ ነው።
ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ሥፍራ፣ እግዚአብሔር መንፈስ
ቅዱስ ለሐዋርያት ወርዶበት የነበረውና ሐዋርያት ተሰብስበውበት የነበሩበትን የማርቆስ እናት የማርያም ባውፍልያ ቤት ነው። በሐዋርያት ፪ ላይ ተጽፎ እንደምናነበው፣ በዚህ ዕለት፣መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ከወረደ በኃላ፣ ሐዋርያት ከ15 ቋንቋ እስከ 72 ቋንቋ ተገልጦላቸው በልሳን አስተምረዋል። ዛሬ በቋንቋ ስንጣላ ይገርመኛል፣ቋንቋን የሰጠን እግዚአብሔር ነው። ያደለው በ72 ቋንቋ ፍቅርና ወንጌልን ያስፋፋል። ያላደለው ደግሞ ሶስትና አራት ቋንቋ ይዞ እርስ በእርሱ ይጠፋፋል። የቋንቋ አንድነት ሰውን አንድ አያደርገውም፣ የቋንቋ መብዛትም ሰውን አያጠፋውም። በዘፍጥረት 11 ላይ ዓለም በአንድ ቋንቋ ነበረች ግን በደለች።በበዓለ ሃምሳ ደግሞ በ ሰባ ሁለት ቋንቋ ዓለም እግዚአብሔርን አከበረች። ስለዚህ በሰማይና በምድር
የታወጀው ለሰው ልጆችም ሁሉ የተሰጠው ትልቁ ቋንቋ ፍቅር ነው። ሰው ትልቁን ቋንቋ ፍቅርን ከጣለ ከአካሉ ቀድሞ የሚታሰረውና መቃብር ድረስ ወርዶ የማያገለግለው ትንሹ ቋንቋ ያጣላዋል። በጽራ ጽዮን የወረደ መንፈስ ቅዱስ የሁላችንንም ሕይወት ይቀድስ።

@mhretab
1.8K views19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 05:21:31
ከዚህ በላይ ስብከት የለም፣ቃላት መቶ ሰው ቢሰብክ ተግባር ደግሞ ሺ ሰው ይሰብካል። የሞላው ገበታህን እያየህ፣ የተራቆተውን የወገን ገበታ ማሰብ፣በሠርግ ቤት ሆነህ፣ በሀዘን ድንኳን ውስጥ ያሉትን ማስታወስ፣ብዙሃን ከበውህ ሙሽራዬ እያሉ ሲያጨበጭቡልህ፣ በደስታ ስካር፣ አስከሬን እየጠቡ የሚሞቱትን ህጻናት፣እህል በዓይናቸው እንደዞረ
የሚያሸልቡትን አረጋውንና ጠኔ ያጨበጨበባቸውን፣ወግኖችህን
አለመርሳት፣የመንፈሳዊነት ጥግ ነው።ወንድሜ ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ እንዲሁም እህታችን ሳምራዊት እንኳን ለዚህ ክብር
አበቃችሁ።

@mhretab
1.6K views02:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ