Get Mystery Box with random crypto!

ጾመ ሐዋርያት መጣልን።አባቶቻችን የሆኑት ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው፣ የመንግሥቱን | የማንቂያ ደውል

ጾመ ሐዋርያት መጣልን።አባቶቻችን የሆኑት ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው፣ የመንግሥቱን ወንጌል ዞረው ለዓለም ከማስተማራቸው በፊት፣ጾም አውጀው ጾመዋል፣ በጸሎትም አምላካቸው ፊት ተንበርክከዋል። በጾምና በጸሎት የተጀመረው አገልግሎታቸውም የተሳካ ሆኖ አልጫውን ዓለም በወንጌል ጨውነት አጣፍጠዋል። ሥራችን የተሳካ ይሆን ዘንድ አምላካችን ፊት በጾምና በጸሎት ተንበርክከን እንለምን።ላሞቻችን ቀንድ
አላቸው እኛም ልብ አለን ብሎ ለውጊያ መነሳት ሞኝነት ነው።ምክንያቱም የላሞች ቀንድ የራሳቸውና የራሳቸው ነው። ልባችንም ብቻውን ጉልበት ሊፈጥር አይችልም።ሁሉን ይኑረን ለማለት ደግሞ ሰው ነንና የማንችላቸው ነገሮች አሉ። ስለዚህ ሁሉን ወደሚችለው ወደ እግዚአብሔር እንንበርከክ። "አልችልም" ማለት እምነት ነው።አለመቻልን በእግዚአብሔር እችላለሁ ማለትም እምነት ነው ።አልችልም ስንል አንድ ክንፍ
አብቅለናል።ያልቻልኩትን በእግዚአብሔር እችላለሁ ስንል ደግሞ የእምነትን ሁለተኛ ክንፍ አብቅለናል።ለእግዚአብሄር የችግራችንን ትልቅነት ከመንገር ይልቅ፣ለችግራችን የእግዚአብሔርን ትልቅነት
እንንገረው።መልካም የበረከት ጾም ይሁንልን።