2022-07-02 21:57:10
➢ ‹‹ #ባልንጀራህን_እንደራስህ_ውደድ።›› ዘሌ 19፡18፡፡
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
➢“አትበቀልም፥ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
ዘሌዋውያን 19፥18"
➢• ባልንጀራህን ውደድ የተባለው በሥላሴ አርአያ የተፈጠረውን ሰው በሰውነቱ መውደድ እንደሚገባ ለማመልከት ነው፡፡
‹➢‹ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃ አተኞችም በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
➢የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ?
➢አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።›› ማቴ 5፡42-48፡፡
➢• ጌታችን ትእዛዛትን ዘርዝሮ ባስረዳበት ክፍል ‹‹ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፡፡›› ብሎአል፡፡ ማቴ 19፡19፡፡
➢• ባልንጀራን መውደድ ለሰው መልካም ሉቃ 10፡25-37፣ ነፍሱ የምትድንበትን ያዕ 2፡8-9 ማድረግን ያካትታል፡፡
•➢ ባልንጀራንም መውደድ ለራስ የሚሹትን መልካም ነገር ለባልንጀራ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ‹‹እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና።›› ማቴ 7፡12፡፡
➢• ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ነገረንም ባልንጀራን መውደድ ከራስ ጥቅምም የባልንጀራን ጥቅም መመልከትንም የተመለከተ ነው፡፡ ‹‹እያንዳንዱ የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድስ እንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ፡፡›› ቀዳ ቆሮ 10፡24፣ ፊል 2፡2-4
➢• ባልንጀራውን የሚወድ ሰው ሰውነቱን በዝሙት፣ ሀብቱን በስርቆት፣ ስሙን በሐሰት በማጥፋት ወይም በሐሰት በመመስከር ባልንጀራው የሚጠፋበትን አያደርግም፡፡
➢• ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፡፡››ቀዳ ጢሞ 1፡5፡፡ እንዳለን፡፡
➢• ጌታችን ‹‹… ሁለተኛይቱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።… በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው።›› ማር 12፡31-33፡፡
➢• እግዚአብሔርን መውደድና ባልንጀራን መውደድ አይነጣጠሉም፡፡ ‹‹እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን። ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ
ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።›› ቀዳ ዮሐ 5፡2-3፡፡
➢• ‹‹እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል።
ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ። እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል። ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል? ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።››ቀዳ ዮ ሐ 3፡14-18፡፡
➢• ‹‹በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ። ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል
ማሰናከያም የለበትም፤ ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥
ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።›› ቀዳ ዮሐ 2፡9-11፡፡
•
➢ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን መውደድ የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ነው፡፡
➢‹‹ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን
እግዚአብሔርን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? እግዚአብሔርንም እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።›› ቀዳ ዮሐ 4፡20-21፡፡
እንደተባልነው እንደራሳችን ባልንጀሮቻችንን እንድንወድ ይገባል፡፡
➢• ‹‹ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው።›› ገላ 5፡14፡፡
➢• ‹‹ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።›› ፊል 2፡3-4፡፡
➢• ‹‹አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።›› ማቴ 19፡19፡፡
➢• ‹‹ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት።›› ማቴ 22፡39፡፡
➢• ‹‹ሁላችሁም በባልንጀራችሁ ላይ ክፉን ነገር በልባችሁ አታስቡ ፡፡›› ዘካ 8፡17፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን
@mhretab
@mhretab
984 views18:57