Get Mystery Box with random crypto!

ስንክሳር

የቴሌግራም ቻናል አርማ meselenigatu — ስንክሳር
የቴሌግራም ቻናል አርማ meselenigatu — ስንክሳር
የሰርጥ አድራሻ: @meselenigatu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 784
የሰርጥ መግለጫ

ሁሌ ዝቅ ማለትን አብዝቶ መስማትን ገንዘብ እናድርግ።
@meselenigatu
"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-14 22:43:56
12 viewsᴍᴇsᴇʟᴇ ɴɪɢᴀᴛᴜ, 19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 21:13:24 መኮንኑም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ወደ ላይኛው ግንጽ ላከው፡፡ በዚያም ከድያን ይዘው አሠቃዩት፡፡ ዘቅዝቀው ሰቅለውት ሳለ አልሞት ቢላቸው ዳግመኛ በብረት ምጣድ ውስጥ ጨምረው በእሳት አቃጠሉት፡ አሁንም ጌታችን ተገለጠለትና አዳነው፡፡ ታላቅ ቃልኪዳንም ገባለት፡፡ በመጨረሻም አንገቱን ሰየፉትና የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ሆነ፡፡ የአቅፋሃስ ከተማ ሹም የዮልያኖስ ባሮችም የአባ ቢማን ቅዱስ ሥጋ በክብር ወደ አገሩ ወሰዱት፡፡ በዚያም ገዳም ገድመውለት ቅዱስ ሥጋውን በክብር አኖሩ፡፡ ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገልጠው ለብዙ ሕሙማን ፈውስ ሰጠ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን።

ሰማዕቱ አባ በላኒ

ይኸውም አባ በላኒ በደቡባዊ ግብጽ አካ በምትባል አውራጃ የሚኖር ቄስ ነበረ፡፡ ክርስቲያኖችም በጌታችን ስም ሰማዕትነትን እየተቀበሉ እንደሆነ ሲሰማ እርሱም ምስክር ሆኖ ይሞት ዘንድ ተመኘ፡፡ ንብረቱንም ሁሉ ለድኆችና ለጦም አዳሪች ሰጥቶ ወደ እንዴናው መኮንን ዘንድ በመሄድ የጌታችንን አምላክነት መሰከረ፡፡ መኮንንኑም ይዞ ጽኑ በሆኑ ሥቃዮች ለብዙ ቀን አሠቃየው፡፡ አባ በላኒም ሰማዕትነቱን ፈጽሞ ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ የክብር አክሊልንም ተቀዳጀ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን።


ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ
እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ
ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ
እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ
እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ።

ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን
ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን
ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን
ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን
እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን።

ለዘጸሐፎ በክርታስ
ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ
ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ
ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ
በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ
ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ
እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን።

ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።

እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።

ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖

. ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

የቴሌግራም ቻናል፦ ➛@meselenigatu
የፌስቡክ ገጽ ፦
https://www.facebook.com/MeseleNigatuDek0

, ሐምሌ ➐ ቀን 2011 ዓ.ም
24 viewsᴍᴇsᴇʟᴇ ɴɪɢᴀᴛᴜ, edited  18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 21:13:23 ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው የቅዱሳኑን ሥጋ ከሰማዕቱ ከቅዱስ አንያኖስ ሥጋ ጋር በውስጧ አኖሩ፡፡ ከሥጋቸውም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራት እስከዛሬ ድረስ ይደረጋሉ፡፡ ጌታችንም በመከራቸው ጊዜ ተገልጦላቸው ታላቅ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን።

አባ ሚሳኤል

ይኸውም ቅዱስ የንጉሥ ልጅ ቢሆን የአባቱን ቤተ መንግሥት ንቆ በመተው ነዳይ ሆኖ በድብቅ መኖር ብዙ መከራን የተቀበለ ሲሆን ቀደም ብለን ገድላቸውን ላየነውና በዚሁ ዕለት ላረፉት ለአባ ኪሮስ የተደበቀ ምሥጢሩን የነገራቸውና ሲያርፍም እርሳቸው የቀበሩት ነው፡፡ ታሪኩም እንዲህ ነው፡-

አባ ኪሮስ በጌታችን ትእዛዝ ወደ ሳት ገዳም በሄደ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱን ሲሳለማት የእመቤታችንን ሥዕል ተመለከተና ከዐይኖቹ ዕንባ እያፈሰሰ ‹‹እመቤቴ ሆይ አስቢኝ›› አላት፡፡ ሥዕሊቱም አፍ አውጥታ በሰው አንደበት ‹‹ኪሮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው፣ ከዚህ ግን አልፈህ ወደ ሌላ ቦታ አትሂድ የአባትህን ዐፅም ትጠብቅ ዘንድ ይገባሃል›› አለችው፡፡ እርሱም ይህን ሰምቶ በፊቷ 700 ሰግደትን ሰገደ፡፡ በዚያ ያሉ መነኮሳትም አባ ኪሮስን መልኩ የተዋበ ሁለመናው ያማረ ሆኖ አገኙትና ‹‹ይህስ ከመንግሥት ከተማ የመጣ ነው በጸም በጸሎት ብዛትም ሰውነቱ አልጠወለገም›› ብለው በውስጣቸው እጅግ ከነቀፉት በኋላ ወደሚንቁት ቦታ ወሰዱት፡፡ አባ ኪሮስም በዚያ በተናቀ ቦታ ላይ በጽኑ ሕማም የታመመ ሰውን አገኘ፡፡ በታመመውም ሰው ራስጌ ቅዱስ ሚካኤል፣ በግርጌው ቅዱስ ገብርኤል፣ በቀኙ ቅዱስ ሩፋኤል፣ በግራው ቅዱስ ሰዳካኤል ሆነው በክንፋቸው ጋርደው ሲጠብቁት አገኛቸው፡፡ ከሰውም እነርሱም ማንም ያያቸው የለም፡፡ ለአባ ኪሮስም ሰላምታ በሰጡት ጊዜ እርሱም እጅግ አድንቆ ‹‹በልዕልና ነዋሪዎች ሆይ! ከዚህ ለምን ተቀመጣችሁ?›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ይህን ድኃ እንጠብቀው ዘንድ እግዚአብሔር አዞናል›› አሉት፡፡ አባ ኪሮስም ‹‹እስከመቼ ነው የምትጠብቁት?›› ሲላቸው ቅዱሳን መላእክቱም ‹‹እግዚአብሔር እስኪያሳርፈው ድረስ›› አሉት፡፡ አባ ኪሮስም ወደ ድኃው ጠጋ ብሎ ‹‹በዚህ በተናቀ ቦታ ተጥለህ መኖር ከጀመርህ ምን ያህል ጊዜ ሆነህ?›› አለው፡፡ በሕማም የተያዘው ድኃውም ‹‹በዚህ ቦታ 65 ዓመት ኖርኩ›› አለው፡፡ ከዚህም ውስጥ ሃያውን ዓመት በሕማም እንደኖረ ነገረው፡፡ አባ ኪሮስም ‹‹የገዳሙ አበ ምኔትና የገዳሙ መነኮሳት ይጎበኙሃልን?›› አለው፡፡ ድኃው ሚሳኤልም ‹‹አባቴ ሆይ! የለም አይጎበኙኝም፣ ፊታቸውን ካየሁ 15 ዓመት ሆኖኛል›› አለው፡፡ አባ ኪሮስም ማንነቱን በደንብ እንዲነግረው ሚሳኤልን ለመነው፡፡ ድኃው ሚሳኤልም ‹‹አባቴ የኬልቄዶን ንጉሡ እናቴም የራሕራሕ ንጉሥ ልጅ ናት፡፡ አባቴ ሆይ ዕውነት እልሃለሁ በአባቴ ቤተ መንግሥት አገልጋዮቹ ወርቁን፣ ብሩን በእግሮቻቸው ይረግጡታል›› አለው፡፡ አባ ኪሮስም ‹‹ወደዚህ ገዳም ማን አመጣህ?›› አለው፡፡ እርሱም ‹‹እንደ አንተ ያሉ ሁለት ሰዎች በአባቴ መጥተው ባደሩ ጊዜ በእኩለ ሌሊት ፊቱ ብሩህ የሆነ ሰው ወደኔ መጥቶ ‹ሚሳኤል ሆይ ሲነጋ ተነሥተህ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ሂድ› ሲለኝ እኔም ወጥቼ ከዚህ ቦታ ደረስኩ›› አለው፡፡ አባ ኪሮስም የአባቱን የአባ በብኑዳን ታሪክ ለሚሳኤል በመንገር አጽናናው፡፡
ከዚህም በኋላ አባ ኪሮስ በጽኑ ሕማም የተያውን ሚሳኤልን በሞት ያሰናብተው ዘንድ ወደ ጌታችን ለመነ፡፡ ጌታችንም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ ተገለጠለትና ‹‹ወዳጄ ኪሮስ ሆይ ጠርተኸኛልና መጣሁ›› አለው፡፡ አባ ኪሮስም ‹‹ጌታዬ ሆይ ይህ ሰው ሕማም በዝቶበታልና ያርፍ ዘንድ አናብተው›› ብለ ጌታችንን ለመነው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወዳጄ ኪሮስ ምን ያህል እንደምወድህ የመላእክት ሠራዊት ያዩና ያውቁ ዘንድ ይህን በሕመም በተያዘው ወዳጄ ላይ ጣለው›› ብሎ በእጁ የያዘውን የገነት ተክል አበባ ለአባ ኪሮስ ሰጠው፡፡ አባታችንም ያንን የገነት ተክል አበባ ከጌታችን እጅ ተቀብሎ በሚሳኤል ፊት ላይ በጣለው ጊዜ ወዲያውኑ የሚሳኤል ቅድስት ነፍሱ ያለ ምንም ፃዕር ወጣች፡፡ ጌታችንም ያችን ቅድስት ነፍስ ተቀብሎ ሳማት፡፡ ከእርሱም ጋር በብርሃን ሠረገላ አስቀመጣት፤ አውጥቶም በሰማያዊ ክብር አኖራት፡፡
ከዚህም በኋላ አባ ኪሮስ ወደ ገዳሙ አበ ምኔት ሄዶ ድኃውን ይቀብሩት ዘንድ ለመነኮሳቱ እዘዝ አለው፡፡ አበ ምኔቱም በመታጀር ‹‹ምን ግዴታ አለብኝ?›› አለው፡፡ አባ ኪሮስም ባስጨነቀው ጊዜ ሰባት መነኮሳትን አዘዘለት፡፡ እነርሱም መዕጠንታቸውን ይዘው ሲነሡ በዚህ ጊዜ አባ ኪሮስ ‹‹የሚያጥኑት አሉና የረከሱ ማዕጠንቶቻችሁን አስወግዱ ነገር ግን ዝም ብላችሁ ቅበሩት›› አላቸው፡፡ በዚያም ጊዜ አራቱ የመላእክት አለቆች የቅዱስ ሚሳኤልን ሥጋ ሲያጥኑት መዓዛው ገዳሙን መላው፡፡ መነኮሳቱም ‹‹ይህ የሚሸተን እጅግ የሚጥም መዓዛ ምንድነው? ወይስ ይህ መነኩሴ ሥራይን ያውቅ ይሆንን?›› ተባባሉ፡፡ የቅዱስ ሚሳኤልንም ሥጋውን ወስደው ከቀበሩት በኋላ ከመቃብሩ ጠበል ፈለቀና ለብዙ ሕሙማን ፈውስ ሆነ፡፡
አባ ኪሮስም የአባ ሚሳኤልን ክብር ለእነዚያ ግብዝ መነኮሳትና ለአበ ምኔቱ በነገራቸው ጊዜ ፈጽመው አዘኑ፡፡ ከአባ ኪሮስ እግር ሥር ወደቀው ‹‹ይቅር በለን›› ባሉት ጊዜ እርሱም ‹‹በአባ ሚሳኤል መቃብር ላይ ወድቃችሁ እርሱን ይቅር በለን በሉት›› አላቸው፡፡ እነርሱም አባ ኪሮስ እንደነገራቸው ባሉ ጊዜ ‹‹በእናንተ ምክንያት ወደ መንግሥተ ሰማያት ገብቻለሁና እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ›› የሚል ቃል ከአባ ሚሳኤል መቃብር ሰሙ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን።

ሰማዕቱ አባ ቢማ

ይህም አባ ቢማ ባለጸጋና በጎ ሥራዎችን የሚሠራ በአገርም የተሾመ ነው፡፡ በአንዲት ዕለትም ጌታችን በራእይ ተገለጠለት ወደ ከሃዲው መኮንን ዘንድ ሄዶ ስለ ስሙ መስክሮ ሰማዕት ይሆን ዘንድ ለዚህም የክብርን አክሊል እንዳዘጋጀለት ነገረው፡፡ በማግሥቱም ንብረቱን ሁሉ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ከመጸወተ በኋላ ሉቅያኖስወደሚባለው ከሃዲ መኮንን ዘንድ ሄዶ የጌታችንን አምላክነት መሰከረ፡፡ መኮንኑም አባ ቢማ ሹም እንደሆነ ዐውቆ ሊያባብለው ሞከረ፡፡ ለአማልክትም እንዲሠዋ አዘዘው፡፡ ነገር ግን ‹‹ሰማይንና ምድርን የፈጠረውን ጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ አመልካለሁ›› ብሎ ጣዖትቱን ረገመበት፡፡
ከዚህም በኋላ መኮንኑ አባ ቢማን ይዞ በእጅጉ አሠቃየው፡፡ በመጀመሪያ የመሰከረበትን ምላሱን አስቆረጠው፡፡ ጌታችንም የአባ ቢማን ምላስ እንደቀድሞው መለሰለት፡፡ ዳግመኛም አባ ቢማን በማበራያ ውስጥ አበራዩት፡፡ በብረት አልጋም ላይ አስተኝተው ከሥሩ እሳት አነደዱበት፡፡ ነገር ግን ጌታችን ፈወሰውና ያለ ምንም ጉዳት አስነሣው፡፡ ከዚህም በኋላ መኮንኑ ወደ እስክንድርያ ላከው፡፡ በዚያም ጌታችን ተገልጦለት አጽናናው፡፡ በወህኒ ቤትም ጥለውት ሳለ አባ ቢማ የተለያዩ ተአምራትን አደረገ፡፡ በአቅፋሃስ ከተማ ሹም በዮልያኖስ እኅት ላይ አድሮ ያሠቃየት የነበረውንም ጋኔን አስወጣውና ፈወሳት፡፡ ዜናውም በሁሉ ዘንድ ተሰማ፡፡ የሚያደርጋቸውንም ብዙ ተአምራት አይተው ብዙዎች በጌታችን አመኑ፡፡ መኮንኑም ይህንን ሲሰማ ተቆጥቶ አባ ቢማን አሠቃየው፡፡ የእጆቹንና የእግሮቹን ጥፍሮች አወለቋቸው፡፡ በእሳት ባጋሏቸው በብረት ሰንሰለቶች አሥረው ጎተቱት፡፡ በእሳት ውስጥም በጣሉት ጊዜ ከእሳቱ መካካል ቆሞ የሚጸልይ ሆነ፡፡ በአንገቱም ላይ ትልቅ ድንጋይ አሥረው ከባሕር ውስጥ ጣሉት ነገር ግን ጌታችን ከመከራዎቹ ሁሉ ይፈውሰው ነበር፡፡
16 viewsᴍᴇsᴇʟᴇ ɴɪɢᴀᴛᴜ, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 21:13:23 ውኃ እንዲጠጣ ቢነግሩት በልቡ ‹‹ለምን በመቅጃው ውስጥ ካለው ከጥሩው ውኃ አይሰጡኝም›› ብሎ አሰበና ሳይጠጣው ቀረ፡፡ ለሁለተኛም ጊዜ ጠጣው ብለው ታዛዥነቱንም እንዲያሳያቸው ቢለምኑት እምቢ አላቸው፡፡ ለ3ኛ ጊዜ ግድ ጠጣ ብለውት ደቀ መዝሙራቸው ውኃ ወዳለበት ኩስኩስት ቢሄድ ውኃው ዐይኑ እያየው ከኩስኩስቱ ላይ ደረቀና ጠፋበት፡፡ የጌታችን እግር እጣቢ መሆኑንም በነገሩት ጊዜ በድንጋጤ እንደበድን ሆነ፡፡ እንዲያረጋጋው በማሰብ ራሱን እብድ በማስመሰል ይኖር ወደነበረ አንድ ትልቅ ጻድቅ ጋር ልከውት አበረታው፡፡ ድንጋጤውም ባልተሸለው ጊዜ አባ ብሶይ ድጋሚ ወደዚያ አባት ላኩትና ሲሄድ ያንን ዕብድ መሳይ ቅዱስ አባት ዐርፈው አገኛቸው፡፡ አባ ብሶይም በትራቸውን ሰጥተው በአስክሬናቸው ላይ እንዲያኖረው ለረድኡ ሰጡትና ሄዶ በትራቸውን በአስክሬኑ ላይ አኑሮት ‹‹ተነሥተህ እንድታነጋግረኝ አባቴ አዞሃል›› ቢላቸው ከሞት አፈፍ ብለው ተነሥተው ‹‹አንተም ለአባትህ ታዛዥ ብትሆን ኖሮ የጌታችንን በረከት አጥተህ እንደዚህ ዓይነቱ ድንጋጤ ላይ ባልወደክ ነበር›› ብለውት ተመልሰው ዐረፉ፡፡
ጻድቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስም ለአባ ብሶይ በአካለ ነፍስ ተገልጦላቸው በሰማያት የመነኮሳትን ክብር አይቶ ቀድሞ የምንኩስናን ክብር እንዲህ መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ ይመነኩስ እንደነበር ሲነግራቸው እሳቸውም ‹‹አንተስ ምን ጎደለህ የጣዖት አምልኮን አጥፍተህ የቀናች ሃይማኖትን አጽንተሃል›› አሉት፡፡ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስም ‹‹ክብርንስ እግዚአብሔር አብዝቶ ሰጥቶኛል ነገር ግን የመነኮሳትን ክብር ያህል አይሆንም፣ እነርሱ በእሳት ክንፎች እየበረሩ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ሲገቡ አይቻቸዋለሁ›› ብሏቸዋል፡፡
ክብርና ምስጋና ይግባውና ‹‹መንፈስ ቅዱስ የለም›› እያለ የሚያስተምር አንድ የካደ መነኩሴ በእንዴና አገር መኖሩን በመንፈስ አውቀው አባ ብሶይ እጅግ አዘኑ›፡ መስሚያ ጆሮዎቻቸውንም ሦስት አድርገው ሄደው ከሚያስተምርበት ደርሰው ተገናኙት፡፡ ሕዝቡም አባታችንን ሰላምታ ሰጥተው ከእሳቸው ከተባረኩ በኋላ ስለ ሦስቱ ጆሮዎቻቸው ቢጠይቋቸው ‹‹እኔ ልዩ ሦስት አካላት አሉኝ፣ ሥራዬ ሁሉ በእነርሱ አምሳል ነው›› በማለት ሰለ ሥሉስ ቅዱስ አንድነትና ሦስትነት ቅዱሳት መጻሕፍትን እየጠቀሱ ሕዝቡን አስተምረው ከስሕተት ትምህርት ታድገዋቸዋል፡፡ ሕዝቡም ንስሓ ገብተው ወደ ቀናች ሃይማኖት ተመለሱ፡፡ አባ ብሶይን ደቀመዛሙርቶቻቸው ‹‹ጌታችን ለእኛም እንዲገለጥልን ጸልይልን›› አሏቸው፡፡ አባም በጸሎታቸው ጌታችንን ሲጠይቁት ‹‹ነገ በጠዋት ወደ ተራራው ይውጡ በዚያ እገለጥላቸዋለሁ›› አላቸውና ለመነኮሳቱ ሁሉ ይህንን ተናገሩ፡፡ በጠዋትም ተነሥተው ሁሉም ጌታን ለማየት እየተቻኮሉ ወጡ፡፡ በተራራው ግርጌም አንድ የደከሙ ሽማግሌ መነኮሳቱን ‹‹ወዴት ትሄዳላችሁ?›› እያሉ ሲጠይቋቸው ‹‹ጌታችን በተራራው ላይ ሊገለጥልን ነውና እርሱን ለማየት እንሄዳለን›› እያሉ እየተቻሉ ሲሄዱ ሽማግሌው ‹‹እኔንም ይዛችሁኝ ሂዱና ጌታችንን ልየው›› አሏቸው፡፡ ነገር ግን ሁሉም መነኮሳት ትተዋቸው ሄዱ፡፡ አባ ቢሶይ ከሁሉም መጨረሻ ሆነው ወደ ተራራው ሲወጡ ሽማግሌውን አይተው ‹‹አባቴ ወዴት መሄድ ፈልገው ነው?›› ሲሏቸው ሽማግሌውም ‹‹ወደ ተራራው መውጣት ፈልጌ ነበር›› አሏቸው፡፡ አባ ቢሶይ ሽማግሌውን ተሸክመዋቸው ተራራውን መውጣት ጀመሩ፡፡ በመጀመሪያ በጣም ቀለዋቸው ነበር ነገር ግን ተራራውን እየወጡ በመጡ ቁጥር እጅግ እየከበዷቸው መጡ፡፡ የተሸከሟቸውንም ሽማግሌ ሁለቱንም እግራቸውን ሲመለከቷቸው በችንካር ተቸንክረዋል፡፡ መልካቸውም እየተለወጠ መጣ፡፡ ያ ሽማግሌ ግን ራሱ ጌታችን ነበር፡፡
ወደ ተራራውም ወጥተው ጌታችንን ለማየት ሲጠባበቁ የነበሩት መነኮሳት ‹‹ጌታችን የታለ? መች ተገለጠልን?›› ብለው ጠየቋቸው፡፡ አባ ብሶይ ‹‹ጌታችንም ከተራራው ግርጌ ተገልጦላችሁ ነበር ነገር ግን እናንተ ትታችሁት መጥታችኋል›› በማለት የሆነውን ሁሉ ነገሯቸው፡፡ አባ ብሶይ እጅግ ብዙ ተአምራት በማድረግ በታላቅ ተጋድሎ ኖረው ሐምሌ 8 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን።

ቅዱሳን ሰማዕታት አቤሮንና አቶም

አቡነ ዮሐንስና ማርያም የተባሉት ደጋግ ወላጆቻው በሃይማኖት በምግባር አሳደጓቸው፡፡ አቤሮንና አቶምም መጻተኞችን በፍቅር በመቀበል በትሩፋትና በበጎ ሥራ ሁሉ ፍጹማን ሆኑ፡፡ እነዚህ ሁለት ወንድማማቾች ለንግድ ፈርማ ወደሚባለው አገር በሄዱ ጊዜ በዚያ ብዙ ሰማዕታት እንዳረፉና በእስርም ላይ እንዳሉ ተመለከቱ፡፡ ከንጉሡም ጭፍሮች የሰማዕቱን የቅዱስ አንያኖስን ሥጋ በብዙ ገንዘብ ገዝተው ወደ አገራቸው ወስደው በክብር አስቀምጠው በፊቱ ሁልጊዜ መብራቶችን አበሩ፡፡ ከሰማዕቱም ሥጋ ብዙ ተአምራት ተገለጡ፡፡ በዚህም ጊዜ ቅዱሳን የሆኑ አቤሮንና አቶም የዚህችን ዓለም ከንቱነት ተረድተው ዘላለማዊውን ሕይወት በመመኘት እነርሱም ምስክር ይሆኑ ዘንድ ተመካከሩ፡፡
ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ሄደው በከሃዲው መኮንን ፊት የጌታችን አመላክነት መሰከሩ፡፡ መኮንኑም ደማቸው እንደውኃ እስኪፈስ ድረስ ጽኑ ግርፋት አስገረፋቸው፡፡ እሳት ውስጥም እንዲጨምሯቸው አዘዘ፡፡ ዳግመኛም ስለታምና ረጃጅም በሆኑ ችንካሮች ሥጋቸውን ቸንክረው ከታች በእሳት አቃጠሏቸው፡፡ ጌታችንም መልአኩን ልኮ አዳናቸው፡፡ ዳግመኛም ዛፍ ላይ ዘቅዝቀው ሰቀሏቸውና በአፍ በአፍንጫቸው ብዙ ደም ፈሰሰ፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ ተገለጠላቸውና አበረታቸው፡፡ መኮንኑም አቤሮንና አቶም ደግመው በፊቱ ቆመው ሲመሰክሩ ሲያይ እጅግ አደነቀ፡፡ ወደ ፈርማ አገርም ላካቸው፡፡
በዚያ ያለው መኮንንም ለአማልክት እንዲሰግዱ ሲያዛቸው እነርሱ ግን ጣዖታቱን አቃለሉበትና እውነተኛውን አምላክ ሰበኩለት፡፡ እርሱም ኮምጣጤ፣ ሙጫና ጨው ደባልቆ አፍልቶ በአፍና በአፍንጫቸው ጨመረ፡፡ በብረት አልጋ ላይም አስተኝቶ ከታች እሳት አነደደባቸው፡፡ የእጅና የእግር ጥፍሮቻቸውን አውልቀው በብረት በትር ደበደቧቸው፡፡ በዚህም ወቅት የመኮንኑ ሚስት ሞተች፡፡ ቅዱሳን አቤሮንና አቶምም ወደጌታችን ጸልየው ከሞት አሥነሷት፡፡ መኮንኑም ከሕዝቡ ሁሉ ጋራ በጌታችን አመነ፡፡ ቅዱሳኑንም አክብሮ በሰላም ወደ አገራቸው ላካቸው፡፡
ሀገራቸው ገምኑዲ በደረሱም ጊዜ የቀረ ገንዘባቸውን በሙሉ አውጥተው ለድኆችና ጦም አዳሪዎች ሰጡ፡፡ የሰማዕቱን የቅዱስ አንያኖስንም ሥጋ ሰረባሞን ለሚባል አንድ ጻድቅ ሰው በአደራ ሰጥተው በፊቱም መብራት እንዲያበራ ነግረው እነርሱ ዳግመኛ ወደ ሰማዕትነት አደባባይ ሄዱ፡፡ በርሙን ወደሚባል አገርም ሄደው በከሃዲው መኮንን ፊት የጌታችንን አምላክነት ስመሰክሩ መኮንኑ ይዞ በእጅጉ አሠቃያቸው፡፡ ከጽኑ ግርፋት የተነሣ ደማቸው እንደውኃ ፈሰሰ፡፡ ደንቆና ድዳ የሆነች አንዲት ሴትም መጥታ ከቅዱሳኑ ደም ወስዳ ጆሮዎቿንና አፏን ብትቀባው ወዲያ መናገርና መስማት ቻለት፡፡ በዚህም ብዙዎች በጌታችን አመኑ፡፡
ከዚህም በኋላ መኮንኑ ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ የቅዱስ አቤሮንና የቅዱስ አቶምን ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ፡፡ እነርሱም ራሶቻቸውን ተሰየፉና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ሆነ፡፡ በመንግሥተ ሰማያትም የክብር አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ አባ ሰረባሞንም ከሕዝቡ መጥቶ ቅዱስ ሥጋቸውን ወደ አገራቸው ገምኑዲ ወሰደው፡፡ ከከተማዋም ውጭ በደረሱ ጊዜ የቅዱሳኑን ሥጋ የተጫነበት ሠረገላ የማይንቀሳቀስ ሆነ፡፡ ሰዎቹም በድንጋጤ ቆመው ሳሉ ‹‹ሥጋችን በውሰጡ ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር የመረጠው ቦታ ይህ ነው›› የሚልን ቃል ከሰማይ ሰሙ፡፡ በዚያም
15 viewsᴍᴇsᴇʟᴇ ɴɪɢᴀᴛᴜ, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 21:13:23 አባ ኪሮስም ይህን በተመለከተ ጊዜ ነው ጌታችንን ‹‹የአንተን ፍርድ ሳላውቅ እንዳልነሳ በሕያው ስምህ ምያለሁ›› በማለት ለአርባ ቀን ከተኛበት ሳይንቀሳቀስ ሥጋው ተሰነጣጥቆና ተፍቆ እስኪያልቅ ድረስ በደረቱ መሬት ላይ የተኛው፡፡ ጌታችንም በተገለጠለት ጊዜ ምክንያቱን ሲነግረው እንዲህ ነው ያለው፡- ‹‹ወዳጄ ኪሮስ ሆይ! እውነት እልሃለሁ እንደ አንተ ትዕግስትን ገንዘብ ያደረገ በምድር ላይ አላገኘሁም፡፡ ሥራው እሪያ ለሆነ ከምድያም ለመጣ ለዚያ መጻተኛ መነኩሴ የተቀደሰውን ለምን ሰጣችሁ? ስለዚህ ነገር በፊቴ እንዳይወቀስ የበቡኑዳን ሥጋ አንበሳ ይበላው ዘንድ ሰጠሁ፡፡ ለሁሉ እንደሥራው ይከፈለዋል፡፡ በዚህ ዓለም ፈጣሪው የገሠጸው ሰው ንዑድ ክቡር ነው ያለውን አልሰማህምን?› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ኪሮስ ‹ጌታዬ ፈጣሪዬ ፍርድህ ቅን ነው› አለው፡፡›› ጌታችንም የኃጥአንና የጻድቃን ነፍስ ስትወጣ ምን እንደምትመስል በየሀገሩ እየዞረ እንዲያይ ነገሮት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡

አባ ኪሮስም መላእክተ ብርሃናት የጻድቃንን ነፍስ ሲቀበሉና መላእክተ ጽልመትም የኃጥአንን ነፍስ ሲቀበሉ በገሃድና በግልጽ ያይ ነበር፡፡ ይህንንም ካየ በኋላ በየቀኑ እስከ ዘጠኝ ሺህ ስግደትን መስገድ ጀመረ፡፡ አባ በቡኑዳም ጌታችን የሰጠውን ክብር ያይ ዘንድ ተገልጦለት የተሰጠውን ክብር አሳይቶታል፡፡
ጌታችን ለአቡነ ኪሮስ የተገለጠበት ልዩ ሁኔታ፡- ‹‹አባታችን አባ ኪሮስም በበዓቱ ሳለ አንድ ቀን ጌታን እጅግ የጎበጠ ፈጽሞ ያረጀ መነኩሴ መስሎ በእጁ ምርኩዝ ይዞ ቀስ ቀስ እያለ ሄዶ ከጥላ ሥር ሲያርፍ ከሩቅ አየው፡፡ አባ ኪሮስም ከሩቅ አይቶ ወደ ‹ይህ መነኩሴ ፈጽሞ ደክሟል› ብሎ አደነቀ፣ ሊጠይቀውም ወደ እርሱ ሄደ፡፡ ያም ሽማግሌ ‹እግዚአብሔርን የምትወድ ከሆንክ ከአንተ ጋር ወደ በዓትህ ውሰደኝ› አለው፡፡ አባ ኪሮስም ‹ከወዴት መጣህ?› አለው፡፡ ሽማግሌውም ‹ኤረር ከሚባል ቦታ ነው የመጣሁት› አለው፡፡ መልሶም ‹ኤረር የሚሉት ቦታ የት ነው ያለው?› አለው፡፡ ያም ሽማግሌ ‹በምሥራቅና በምዕራብ፣ በደቡብና በሰሜን አይደለም› አለው፡፡ አባ ኪሮስም ‹አባ ምን ትላለህ? በምሥራቅና በምዕራብ፣ በደቡብና በሰሜን ካልሆነ በየት ሀገር ነው?› አለው፡፡ ሽማግሌውም ‹ዛሬስ አታውቀውም፣ ኋላ ግን ታውቀዋለህ› አለው፡፡ አባታችን አባ ኪሮስም ‹ሃይማኖትህ ከሃይማኖታችን ጋር አንድ ይሆናልን?› አለው፡፡ ሽማግሌውም ‹አዎ አንድ ነው› አለው፡፡ አባ ኪሮስም ‹ምስጋናህ በሰማይና በምድር የመላ አንድ አምላክ የሚሆን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በል› አለው፡፡ ያም ሽማግሌ አባታችን አባ ኪሮስ እንዳለው አለ፡፡ ያንጊዜም አባታችን አባ ከሮስ ‹እውነተኛ ክርስቲያን ነህና ወደ በዓቴም እንሂድ› አለው፡፡ ሽማግሌውም ‹አንተ ብርቱ ነህ፣ እኔ ግን ደካማ ሽማግሌ ነኝ፡፡ እግዚአብሔርን የምትወድ ከሆንክ አዝለህ ውሰደኝ› አለው፡፡ አባታችን አባ ኪሮስም ‹እሺ እሸከምሃለሁ› ብሎ ወገቡን በአፅፉ ታጥቆ አዝሎ ጥቂት ጥቂት እያለ ሔዶ ደከመ፡፡ ያ ሽማግሌም አባ ኪሮስን ‹ደከምክን?› አለው፡፡ አባታችንም ‹ጸሎትህ ይረዳኛል› አለው፡፡ ያንጊዜም የሽማግሌው መልኩ ተለወጠ፣ ነጎድጓድ ብልጭልጭታም ሆነ፡፡ አባ ኪሮስም ክብሩን ማየት ተሳነው፣ ዐይኑም ተጋረደና ወደ መሬት ወደቀ፡፡ ጌታችንም አባ ኪሮስን ‹ፈጽሜ ላከብርህ ነው እንጂ ላጠፋህ አልመጣሁምና ተነሥ› አለው፡፡ ‹በእውነት አንተ እግዚአብሔርን የምትፈራ ፈጽመህም የምታከብረኝ ነህና እኔም አሥራ ሁለት እጥፍ እወድሃለሁ› አለው፡፡ ‹እውነት እልሃለሁ ስምህን በገሃድ አባ ኪሮስ ብሎ የጠራ ብቻም ሳይሆን በሕልሙም ስምህን አባ ኪሮስ ብሎ የጠራውን ሁሉ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ› አለው፡፡››
ጌታችን ለአባ ኪሮስ በዕረፍቱ ጊዜ ተገልጦለት ገድሉን እንዳጻፈለት፡- ‹‹የአባ ኪሮስ ዕረፍቱ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር አባ ስምዖንና አባ ባውማ የተባሉ ቅዱሳንን ወደ እርሱ ላከለት፡፡ እነርሱም አባ ኪሮስን ባገኙት ጊዜ ተቃቅፈው አለቀሱ፣ መላእክትም አብረው ከእነርሱ ጋር አለቀሱ፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ‹ወዳጄ ኪሮስን በማጽናናት ፋንታ እንዲህ ታስፈራሩታላችሁን? ስለ ወዳጄ ስለ ኪሮስና ስለ እናንተ ያዘጋጀሁትን ዙፋኖችንና አክሊሎችን የመንግሥተ ሰማያት ቦታዎችን ብታዩ በሳቃችሁ ፈጽሞም ደስ ባላችሁ ነበር፡፡ አሁንም ስለ መከራው እጥፍ ድርብ ዋጋው እንዲበዛለት እነግራችኋለሁ› አላቸው፡፡ አሁንም ‹አባ ባውማ ወዳጄ ኪሮስ ከአባቱ ቤት ከወጣ ጀምሮ እስከዚህች ቀን ድረስ የሆነውን ሁሉ የገድሉን መጽሐፍ ጻፍ› አለው፡፡ አባ ስምዖንም አባ ኪሮስን ‹ከአንተ በኋላ ለሚነሱ ሰዎች ትምህርትና ተስፋ ይሆን ዘንድ የተቀበልከውን ቃልኪዳንና ገድልህን ንገረን› አለው፡፡ በአባታችን በአባ ኪሮስም መንፈስ ቅዱስ መልቶበት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ይነግራቸው ጀመር፡፡ አባ ባውማም ጻፈ፣ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ተፈጸመ፡፡ አባታችን አባ ኪሮስም ‹አጥንቶቼ ሊለያዩ ነውና ከመሬት አስተኙኝ› አላቸው፡፡ እነርሱም አስተኙት፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ ከራስጌው ተቀምጦ የፊቱን ላብ በነጭ ሐር እየጠረገለት ‹ወዳጄ ኪሮስ ሆይ! ምን ሆነሃል አትፍራ ምንስ ትሻለህ?› አለው፡፡ አባ ኪሮስም ‹የምሻውስ እመቤታችን ድንግል ማርያምን አያት ዘንድ ነው› አለው፡፡ እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ በታላቅ ግርማ መጥታ አጽናናችው፣ አባታችንም ‹እመቤቴ ሆይ! በቃልኪዳንሽ አስቢኝ› አላት፡፡ ጌታችንም አቅፎ ይዞ ሳመው፡፡ ‹ወዳጄ ኪሮስ የላይኛውን ሰማያዊውን አስብ ሥጋ ግን ከመሬት የተገኘ ከንቱ ነውና› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ዳዊት ዓሥር አውታር ባለው በገናው ዘመረለት ቅድስት ነፍሱ ሐምሌ ስምንት ቀን ከሥጋዋ ተለየች፡፡ ጌታችንም በእጁ ተቀበላት፡፡ መላእክቱንም ‹የኪሮስ ሥጋ በዚህ እንዲቀበር አልፈቅድም› አላቸው፡፡ ይህንንም ብሎ ሥጋውን ከእርሱ ጋር እንዲያሳርጉት አዘዛቸው፡፡ አዳም ቀድሞ ከነበረበት ከደብር ቅዱስ ደረሰ፡፡ ነፍሱን ከሥጋው ጋር አዋሕዶ ጸሎተ ቅዳሴ አደረሰ፡፡ ተስፋ ያደረገለትን የብርሃን አክሊሎችንና ዙፋኖችን በረከት የመላበት መንግሥተ ሰማያትን አሳየው፡፡ ለዘለዓለሙ ወደማይሞትበት ወደ ገነት አስገባው፡፡
የአባ ኪሮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን።

አባ ብሶይ ዘገዳመ መቃርስ

የዓለም ሁሉ ኮከብ የተባሉት የአባ መቃርስ ገዳሙ አባ ብሶይ በግብፅ ተወለዱ፡፡ ሰባት ወንድሞችም ስለነበሯቸው እናታቸው በሌሊት ራእይ አየች፡፡ መልአኩ ተገልጦላት ‹‹እግዚአብሔር ያገለግለኝ ዘንድ ከልጆችሽ አንዱን ስጪኝ›› ብሎሻል አላት፡፡ ‹‹ሁሉም የእርሱ ገንዘቦቹ ናቸውና የወደድከውን ውሰድ›› አለችው፡፡ መልአኩ የብሶይን ራስ ይዞ የተመረጠው እርሱ መሆኑን ነገራት፡፡ የብሶይም ሥጋው የከሳ ነበርና እናቱ መልአኩን ‹‹ከጠንካራዎቹ ውስጥ አንዱን ውሰድ›› አለችው፡፡ መልአኩም እግዚአብሔር የመረጠው ብሶይን መሆኑን ነግሯት ተሰወረ፡፡
አቡነ ብሶይ ባደጉ ጊዜ ወደ አስቄጥስ ገዳም ገብተው በአባ ባይሞይ እጅ መነኮሱ፡፡ እርሳቸውም ዮሐንስ ሐፂርን ያመነኮሱት ናቸው፡፡ ብሶይም ከበፊቱ አብዝተው በጽኑ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ ምንም ሳይቀምሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት ይጾሙ ይጸልዩ ነበር፡፡ ጌታችንም ብዙ ጊዜ እየተገለጠላቸው ያነጋግራቸው ነበር፡፡ የጌታችንን እግሩን እያጠቡት እጣቢውን ይጠጡ ነበር፡፡ አንድ ቀንም እንዲሁ ጌታችንን ያጠበበትን ውኃ ግማሹን ብቻ ጠጥተው ግመሹን ለደቀ መዝሙራቸው ተውለት፡፡ ደቀ መዝሙራቸውም በመጣ ጊዜ ከእግር ማጠቢያው ውስጥ ያለውን
13 viewsᴍᴇsᴇʟᴇ ɴɪɢᴀᴛᴜ, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 21:13:23 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም አሜን።
ሐምሌ 8 ጌታችን ፈጽሞ ባረጀ መነኩሴ አምሳል ተገልጦላቸው በእጁ ምርኩዝ ይዞ ከጥላ ሥር አረፍ ብሎ ቢያገኙት "ወደ በዓትህ ውሰደኝ" ያላቸውና እርሳቸውም "ሃይማኖትህ ከሃይማኖታችን ጋር አንድ ይሆናልን?" ብለው የፈተኑት ታላቁ ጻድቁ አቡነ ኪሮስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ በሽማግሌ የተመሰለ ጌታችንም "አዎ አንድ ነው" ቢላቸው እስቲ "ምስጋናህ በሰማይና በምድር የመላ አንድ አምላክ የሚሆን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በል" ብለው ከፈተኑት በኋላ አዝለው ወደ በዓታቸው ወስደውታል፡፡

➛ የዓለም ሁሉ ኮከብ የሆኑት የአባ መቃርስ ገዳሙ አባ ብሶይ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ይኸውም ጻድቅ እንደ አባ ኪሮስ ሁሉ ጌታችን በመንገደኛ ሽማግሌ አምሳል ቢገለጥላቸው እግሩን አጥበውት ሲጨርሱ የጌታችንን የእግሩን እጣቢ የጠጡ ናቸው፡፡

➛ የንጉሡ ልጅ ሆኖ ሳለ ከአባቱ ቤተ መንግሥት መጥቶ ነዳይ ሆኖ በድብቅ በመኖር ብዙ መከራን የተቀበለው አባ ሚሳኤል ዕረፍቱ ነው፡፡ እርሱም በዚህ ዕለት ላረፉት ለአባ ኪሮስ የተደበቀ ምሥጢሩን የነገራቸውና ሲያርፍም እርሳቸው የቀበሩት ነው፡፡

➛ ወንድማማቾቹ የከበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት አቤሮንና አቶም ዕረፍታቸው ነው፡፡
ሰማዕቱ አባ በላኒ ዕረፍቱ ነው፡፡
ሰማዕቱ አባ ቢማ ዕረፍቱ ነው፡፡

አቡነ ኪሮስ

አባቱ አብያ የሮም ንጉሥ የነበረ ሲሆን እናቱ ሜናሴር 30 ዓመት መካን ሆና ከኖረች በኋላ በጾም በጸሎት ጸንታ ስትኖር ሁለት ልጆችን ወለደች፡፡ እነርሱም በኋላ አባ ኪሮስ የተባለው ዲላሶርና ቴዎዶስዮስ ናቸው፡፡ አባታቸው ሞቶ ታላቁ ልጅ ቴዎዶስዮስ ሲነግሥ ታናሹ ዲላሶር ድርሻዬን ስጠኝ ብሎ ሲጠይቀው ታላቁ ‹‹የእኔ የሆነው ሁሉ ያንተ ነው፣ ዕድሜህም ቢሆን አሁን ገና ነው›› ቢለው በዚህ ተቆጥቶና አኩርፎ ወደ አንድ ተራራ ሥር ሄዶ ተቀመጠ፡፡ በዚያም ሳለ እግዚአብሔር ዓለም ለእርሱ እንዳልተገባችው ነገረው፡፡ ወደ አባ በቡኑዳ ገዳምም ሄዶ እንዲመነኩስና ለብዙዎችም አባት እንደሚሆን ስለነገረው አባ በቡኑዳ ጋር ሄዶ ተቀመጠ፡፡ አባ በቡኑዳም ደመና ጠቅሶ በእርሷም ላይ ሆኖ ወደ አስቄጥስ ገዳም በመሄድ ከአበምኔቱ ከአባ ተርዋ ዘንድ ልብሰ ምንኩስናን አምጥቶ አልብሶታል፡፡ ስሙንም አባ ኪሮስ አለው፡፡ አባ ኪሮስም አባ በቡኑዳን እያገለገለው በዚያው ኖረ፡፡
አቡነ ኪሮስ በገዳም የነበሩና በኃጢአታቸው ምክንያት በጋራ የተኮነኑ የ798 ነፍሳትን ጌታችንን ካልማርክልኝ ብለው እንዲሁ ሁለት ጊዜ ዐርባ ቀን ሰማንያ ቀን ሙሉ ግለቱ ከሚያቃጥል የባልጩት ድንጋይ ላይ ተኝተው ለምነዋል፡፡ ከባጩቱ ድንጋይ ግለትና ከለቅሷቸውም የተነሳ ሁለቱም ዐይኖቻቸው ታውሩ፣ ሰውነታቸውም ተጠበሰ፡፡ የወዳጆቹ ፍቅር የሚያሸንፈው መድኃኔዓለምም ተገልጦላቸው ዐይነ ብርሃናቸውን መልሶ ሰውነታቸውንም ፈውሶላቸው እነዚያንም ነፍሳት ከሞት አስነሥቶለት የበደሉትን በይቅርታ እንዲክሱና በምግባር እንዲኖሩ ካደረገለት በኋላ ለአባ ኪሮስ ለሌላውም ትውልድ የሚሆን የዘለዓለም ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡

አንድ ቀን አባ ኪሮስ ምግብ ፍለጋ ወደ ሀገር ወጥቶ ሲሄድ በመንገድ ላይ የኬልቄዶን ንጉሥ ሞቶ ካህናቱ ማዕጠንት ይዘው ከፊት ከኋላ እየዘመሩ እጅግ ባማረ ሥርዓት ቀብሩ ሲፈጸም አየ፡፡ መጀመሪያ ላይ የንጉሡ ልጅ እያገባ መስሎት ነበርና ባየው ሥርዓተ ቀብር እየተደነቀ ጥራጥሬውን ሰብስቦ ወደ አባ በቡኑዳ ሲመለስ አባ በቡኑዳን አንበሳ ገድሎት ሲበላው አጥንቱም ከመሬት ተበትኖ አገኘው፡፡ አባ ኪሮስ ዐፅሙን ሰብስቦ ከበዓቱ ቀብሮት ወደ ውጭ ወጥቶ መራራ ልቅሶን አለቀሰ፡፡ የንጉሡንና የአባ በቡኑዳን የአሟሟትና የቀብር ሁኔታ አነፃፅሮ እንዲህ እያለ እግዚአብሔርን ወቀሰ፡- ‹‹ጌታ ሆይ ለምን እንዲህ ታደርጋለህ? ፍርድህ መልካም አልሆነም፡፡ በዓለም በመንግሥት በመብል በመጠጥ በደስታ የኖሩትን በክብር እንዲቀበሩ ታደርጋለህ፡፡ አባት እናታቸውን፣ ሚስትና ልጆቻቸውን ትተው በተራራና በዋሻ በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በድካም የሚኖሩትን ያንተን ቅዱሴን ደሞ ሥጋቸውን ለአራዊት ትሰጣለህ ፍርድህ መልካም አልሆነም፡፡ ስለዚህ የአንተን ፍርድ ሳላውቅ እንዳልነሳ በሕያው ስምህ ምያለሁ›› ብሎ በደረቱ መሬት ላይ ተኛ፡፡ ለዐርባ ቀንም ከተኛበት አልተንቀሳቀሰም ነበርና ሥጋው ተሰነጣጥቆና ተፍቆ አለቀ፡፡
ጌታችንም ከዐርባ ቀን በኋላ የአባ በቡኑዳን ጉዳይ ምክንያቱን ሊነግረው ፈቃዱ ሆነና ተገለጠለት፡፡ አባ ኪሮስም ሊነሳ ቢሞክር ሰውነቱ ከመሬት ጋር ፈጽሞ ተጣብቆ ነበርና መነሣት ተሳነው፡፡ ጌታችንም ምድሪቷን ‹‹የኪሮስን ሥጋ ተይ አትያዥ›› ብሎ በማዘዝ እጁን ይዞ ካነሳው በኋላ ሰውነቱን ቢዳስስለት እንደ ሕፃን ልጅ ሆነ፡፡ ዐይኑም ተከፈተለትና ጌታችን እንደ መብረቅ ሲለወጥ አየውና ከመሬት ላይ ወደቀ፡፡ ጌታችንም አበረታውና ‹‹እንደ አንተ ትዕግስትን ገንዘብ ያደረገ በምድር ላይ አላገኘሁም›› አለውና አባ በቡኑዳን ለምን በአንበሳ እንዲበላ እንዳደረገው ምክንያቱን በዝርዝር ነገረው፡፡ አባ ኪሮስም ምክንያቱን ሲሰማ ‹‹ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ፍርድህ ቅን ነው›› በማለት አመሰገነው፡፡ ጌታችን ለአባ ኪሮስ የነገረው ምክንያትና ምሥጢር ምንድነው? ከተባለ ቀጥሎ ባለው ርዕስ ላይ መልሱን ያገኙታል፡፡
የተቀደሰውን ለውሾች መስጠት ቅጣት እንዳለበትና በረከትንም እንደሚያሳጣ፡-ለአባ በቡኑዳ ቅዱስ ሚካኤል ሁልጊዜ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ እያመጣ ይመግበው ነበር፡፡ አንድ ቀን አንድ መነኩሴ ወደ አባ በቡኑዳ ዘንድ መጥቶ ከገዳመ አስቄጥስ ነው የመጣሁት ቢለው ደስ ብሎት ተቀበለው፡፡ ያም መነኩሴ ከአባ በቡኑዳ ጋር ሳለ እንደተለመደው ቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊውን ኅብስት አምጥቶ ለአባ በቡኑዳ ሰጠው ነገር ግን መነኩሴው ይህን አያይም ነበር፡፡ መጀመሪያ በዓቱ ውስጥ ምንም የሚበላ የሌለበት ባዶ መሆኑን አይቶ አባ በቡኑዳን ‹‹የሚበላ የለህምሳ!›› ሲለው ‹‹እግዚአብሔር ይመግበናል›› ብሎት ነበርና በኋላ ኅብስቱን ብቻ ቢመለከት ‹‹ይህ ሰው መሠሪ ነው›› ብሎ በልቡ አሰበ፡፡ አባ በቡኑዳም የልቡን ክፉ ሃሳብ አውቆበት ገሠጸውና ኅብስቱን አብረው በሉ፡፡ አባ ኪሮስ ግን በትሕትና ይላላካቸው ነበር፡፡ ያ እንግዳ መነኩሴም እነርሱ ሳያዩት እየቆረሰ ደብቆ በልብሱ ያዘና ወደ አስቄጥስ ተመለሰ፡፡ በዚያም እንደደረሰ ገዳማውያኑን በሙሉ ጠራና ሸሽጎ ያመጣውን ሰማያዊ ኅብስት አሳያቸው፡፡ ‹‹ከየት አመጣኸው?›› ቢሉት ‹‹በዮርዳኖስ በረሃ ውስጥ አንዲት ዋሻ አለች፡፡ በውስጧም በቡኑዳ የሚባል አንድ መሠሪ ሰው አለ›› እያለ ሲናገር ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ያችን የኅብስት ቁራሽ ነጥቆ ወደ ሰማይ አሳረጋት፡፡ እግዚአብሔርም ቅዱስ ሚካኤልን ‹‹መልካም አገልጋዬ ሆይ! የተቀደሰውን ለውሻ በመስጠቱ በቡኑዳ ክፉ አደረገ፣ ስለዚህም በአንበሳ አፍ ይሞታል፣ ይህችም በረከት ከእርሱ ትከለከላለች፣ እስከ ዕለተ ሞቱ ምግብ ትሆነው ዘንድ በበረሃ ለሚኖር ስሙ ፊልሞና ለሚባል መነኩሴ ስጠው›› አለው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እንደታዘዘው አደረገ፡፡ በቡኑዳም በአንበሳ ተበልቶ ሞተ፡፡
20 viewsᴍᴇsᴇʟᴇ ɴɪɢᴀᴛᴜ, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 21:10:33
23 viewsᴍᴇsᴇʟᴇ ɴɪɢᴀᴛᴜ, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:24:18
የስማቸው አጻጻፍና የፊደላቱ ትርጉም

የቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደላት ትርጉም ያለው በመሆኑ "ስላሴ" ወይም "ሥላሤ" ሳይሆን “ሥላሴ” በማለት የፊደላቱን ቀለም አስተካክሎ መጻፍ ይገባል።)
የቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደላት ትርጉም ያለው በመሆኑ "ስላሴ" ወይም "ሥላሤ" ሳይሆን “ሥላሴ” በማለት የፊደላቱን ቀለም አስተካክሎ መጻፍ ይገባል። ይህ “ሠ” ሠራተኛው ወይም ንጉሡ ሠ የሚባል ሲሆን፤ ይህ “ሰ” ደግሞ እሳቱ ሰ ይባላል።
➧ “ሥላሴ” ከስማቸው ፊደል ሠራተኛው "ሠ" ይገኛል ይኸውም ቅድስት ሥላሴ ዓለምን መፍጠራቸውን ያመለክታል፤ በተጨማሪም ንጉሡ "ሠ" ይባላል ይኸውም ቅድስት ሥላሴ የፈጠሩትን ፍጥረት የሚገዙ የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ያስረዳል። በአጠቃላይ በዚህ "ሠ" ስማቸው መጻፉ ቅድስት ሥላሴ ዓለምን ፈጥረው የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ያስረዳል።
➧ ከስማቸው ፊደል ላይም እሳቱ "ሰ" ይገኛል ይኸውም እሳት ባህር ገደል ካልከለከለው በስተቀር ሁሉን ላጥፋ ቢል ይቻለዋል ቅድስት ሥላሴም ቸርነታቸው ካልገደባቸው በስተቀር ሁሉን ላጥፋ ቢሉ የሚቻላቸው መሆኑን ያስረዳል።
- አንድም፦ እሳት ወርቅን ከእድፉ፣ ምግብንም ከተዋህስያን እንደሚያጠራ ቅድስት ሥላሴም ሰውን ከኃጢኣቱ በምህረታቸው የሚያነጹ ናቸው።
በቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደል ላይ ሁለት በፊደል ቤት ቢለያዩም ተመሳሳይ ድምጸ ቀለም ያላቸው "ሥ" "ሳ" እና በፊደል ቤትም በድምጸ ቀለም ከሁለቱ የምትለይ "ላ" እናገኛለን። ይህም "ሥ" እና "ሴ" የአብ እና የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ናቸው በድምጽ ቀለም መመሳሰላቸውም አብና መንፈስቅዱስ ሰው አልሆኑም፥ "ላ" የወልድ ምሳሌ ናት "ላ" በድምጸ ቀለም ከሁለቱ እንደምትለይ ወልድም በተለየ አካሉ ሰው በመሆኑ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ይለያል።
@meselenigatu
55 viewsᴍᴇsᴇʟᴇ ɴɪɢᴀᴛᴜ, edited  12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:47:15
42 viewsᴍᴇsᴇʟᴇ ɴɪɢᴀᴛᴜ, 11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ