Get Mystery Box with random crypto!

የስማቸው አጻጻፍና የፊደላቱ ትርጉም የቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደላት ትርጉም ያለው በመሆኑ 'ስ | ስንክሳር

የስማቸው አጻጻፍና የፊደላቱ ትርጉም

የቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደላት ትርጉም ያለው በመሆኑ "ስላሴ" ወይም "ሥላሤ" ሳይሆን “ሥላሴ” በማለት የፊደላቱን ቀለም አስተካክሎ መጻፍ ይገባል።)
የቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደላት ትርጉም ያለው በመሆኑ "ስላሴ" ወይም "ሥላሤ" ሳይሆን “ሥላሴ” በማለት የፊደላቱን ቀለም አስተካክሎ መጻፍ ይገባል። ይህ “ሠ” ሠራተኛው ወይም ንጉሡ ሠ የሚባል ሲሆን፤ ይህ “ሰ” ደግሞ እሳቱ ሰ ይባላል።
➧ “ሥላሴ” ከስማቸው ፊደል ሠራተኛው "ሠ" ይገኛል ይኸውም ቅድስት ሥላሴ ዓለምን መፍጠራቸውን ያመለክታል፤ በተጨማሪም ንጉሡ "ሠ" ይባላል ይኸውም ቅድስት ሥላሴ የፈጠሩትን ፍጥረት የሚገዙ የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ያስረዳል። በአጠቃላይ በዚህ "ሠ" ስማቸው መጻፉ ቅድስት ሥላሴ ዓለምን ፈጥረው የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ያስረዳል።
➧ ከስማቸው ፊደል ላይም እሳቱ "ሰ" ይገኛል ይኸውም እሳት ባህር ገደል ካልከለከለው በስተቀር ሁሉን ላጥፋ ቢል ይቻለዋል ቅድስት ሥላሴም ቸርነታቸው ካልገደባቸው በስተቀር ሁሉን ላጥፋ ቢሉ የሚቻላቸው መሆኑን ያስረዳል።
- አንድም፦ እሳት ወርቅን ከእድፉ፣ ምግብንም ከተዋህስያን እንደሚያጠራ ቅድስት ሥላሴም ሰውን ከኃጢኣቱ በምህረታቸው የሚያነጹ ናቸው።
በቅድስት ሥላሴ የስማቸው ፊደል ላይ ሁለት በፊደል ቤት ቢለያዩም ተመሳሳይ ድምጸ ቀለም ያላቸው "ሥ" "ሳ" እና በፊደል ቤትም በድምጸ ቀለም ከሁለቱ የምትለይ "ላ" እናገኛለን። ይህም "ሥ" እና "ሴ" የአብ እና የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ናቸው በድምጽ ቀለም መመሳሰላቸውም አብና መንፈስቅዱስ ሰው አልሆኑም፥ "ላ" የወልድ ምሳሌ ናት "ላ" በድምጸ ቀለም ከሁለቱ እንደምትለይ ወልድም በተለየ አካሉ ሰው በመሆኑ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ይለያል።
@meselenigatu