Get Mystery Box with random crypto!

merkatotube

የቴሌግራም ቻናል አርማ merkatotube — merkatotube M
የቴሌግራም ቻናል አርማ merkatotube — merkatotube
የሰርጥ አድራሻ: @merkatotube
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.03K
የሰርጥ መግለጫ

Important Ethiopian and international news.
If you have tips/ጥቆማ @merkatotube_bot
We are open 24/7

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-01 13:50:06
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ችሎት በመጪው ማክሰኞ መጋቢት 26፣ 2015 ዓ.ም መቀጠሩ ተዘግቧል።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከፍሎሪዳ በግል አውሮፕላናቸው ወደ ኒውዮርክ በመብረር ለፌደራል ደኅንነት አካላት እጃቸውን ይሰጣሉ ተብሏል።
ትራምፕ የወሲብ ፊልም ተዋናይት የሆነችውን ስቶርሚ ዳንኤልስን ዝም ለማሰኘት ከፍለዋታል በተባለው 130 ሺህ ዶላር ክፍያ ጋር በተያያዘ ተከሰዋል።


@merkatotube @merkatotube_bot
1.4K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 12:25:06
በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ የማስነሳት ሂደት የጸጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ መውሰዳቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።በአንዳንድ ቦታዎች የማፍረስ እና በግዳጅ የማስነሳቱ ሂደት ለሁከት፣ ለእንግልት፣ ለአካልና ሥነልቦና ጉዳት እና ለእስር ምክንያት መሆኑንም ነው ኢሰመኮ የገለጸው።

@merkatotube @merkatotube_bot
1.4K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 10:50:05
አስራ አንድ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሶማሊያ ውስጥ ቦሳሶ አቅራቢያ በደረሰ ከባድ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታወቀ። የድርጅቱ የሶማሊያ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ይህ መኪና አደጋ የደረሰው ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 19/2015 ዓ.ም. ምሽት ላይ ሲሆን፣ ከሟቾቹ በተጨማሪ ቢያንስ 20 የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል። አደጋው የደረሰባቸው በባሕር በኩል ወደ የመን ለመሻገር የሚገዙ መሆናቸው ተነግሯል።


@merkatotube @merkatotube_bot
1.3K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 09:25:06
በቅርቡ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በተጨማሪ በ38 ዓመቷ ሩሲያዊ ፖለቲከኛም ላይ የእስር ትዕዛዝ አውጥቷል። ማሪያ ሎቫቫ ቤሎቫ ህጸናትን እና ታዳጊዎችን በሕገወጥ መንገድ በማፈናቀል ወንጀል ነው ክስ የቀረበባቸው።


@merkatotube @merkatotube_bot
1.3K views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 04:25:06
“ኡጋንዳውያኑ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የምጽዓትን ቀን ሽሽት አይደለም” የኛንጋቶም ባለሥልጣን
------------------------------------------------------------------------------------------------------
ከኡጋንዳ ምሥራቃዊ ክፍል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት የምፅዓትን ቀን ሽሽት ነው መባሉ ሐሰት መሆኑን የኛንጋቶም ወረዳ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ገለጹ።
በደቡብ ኦሞ ዞን፣ የኛንጋቶም ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት ሎኪኛኒጋ ሙርሌ፣ ኡጋንዳውያኑ በወረዳቸው እንደሚገኙ አረጋግጠው፣ “አመጣጣቸው አካባቢውን ለማየትና የቤተክርስቲያን መልዕክት ለማድረስ ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ይህንንም ከፌደራል ደኅንነት መሥሪያ ቤት ለመጡ አካላት ማስረዳታቸውን ምክትል አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ሐሙስ መጋቢት 21/2015 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ ኡጋንዳውያኑ “የምጽዓት ቀን በአካባቢያችን ይኖራል። ሞት መፈናቀል ይኖራል ብለው በመስጋት የገቡ መሆናቸውን” ተናግረዋል።
ኡጋንዳውያኑ ከምሥራቅ ኡጋንዳ በተለይም ሴራሬ፣ ኩሚ እና ጎራ ከተባሉ አካባቢዎች የመጡ መሆናቸውንም ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል።
የቱርክ መንግሥት የዜና ወኪል አናዶሉ ከአንድ ወር በፊት፣ የኡጋንዳን ፖሊስ ጠቅሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን የአንድ ሃይማኖታዊ ቡድን ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን ዘግቦ ነበር።
ሃይማኖታዊ ተጓዦቹ የሚገኙበት ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ዜጎቹ በቁጥር ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ 277 እንደሚደርሱ እና በቤተክርስቲያን የእንግዳ መቀበያ እና በግለሰቦች መኖሪያ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ሙሉውን ለማንበብ፦
@merkatotube @merkatotube_bot
1.3K views01:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 02:25:06
የዋሊያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ተስፋ እና የአሠልጣኙ ዕጣ ፈንታ
---------------------------------------------------------------------------
አርብ መጋቢት 15/2015 በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ጊኒ ከኢትዮጵያ ምሽት 5 ሰዓት ሲጫወቱ ለማየት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ቁጭ ብለው ጠበቁ።
ነገር ግን ውጤቱ ብዙዎችን ተስፋ ያስቆረጠ፤ አንገት ያስደፋ ነበር።
የዋሊያዎቹ የኋላ መስመር መፈረካከስ የተመቸው የጊኒ ካማኖ በ39ኛው ደቂቃ የመጀመሪያዋን ጎል አስቆጠረ።
ከእረፍት በኋላ አዲስ ነገር እናያለን ብሎ የጠበቀው ደጋፊ ተስፋ በ73ኛው ደቂቃ መነመነ፤ የጊኒው ባዮ ከሲላ የተሻገረችለትን ኳስ ከመረብ አገናኝቶ ጨዋታው 2 ለምንም እንዲጠናቀቅ ሆነ።
ሰኞ መጋቢት 18/2015 ምሽት 4 ሰዓት ኢትዮጵያ ከጊኒ የምድቡ አራተኛ ጨዋታ።
በዚህኛው ጨዋታ ዋሊያዎቹ ኳስን እንደልብ እያንሸራሸሩ መጫወት ቢጀምሩም ጊኒ በአምበሏ ናቢ ኬይታ አማካይነት በ4ኛው ደቂቃ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጠረች።
በጨዋታው ምርጥ ብቃት ካሳዩ ሦስት ተጫዎች መካከል አንዱ የነበረው ከነዓን ማርክነህ ከቸርነት ጉግሳ ያገኛትን ኳስ ከመረብ በማገናኘት ዋሊያዎቹ በአስደናቂ የቡድን ጎል አቻ እንዲሆኑ አስቻለ።
ከስምንት ደቂቃ በኋላ ጊኒዎች በሞሪባ ካሩማ አማካይነት ሁለተኛ ጎል በመድገም የኢትዮጵያን የማለፍ ተስፋ አመነመኑ።
ጨዋታው በጊኒ 3-2 አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ኢትዮጵያም ከምድብ የማለፍ ተስፋዋም ደቀቀ።
ለመሆኑ ዋሊያዎቹ ውጤት እንዲህ የራቃቸው ለምንድን ነው? ጫና የበረታባቸው አሠልጣኝስ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል?
ሙሉውን ለማንበብ፦
@merkatotube @merkatotube_bot
1.2K views23:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 21:25:06
በዩክሬኑ ጦርነት ሩሲያ ከሰራዊቷ ይልቅ ሰላዮቿ የበለጠ ውጤታማ እንደሆኑ ተነገረ
***
በዩክሬኑ ጦርነት ሩሲያ ከጦሯ ይልቅ የደህንነት እና የስለላ አገልግሎቷ የበለጠ ስኬት እንዳስመዘገበ የዩናይትድ ኪንግደም የመከላከያ ምርምር ተቋም አሳወቀ።

የሩሲያ የስለላ ኤጀንሲዎች ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ከአውሮፓውያኑ ሰኔ 2021 ጀምሮ ለወረራው ዝግጅት ያደርጉ እንደነበር ነው የሮያል ዩናይትድ ሰርቪስ ኢንስቲትዩት፣ ሩሲ ያስታወቀው።

የሩሲያው የፌደራል ደኅነነት አገልግሎት (ኤፍኤስቢ) በዩክሬን በተያዙ አካባቢዎች ሕዝብን በፍጥነት መቆጣጠር ችሏል ሲል ሩሲ አክሏል።

የዩክሬን የስለላ ባለስልጣናት፣ የተጠለፉ መረጃዎች እንዲሁም መሬት ላይ የተደረጉ ምርመራዎችም በዚህ ሪፖርት ተካትተዋል።

ተመራማሪዎች እንደሚሉት የሩስያው የስለላ ተቋም የመንግሥትን ኮምፒውተሮች በመፈተሽ የዩክሬን ደጋፊ ግለሰቦችን ለመለየት እንዲሁም ለመያዝና ለመመርመር ጥቅም ላይ አውለዋቸዋል ተብሏል።

በተጨማሪም ሩሲያ የተቆጣጠረቻቸው የዩክሬን ግዛቶችን በመገናኛ ዘርፉ ከዓለም ለማቆራረጥም ይህንን የሚመራ የዲጂታል ጦር ክፍል ተሰማርቶ እንደነበር ነው ሩሲ ያስታወቀው።
@merkatotube @merkatotube_bot
1.2K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 21:00:07
ከተማሪዎች የቤት ሥራ እስከ ፕሬዝዳንቶች ንግግር የሚጽፈው ቻትጂፒቲ
***
ምን ዓይነት መረጃ ይፈልጋሉ? ምን ዓይነት መረጃ ለማግኘት ፈልገው ወደ ኢንተርኔት ደጃፍ ብቅስ ይላሉ?

ከዚህ ቀደም ለጥያቄዎ መልስ ፍለጋ በጉግል መረጃ ማሰሻ ላይ ጽፈው ሰዓታትን አባክነው ከሆነ አሁን ብዙ ነገር ተቀይሯል።

ለጥያቄዎ ፈጣን መረጃ በማቀበል ረገድ ቻትጂፒቲ (ChatGPT ) የትንፋሽዎ ያህል ቅርብ ነው።

ከዚህ በፊት በጉግል የመረጃ ማሰሻ ፈልገው ይማሩት የነበረውን በማሻሻል፣ ክህሎት የሚጠይቀውን ጉዳይ በአጭር ጥያቄ መዳፍዎ ላይ ያስገባል።

ሚሊዮኖች መልዕክቶቻቸውን ለማርቀቅ፣ የዘፈን ግጥሞችን፣ አልፎ ተርፎም የኮምፒውተር ኮዶችን ለመቀመር ይጠቀሙበታል።

ይህ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) ለሰፊው ተጠቃሚ ክፍት የሆነው ባለፈው ኅዳር ወር ላይ ነው።

ዝናው ግን የዕድሜውን ያህል አጭር አይደለም።

በኅዳር 2015 ዓ.ም. 2022 ወደ ሥራ የገባው ቻትጂፒቲ (ChatGPT ) በአንድ ሳምንት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን አግኝቶ እንደነበር የድርጅቱ ባለቤት ኦፕን ኤአይ በወቅቱ ገልጿል።

ጉግል እና ማይክሮሶፍት ይህንን አርተፊሻል ኢንተለጀንስ አበልጽገው አገልግሎት ላይ ለማዋል እየተጣደፉ ነው።

ማይክሮሶፍት ብቻ በቢሊዮኖች ዶላር መድቦ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው። ይህ የወቅቱ የዓለማችን አነጋጋሪ እና አወዛጋቢ ስለሆነው አዲስ ቴክኖሎጂ ያጠናቀርነውን ሙሉውን ጽሁፍ እዚህ ያንብቡ
@merkatotube @merkatotube_bot
1.2K views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 20:50:05
በትግራይ ውስጥ የተካሄደው ጦርነትን ተከትሎ በተለያዩ በወንጀል ተጠርጥረው ተከሰው የነበሩ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች ክሳቸው እንዲነሳ መወሰኑን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ።
@merkatotube @merkatotube_bot
1.1K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 20:25:05
በምዕራብ ኦሮሚያ የምሥራቅ ወለጋ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው የነቀምቴ ከተማ የገዢው የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ።
@merkatotube @merkatotube_bot
1.1K views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ