Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ ሰዎች…! '…አዎ አንዳንድ ሰዎች በብዙ እርዳታ ጠያቂዎች ተወጠርን እኮ። ለየትኛው እንሁ | መረጃ ቲቪ🇪🇹

አንዳንድ ሰዎች…!

"…አዎ አንዳንድ ሰዎች በብዙ እርዳታ ጠያቂዎች ተወጠርን እኮ። ለየትኛው እንሁን? አሁንስ ግራገባን ስትሉ እሰማለሁ።

"…የእኔ መልስ ለለመናችሁ ሁሉ ስጡ። የምትሰጡት ከሰጣችሁ መልሳችሁ ስጡ። እኛ ለማኞቹ ለእናንተ ለሰጪዎቹ የልመና ፕሮጀክታችንን ቀርጸን አቅርበናል። ሁሉም ለማኝ የሚለምነው ጎደለኝ ብሎ ነው። የጎደለውን ዓይታችሁ ባቀረበው ፕሮጀክት መሠረት ካላችሁ መስጠት የእናንተ ፈንታ ነው።

"…ስለ ዓይነ ብርሃን የሚል ዓይነ ሥውር፣ እጅ እግር ያጣ የኔቢጤ፣ በሽታ ያደቀቀው ለማኝ ሁላቸውም ለማኝ ናቸው። በዜማ የሚለምን አለ። በባን የሚለምን አለ። ዝም ብሎ ተቀምጦ የሚለምንም አለ። እንደ እኔ መራታም ደግሞ አለ በኪሳችሁ ውስጥ ብር ያስቀመጠ ይመስል ነፍሴ የማትፈልገው 100 ብር ካለህ ወዲህበል የሚል ገገማም አለ። ብቻ ሁሉም ለማኝ ነው።

"…በነገራችን ላይ አጭበርባሪ ከማኝም አለ። ኖራ ተለቅልቆ የቆዳ በሽታ ያዘኝ ብሎ የሚቀፍል ጤነኛ የሆነ አጭበርባሪ ለማኝም አለ። ሳይታወር እውር የሚመስል፣ ሳይሰበር በዊልቸር፣ በክራንች የሚሄድ፣ ልመናን እንጀራው ያደረገም ለማኝ አለ። ሁሉም ለማኝ ቸግሮት ነው ማለት አይቻልም። ደኅና እየኖረው ልመና ሱስ የሆነበትም እንዳለ ነው የምሰማው።

"…ዋናው ነገር ያቀረብነውን የልመና ፕሮጀክት ማየት ነው። የእኔ የልመና ፕሮጀክት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሰብረው እንገባለን ያሉ አህዛቦችን አትገቡም በማለታቸው በመንግሥትና በኦሮሞ ጽንፈኞች ገሚሶቹ ታርደው፣ ገሚሶቹ ተጨፍጭፈው የአልጋ ቁራኛ ለሆኑት የሻሸመኔ ከተማ ባለማዕተብ ክርስቲያኖች ነው።

በማርያም…!
በቅዱስ ሚካአል…!

"…ማርያምን ተጎጂዎቹን አንዳቸውንም አላውቃቸውም። እመቤቴን።