Get Mystery Box with random crypto!

#AmharaEducationBureau በ2015 የትምህርት ዘመን በአማራ ክልልበሚገኙ የመንግስት ት | 43 All University

#AmharaEducationBureau

በ2015 የትምህርት ዘመን በአማራ ክልልበሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ ጭማሪ ማድረግ #እንደማይፈቀድ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

"የተወሰኑ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የመመዝገቢያ ክፍያ ጭማሪ ማድረጋቸውን አረጋግጠናል" ያሉት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ/ር)፤ ተግባሩ ህገ-ወጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ማንኛውም በክልሉ የሚገኝ የመንግስት ትምህርት ቤት ከባለፈው ዓመት የተለየ ምንም አይነት የመመዝገቢያ ክፍያ ጭማሪ ማድረግ ያልተፈቀደለት መሆኑን ኃላፊው አሳስበዋል።

በአማራ ክልል የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 04/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን መገለጹ ይታወሳል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25