Get Mystery Box with random crypto!

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ ግብር ከተቋሙ በከፍተኛ ውጤት ለ | 43 All University

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ ግብር ከተቋሙ በከፍተኛ ውጤት ለተመረቁ 18 ተማሪዎች በ2015 የትምህርት ዘመን ነጻ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል አወዳደሮ መስጠት እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡

የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር የተመረቁና ለወንድ 3.5 እና ከዚያ በላይ፤ ለሴት 3.25 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

በመሆኑም የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉ መስከረም እና ሰኔ/2014 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲው የተመረቃችሁ እስከ አርብ ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች፡-

• ሙሉ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ሁለት ኮፒ
• ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
• የድጋፍ ደብዳቤ
• በተማሪ አደረጃጀቶች አገልግሎት የተሰጠበት የምስክር ወረቀት

የማመልከቻ ቦታ፡- በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

ለፈተና ያለፉ አመልካቾች በውስጥ ማስታወቂያ ከጳጌሜን 01 እስከ 03/2014 ዓ.ም ይገለጻል።

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መስከረም 05/2015 ዓ.ም።

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡- በዩኒቨርሲቲው አምስት ካምፓሶች/ኮሌጆች

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25