Get Mystery Box with random crypto!

ሜርሲ እና ብዕሯ✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ mercy_ena_berua — ሜርሲ እና ብዕሯ✍
የቴሌግራም ቻናል አርማ mercy_ena_berua — ሜርሲ እና ብዕሯ✍
የሰርጥ አድራሻ: @mercy_ena_berua
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.94K
የሰርጥ መግለጫ

ለ ሀሳብ አስተያየት t.me/mercy_bbot @Mercyabay

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-30 07:28:28

ምሳሌ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤
¹⁷ ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
¹⁸ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
¹⁹ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፥ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።

ሰናይ ቀን

@Mercy_ena_berua
252 viewsMercy, edited  04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 20:28:47 'ራማ'

ከዚህ ቀደም ከፃፍኳቸው እና እዚህ ቻናል ላይ በተከታታይ ይለቀቅ ከነበረ ታሪክ ውስጥ አንዱ ነው።
በህንድ ሀገር ላይ ከመቶ ዓመታት በፊት ወንጌልን ሊሰሩ በሄዱ ሚሽነሮች ዙሪያ የሚያትት ታሪክ ነው።እንድታነቡት ግብዣዬ ነው


@Mercy_ena_berua
261 viewsMercy, edited  17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 19:51:35 #ከስሜ_በፊት
ክፍል አምስት

....ማስታወሻውን እንደገለጠች ባህሩ ወደ ውስጥ ገባ።ደንገጥ ብላ ሳያያት ወደ መደርደሪያው በመመለስ የተዝረከረከውን አልጋ ቦታ ቦታውን ማስያዝ ጀመረች።
"ከሰል...ቡና...ዳቦ...ቆሎ...የረሳሁት ነገር አለ መዓዚ?"
ቀና ብላ በፈገግታ እያየችው
"ምንም አልረሳህም ባይሆን ከሰሉን አያይዝልኝ"
* * * *
"ምን ልታደርግ መጣህ?"
"ምን እየተፈጠረ እንደሆነ እንድታስረዳኝ" መኪናው ላይ መስኮቱን ብቻ ከፈት አድርጎ ግራ በመጋባት ያየዋል።
"አማኑ ችግር አለ እንዴ?" ከቤታቸው በር አጠገብ ቆሞ ከሪም ጠየቀው።
"ምንም ችግር የለም...አንተ ግባ እኔ መጣሁ።" ወዲያው አንገቱን ወደ ባለመኪናው በመመለስ እንደመማፀንም እያለ እንዲሄድለት ለመነው።
"ምን እየተካሄደ እንዳለ ልትነግረኝ የማትችል ከሆነ ወርጄ እኔ እራሴ ጠይቃቸዋለሁ።"
"አታደርገውም ብሩክ!" በሩን መልሶ ዘጋበት ከሪም ተሻግሮ እየመጣ ነበር።
"እባክህ ልለምንህ ሁሉንም ነገር ሌላ ጊዜ አስረዳሃለሁ አሁን ግን ከዚህ የማትሄድ ከሆነ ለዘመናት የለፋሁበትን ድካሜን ነው ከንቱ የምታደርገው!"
"አማን"
"ሂድ አልኩህ እኮ!" ጮሀበት።
ከሪም አጠገባቸው ሲደርስ ብሩክ መኪናውን አስነስቶ ሄደ።
በጥርጣሬ እየተመለከተው
"ምንድነው አማኑ?...ማነው እሱ ታውቀዋለህ?"
"በፍፁም!...ቅድም ሆስፒታል እያለን የተዋወቀኝ ሰው ማለቴ የገጨው ልጅ.. እንዴት ሆነ ብሎ እየጠየቀኝ ነበር።" የራሱ ውሸት ለእራሱ ጎርብጦት ፀጉሩን አከክ አከክ እያደረገ ወደ መሬቱ አጎነበሰ።
"ታዲያ ግባ አትለውም ነበር!?"
"የት!?" በድንጋጤ ጠየቀው።
"ለነገሩ የት ይገባል!....በል እንሂድ ምሳ አዘጋጅተው እየጠበቁን ነው።"

* * * *
"ፍጀው አንተ...ለዓመት ይበቃናል ብለን ስናስብ"
ዳንኤል ቀና ብሎ አፍ አፉን እያየ የሚያጉረመርመውን ባህሩን ተመለከተ
"ልስጥህ?" በእጁ የያዘውን ሾርባ ጠጋ አደረገለት።
ባህሩ እጁን ሲዘረገ መዓዛ በያዘችው መቁያ እጁን መታቸው።
"ከታመመ ሰው?" በቁጣ አፈጠጠችበት።"ማነው የታመመው?...አንዲት መኪና ገፋ አደረገውና መንገዴን ልቀቅልኝ አለው እርሱም አጋጣሚውን ተጠቅሞ ከወደቅኩበት አልነሳ አለ።ሆስፒታልም ሄደ...ስብራት የለው ውልቃት የለው።ደህና ነህ ብለውት ወደ ቤቱ ሸኙት።እዚህ ታሪክ ውስጥ ታሟል የሚል ነገር አለበት!?....የለበትም።"
እነርሱ ሲስቁ ከእጁ ነጥቆ ለእራሱ ወሰደው።
"እኔ ምልህ አማኑ በቃ ሳንከሰው ለቀቅከው ማለት ነው?" ከሪም ነበረ
"በቀል የእግዚአብሄር ነው" ዳንኤል ጣልቃ ገባ።
"ሄቼቼቼ....የትኛው በቀል ባክህ!?"
"ከሪም ክፉ አታውራ"
"ይሻልህና ከአንተ ጋር እንጨርሳለን"
"ቢጎዳማ እኔም አለቀውም ነበር"
አማኑኤል ብሩክን እያሰበ መለሰለት።
"ይሄ ነገር ወዴት እየሄደ ነው!?...ምን እየሆንኩ ነው!?" በውስጡ አውርቶ በረጅሙ ተነፈሰ።
መዓዛ ተመልክታው
"አሙ የሆንከው ነገር አለ?" አለችው።
"አይ አይ ምንም አልሆንኩም ቡናውን ቶሎ አደራራሺና የሆነ ሄጄ የምመጣበት ቦታ አለ"

* * * *
"ልጁ እንዴት ሆነ?"
"ደህና ነው ቡራ..."
በመሃል አስተናጋጇ መጣች።ሁለቱም ማኪያቶ አዘው ከሄደች በኋላ ዝም ዝም ተባብለው ቆዩ።
"ተጎሳቁለሃል እራስህን ጥለሃል..እዛ ሆስፒታል ሳይህ እንዴት እንደደነገጥኩ"
"በዓዕምሮሁ ውስጥ እልፍ ጥያቄዎች እንደተፈጠሩብህ አውቃለሁ።ተረጋግተህ ከሰማሀኝ ለሁሉም መልስ ታገኛለህ።"
"ምንድነው ንገረኝ" ብሩክ ለመስማት እየጓጓ ጠረጴዛው ላይ ደገፍ አለ።

ይቀጥላል....

@mercy_ena_berua
260 viewsMercy, edited  16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 20:44:27 #ከስሜ_በፊት

ክፍል አራት

"እየዋሸሀን አይደለም አአ!?"
"መአዚ.."
"ይሀውልህ አማኑ እዚህ ቦታ የምንኖረው በእምነት ነው።የተጣለ ምግብ አንድ ጤነኛ ሰው ቢበላ ወዲያው እራሱን የሚያገኘው ሆስፒታል ውስጥ ነው።እኛ ግን የተበከለ ምግብ ውሃ አንዳች ሊጎዱን አይችሉም።ይሄም እምነታችን ነው።ምን አልባትም ሰውነታችን ለምዶት ይሆናል።ልክ እንደዛውም አንድን ሰው ወደ እኛ ሲመጣ በእምነት እናቀርበዋለን።እንደብቃለን ግን አንዋሽም።አስር ሺ ብርን ያከለ በዓይናችን አይተነው የማናውቀውን ነገር ከመሬት ወድቆ አገኘሁት ስትል እንዴት ልቀበለው?.."
"እምነት ነው አይደል ያኖራችሁ ስለዚህ እመኚኝ!" ብሏት ወደ መሬቱ አጎነበሰ።
"እሽ አመንኩህ"
"እና ከምግብ የዘለለ ነገር ብናስብስ?"
"እንዴት?"
"መኖር ነዋ መዓዚ...ብያንስ አንድ ቤት መከራየት ብንችል..ከዛ የሆኑ ስራዎችን ተፍ ተፍ እያልን የወር ደሞዙን እንከፍላለን።አንቺም ሴት ሆነሽ..."
"ጥሩ ታስባለህ።ይሄን ከአንዴም ብዙ ጊዜ አስበንበታል...አዲስ አበባ ላይ አንድ ቤት ክራይ ስንት እንደሆነ ለአንተ አልነግርህም ከዛም ብሶ የተፈለገውን ቤት ብናገኝ አምኖን የሚያከራየን አይገኝም።እኛም ስማችንን አመነው መሰለኝ ያንን የማድረግ አቅሙም የለንም።"
"ለምን?"
"መጀመሪያ ውስጥህ ነው መበርታት ያለበት...ውስጥህ መፈወስ አለበት...ውስጥህ ካልዳነ አንዲት የወደቀች እቃ እንኳ የማንሳት አቅሙ አይኖርህም።ውስጣችንን የሚያድንልንን ደግሞ አንዳች አላገኘንም።" ከአጠገቡ በመነሰት ወደ ውስጥ ገባች።

* * * *
"የውስጥ ህመማቸው ምን አንደሆነ አላውቅም።ሁሌ ስለሚስቁ እየቀለዱ ስለሚውሉ ስለውስጥ ህመማቸው እንኳን በዓይን ዓይተው ጠይቀዋቸውም መረዳት አይቻልም።አብሬያቸው ጥቂት ቆየሁ።ግን እያወሩ የማያወሩ ውስጣቸው በህመም የተሞላ ድብቆች ናቸው።ከወር በፊት ሳያቸው እንደዚህ አልነበሩም።በጥቂቱም እያገኘኋቸው ይሆን!?"
"ይሄን ፅሁፍ ትከትበዋልህ ለጉድ...እንደው ምን የሚፃፍ እንደምታገኝ ነው ግርም የሚለኝ።ይመሻል ይነጋል።"
አማኑኤል መፃፉን አቁሞ ወደ ከሪም እየተመለከተ:-
"ከዚህ የተሻለ ምን የሚፃፍ ነገር አለ ብለህ ነው?"
"ስለ እኛ ነው እንዴ የምትፅፈው!?" የፍራሹ ጠርዝ ላይ እየተቀመጠ ጠየቀው።
"አይ...አይ....ምን የሚፃፍ ነገር አለና!?" በመደናገጥ መለሰለት
"ንግግርህ እኮ ነው..."
"እኔ ልል የፈለግኩት..."
ባህሩ በሩን በርግዶ ገባ።ትንፋሹ እየተቆራራጠ ይንተባተባል።
ሁለቱም በድንጋጤ ቆሙ
"ዳ....ዳ....ዳኒ....."
"ዳኒ ምን ሆነ!?" ሁለቱም እኩል ጠየቁት።
"መን...መንገድ....መኪና...."
"አንተ በስርአት ተናገር እንጂ....ዳኒ ምን ሆነ?" ከሪም በቁጣ ጠየቀው።
"መኪና ገጭቶት ሆስፒታል..." የተቀረውን አልሰሙትም ሁለቱም እየሮጡ ወጡ ባህሩም ተከተላቸው።
* * * *
"አቦ ትንሽ ነው ገፋ ያደረገኝ...የኔ ጌታ የት ሄዶ"
"ዝጋ አንተ!....ግራና ቀኙን እያየህ ተሻገር ብዬ ስንቴ ነው የነገርኩህ!" ከሪም ከእንባው ጋር እየታገለ መለሰለት።
"እኮ አንተ መች መች ባክህ!?"
አማኑ ከሪምን ጎሸም አድርጎት
"ብዙ አታውራው በቅጡ እንኳ አላገገመም እኮ።"
"ባክህ እንዳለውም ገፋ ነው ያደረገው ጭረት እንኳ የለበትም እኮ።መኪናው አጠገቡ ከመድረሱ ነው አሉ እራሱን የሳተው።" አራቱም ተሳሳቁ።
"ባይሆን መዓዚና እኔ ሄደን የሚያስፈልገውን ነገር ቤት እናዘጋጃለን ዛሬ ይወጣል ብለዋል።"
* * * *
መዓዛ ሳይዘጋ ክፍቱን ትተውት በሄዱት በር ዘልቃ ገባች።ቤቱ ሲወጡ እንደነበረው ነው።
"ለነገሩ ምን ይሰርቃሉ?" ብላ ለእራሷ ፈገግ አለች።በእጇ የያዘችውን ፌስታል ካስቀመጠች በኋላ ወደ ተመሰቃቀለው ፍራሽ በመሄድ ልታነጥፍ ብልድልብሱን አነሳች።የወደቀውን ነገር ለማየት ዝቅ አለች።አማኑኤል እየፃፈ እዛው ጥሎት የሄደው ማስታወሻው ነበር።ብልድልብሱን ወደ ቦታው መልሳ ማስተወሻውን ከመሬቱ አነሳች።ስታንገራግር ከቆየች በኋላ ገለጠችው።

ይቀጥላል....

@Mercy_ena_berua
307 viewsMercy, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 19:19:49 ለየትኛው ጥበብ እጅ ሰጥተሃል...ለየትኛው ህይወት አልሸነፍ ብለሃል...አይገርምህም ወይስ ይገርምሃል...ነቅተህ ወይስ ፈዘህ...በፍቅር ወይስ በትዳር...በፍቺ ወይስ በአብሮነት...በየትኛው ነህ

??

በሃብቱ ወይስ በማጣቱ
በመማር ወይስ በስራው
ትልቅ በመሆን ወይስ ወደ ትንሽነት

??

ተፈትነህ አልፈህበት ወይስ ወድቀህበት
አሸንፈህ ወይስ ተሸንፈህ
በማውራት ወይስ በመኖር
በመሳቅ ወይስ በማልቀስ

??

እያነባህ ወይስ በሳቅ እንባ
አሞህ ወይስ በመፈወስ መንገድ
ብድር ወይስ ልግስና

??

ወደ መጀመረያው ወይስ በመጨረሻው
ውሸታም ነህ ወይስ ሀቀኛ
እዩኝ ባይ ወይስ እራስ ከላይ
በእምንተ ወይስ በማየት
በመጀመር ወይስ በመጨረስ
??

ልጅ ነህ ወይስ ወጣት
ዕድሜ ገፍቶህ ወይስ አንተ እየገፋሀው
ቆመህበት ወይስ እራሱ አምልጦህ
በመጀመርያው ወይስ በማለቂያው

??

አንተ የሌለህበት ላይ እኔ አለሁኝ እኔ ባለሁበት ላይ ሌላዋ የለችበትም።
ግና ሁላችንም አንድ ታሪክ አለን።

ው ል ደ ት ና ሞ ት

የተወለድንበትን እንነግራቸዋለን ፍፃሜያችንን ይነግሯቸዋል።

የሚነገር ካለን!

ሰናይ ምሽት

@Mercy_ena_berua
271 viewsMercy, edited  16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 22:01:10 Share 'የመውጊያው በትር-ሜርሲ.doc'

ከዚህ ቀደም ቻናሉን የጀመርኩ ሰሞን የፃፍኳት አጭር ልብወለድ ናት ለንባብ እንዲመቻችሁ ነው በ pdf መልክ ያዘጋጀሁላችሁ።
ያላነበባችሁት እንድታነቡት ግብዣዬ ነው።

ሰናይ ጊዜ

@Mercy_ena_berua
318 viewsMercy, 19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 20:57:50 #ከስሜ_በፊት

ክፍል ሶስት(ሜርሲ )

ከእንቅልፉ የባነነበትን ምክንያት ባያውቀውም ነቅቷል።ብልድልብሱን ገለጥ አደረግ።ከእንቅልፉ ለመባነኑ ሶስት ምክንያቶችን አስቀመጠ።
የዝናቡና የመብረቁ ድምፅ...የዳንኤል የማለዳ የፀሎት ድምፅ...ሶስተኛው ደግሞ ጨለማው ለንጋቱ እጁን እየሰጠ መሆኑ ነበር።
አተኛኘታቸውን አይቶ ፈገግ አለ።ከጎኑ ፀላዩ ዳንኤል ተንበርክኮ ስለነበር እየፀለየ የነበረው ብልድልብሱ ወደ እሱ በብዛት ተሰብስቦ ከእግራቸው በኩል የተኙትን ለብርድ አጋልጧቸው ነበር።የተለመደው ጭቅጭቅ ከሪም ከእንቅልፉ እንደተነሳ ተጀመረ።ከሪም ዓይኖቹን ሲገልጥ እንደነገሩ እንደነገሩ ተደርጎ ከተሰራው የቆርቆሮ በር በኩል የሚገባው ብረድ ጆሮ ግንዱን ሲለው በብሽቀት ተነሳ።እስከ እግሩ ብቻ ነበር ብልድልብሱ።
እጁ ላይ የገባለትን ማማሰያ ከባዶ ድስጡ ጋር ማላተም ጀመረ።ያኔ አማኑኤል በሙሉ ልቡ ነቃ።ባህሩ እና መዓዛም ዓይናቸውን እያሹ ቀና አሉ።ከሪም ያሰበው አልተሳካለትም።ዳንኤል ብልድልብሱን እንደተጠቀለለው ተንበርክኮ ድምፁን ከዝናቡ በላይ ከፍ አድርጎ ያሳርጋል።
"አቦ የምትለምነው ባልሰማ ይለፍህ!"
ዳንኤል ፀሎቱን አቁሞ ከተንበረከከበት ቀና ብሎ አየው።
በዛች ቅፅበት ከሪም ብልድልብሱን ወደ እራሱ በመሰብሰብ ተጠቀለለበት።
"ምን አለበት መፀለይ ባትችሉ እንኳ 'አሜን 'በማለት ብትተባበሩኝ።"
"እኔም እፀልያለሁ እኮ ግን በልቤ ለልቤ አምላክ እፀልያለሁ።" ይሄን ብሎት ባህሩ እየተነጫነጨ ከሪምን ተከተለው።
መዓዛና አማኑኤል በሁኔታቸው እየተሳሳቁ ይመለከቷቸዋል።
ባህሩ ከብልድልብሱ አንገቱን በማውጣት ወደ መዓዛ እየተቅለሰለሰ እያያት
"መዓዚዬ ዝናቡን እንደምታይው ነው በዚህ ሰዓት ተፍ ተፍ ማለት አንችልም።አንቺ ከጥበቡ አትጎይምና ያለችዋን ሰራርተሽ"
መዓዛ ብቻዋን ከተኛችበት ፈገግ እያለች ተነሳች።ዳንኤል ወደ ፀሎቱ ተመለሰ።

* * * *

አማኑኤል ከተወጠረችው ሸራ ቤት ፅሁፉን ፅፎ እንደጨረሰ ከሁሉም ዘግይቶ ነበር የወጣው።ዝናቡ አብቅቶ ፀሃይ ለመውጣት ከደመናው ጋር ግብ ግብ ላይ ነበረች።ስትወጣ ደመናው ሲጋርዳት።ከሪም ከግንቡ አጥር ጥግ ቁጭ ብሎ በፈገግታ ይከታተላቸዋል።አማኑኤል እየተጠዳፈ ሄዶ ከአፉ ሳያደርሰው ሃይላንዱን መንትፎ ከመሬት ወረወረው።ከሪም በድንጋጤም በንዴትም ዓይኖቹ ቀሉ።
"ባንዳ!" ብሎ ከመሬቱ እምር ብሎ ተነሳ።አማኑኤል እርሱ በተነሳበት ድንጋይ በመቀመጥ ተቁነጠነጠ።
"ለምንድነው የምትፈታተነኝ!?"
"አንተ ነህ እየተፈታተንከኝ ያለሀው ከሪም።የሲጋራው ሳያንስህ እንደገና...ይሄ እኮ ለመኪና ነዳጅነት ተብሎ የተሰራ እንጂ ለሰው አይለም!"
"ማነው ሰው ያደረገኝ!?..."
"ከሪም..."
"አቦ አማኑ ተወኝ።ሰዉ በዚህ ሰዓት ለሰውነቱ ሙቀት የሚሰጠውን የእለት ምግቡን ተመግቦ ወይ ወደ ሞቀው አልጋው ተመልሷል ወይ ደግሞ ወደ እየለት ክንዉኑ።እና እኔና መሰሎቼ ከየትኛው የሰው ሀረግ ተመዘን ይሆን ሰው ለመባል የበቃነው!?"
አማኑኤል ከተቀመጠበት ቦታ በመነሳት ወደ ውስጥ ገባ ሰከንዳት ሳይፈጅበት ተመልሶ በመውጣት ከበሩ በመቆም
"ና የምንሄድበት ስፍራ አለ"
ከሪም እያንገራገረ ተከተለው።

* * * *
"ስሜቴን መቆጣጠር እችል ነበር።ግን ሰውን ያከለ ፋጡር ሰው አለመሆኑን አምኖ ቤንዚል ሲጠጣ...ሰው አለመሆኑን ሲናገር ምንም አቅም አልነበረኝም።ሰውነት ለብሻለሁ እኮ!...ምግቡን ለመግዛት ገንዘብ ከወዴት እንዳመጣሁ ሲጠይቁኝ ተጥሎ አግኝቼ ከማለት ውጭ ሌላ ምላሽ አልነበረኝም።እንዳመኑኝ ተስፋ አደርጋለሁ።"
ቀና ሲል ትሪውን ዘርግቶ አጥንቱን ከሚግጠው ባህሩ ጋር ዓይን ለዓይን ተጋጩ።ባህሩ በፈገግታ ተመለከተው።
ካገኛቸው ጊዜ ጀምሮ ይሄን ፈገግታ አይቶት አያውቀውም ጥቂት ነገር ያስደስታቸዋል እልፍ ችግር አያንበረክካቸውም።
ማስታወሻውን ከመደርደሪያው አድርጎ ወደ ባህሩ በመሄድ አጠገቡ ተቀመጠ።
መዓዛ ጥጉን ይዛ ቡናውን ትወቅጣለች።
"ዳኒ እና ከሪም ወዴት ሄደው ነው?"
"መዓዚ ለቡና ቁርስ የሚሆን ነገር እንዲገዙ ልካቸው ነው።ዕድሜ ለአንተ እና ለዛ ባለ ጨላ...ለመግዛትም በቃን እኮ።"
ይሄን እንዳለ ከሪም ዳንኤልን አስከትሎ ገባ።
"እንዴ በቆሎ!?" ባህሩ ከተቀመጠበት ሊነሳ ቃጣው።
"አንተ አርፈህ አጥንቱን ጋጥ!" ከሪም እጁን በማስጠንቀቂያነት እየጠቆመበት ከመዓዛ እግር ሥር ባማስቀመጥ ከአጠገባቸው ተቀመጠ።
ዳንኤል ከፍራሹ እየተቀመጠ
"አያችሁ የፀሎት መልሴን..."
"የታል...የታል በክህ¡?" ከሪም እያላገጠ ወደ ግራ እና ቀኝ የጠፋን ነገር እንደሚፈልግ ሰው አማተረ።
"የበላሀው ምኑን ሆነና!?"
"የበላሁት የአንዱን ቱጃር ገንዘብ!"
"አማኑን ወደ እዛ የወሰደው ማን ሆነና!?"
"እግሩ ከአጋጣሚ ጋር ተባብረው"
ክርክራቸው እየጦፈ ሄደ
"በዚህ ምድር ላይ አጋጣሚ የሚባል ነገር የለም።"
"እርሱን ለፈላስፎቹ!" አለው ከሪም በተሰላቸ ድምፅ።
"ፈላስፋዎቹማ ከአንተ ጋር ይወግናሉ።"
"እናንተን ነው ያልኩህ"
"እኛ ፈላስፋ አይደለንም አማኞች ነን!"
"አማኝ!?...የሌለን ነገር በማኖር ማመን¡?"
"እርሱ በአንተ ልብ ውስጥ ነው የሌለው"
"ሄይ...ሄይ...ክርክራችሁን ተዉትና በቆሎውን ፈልፍሉት!" መዓዛ ነበረች።
ሁለቱም ረገቡ...አማኑኤል ግን እንዲቀጥሉት ልቡ ፈልጎት ነበር። ከተቀላቀላቸው ወር አልሞላውም ግን እርሱ በአመታት ውስጥ ፈልጎ ያላገኛቸው ነገሮች አሁን ፈልገውት ወደ እርሱ እየጎረፉለት ነው።እጁን እስኪያመው ድርስ የሚከትባቸው ነገሮች በርክተውለታል።



ይቀጥላል....

@Mercy_ena_berua
@Mercy_ena_berua
309 viewsedited  17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 18:16:30
Join &share
@Mercy_ena_berua
@Mercy_ena_berua
256 viewsedited  15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 14:44:09 ሰላማችሁ የበዛ ይሁን።ተቋርጦ የነበረው "ከስሜ በፊት" የተሰኘው ልብወለድ ዛሬ ይቀጥላል።
ልብወለድ ማለት ከመሬት ተነስተን የምንፅፈው የፈጠራ ታሪክ አይደለም።ከምናየው ከምንሰማው አከባቢያችን ላይ ከታዘብናቸው ነገሮች...ከእነዚህ የተቀዳ ነው...እንደዛ ካልሆነ ተረት ሊሆን በተገባው ነበር።በተለይ መንፈሳዊ ሲሆን እግዚአብሄር አልፎ በዛ ይናገራል የሚል እምነት አለኝ።ስላየሁትም ነው።መንፈሳዊ ፅሁፎች መፃፍ የምትሞክሩ ልጆች ዛሬም ቢሆን ላበረታታችሁ እፈልጋለሁ።ማንነታችሁን ድካማችሁን ከፅሁፋችሁ ጋር አታገናኙት ውስጣችሁን እያዳመጣችሁ ፃፉ።ምልከታችሁን በፅሁፋችሁ አውሩ።ይሄ የእናንተ መክሊት ከሆነ ልታተርፉበት ዛሬ ላይ እንድትነሱ አበረታታችኋለሁ።

ሰናይ ጊዜ ይሁንላችሁ

ሜርሲ እና ብዕሯ
ለ ሀሳብ አስተያየት t.me/mercy_bbot @Mercyabay

https://t.me/Mercy_ena_berua
277 viewsedited  11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 22:34:08 ትንሽ እያለሁ በዓዕምሮዬ ውስጥ የተቀረፁ ብዙ መልካም ነገሮች አሉ።በጊዜው ደስታን የማይሰጡኝ በመፈጠራቸው በእኔ ላይ በመሆናቸው የተጠላሁ የመሰለኝ።በልጅነቴ እጅግ አስፈላጊዎቼ ነበሩ።ስለ እነዛ ነገር ብቻ ለመቀበል እፀልይ አብዝቼም እጨነቅ ነበር።ከእኔ በዕድሜ የሚበልጡትን ለማናገር ስለጭንቀቴ ላወራቸው ወድጄ ላማክራቸው ስቀርብ እነርሱ ዛሬዬ ላይ ስለሚመጣው የፈተና ክብደት ነገሩኝ እንጂ ስለልጅነቴ ፈተና ሊገባቸው አልቻለም።ያኔ የዛሬው አስተሳሰብ ብስለት አልነበረኝ በዕድሜዬ ልክ አስተሳሰቤም የተገደበ ነበር።ዛሬ ቢሆንማ እኔም እንደነሱ ባቀለልኩትና ፈተናዬ ላይ በሳቅኩ ነበር።ግን ልጅ ነበርኩ የማስበው እንደልጅ ነበር።ልጅ ሆኜ በሰራሁት ስህተት በወደቅኩባት ኢምንቷ ምክንያት ዛሬ ላይ ብዙ ዋጋ እከፍላለሁ።አድጌም ከትላንት የባሰ ፈተና ገጠመኝ እንጂ የልጅነት ፈተናዬ አልተደገመልኝም።አይኖቼን ጨፍኜ በከፈትኩ ቁጥር ከፈተናዬ ጋር እጋፈጣለሁ።የትላንት ፍርሃት አለብኝና ፈጣሪ የነገን አስተሳሰብ ቢሰጠኝ ብዬ እመኛለሁ።ግን ትላንት ዛሬ ዛሬም ነገዬን መጥራት አይችልም።በዛሬው ልክ ነው ጥበብም ማስተዋልም የሚሰጠኝ።ክፉ የምላቸው የህይወት ገጠመኞቼ ውድቀቶቼ ነገ በሚባል ቀን ላይ ለእርሱ ማትረፊየው ይሆናል።እኔ ባሰብኩት እና በነደፍኩት መንገድ ቢሄድ እዚህ አይደለሁም።ሩቅ ሄጃለሁ።በእኔ ንድፍ ሁሉም ከንቱ ሆኗል።ያቺ ሴት የለችም ወይም ሌላ ሴት ያቺን ሴት እየኖረቻት ነው።
ስለ እራሴ እየፃፍኩ አይደለም ስለ አንቺ አንተ ለእናንተም ነው የምከትበው።የሰው ልጅ የተለየ መከራ ፈተና አይፈተንም።ከሰው ነውና።አንዳችን የወደቅንበት ላይ አንዳችን ደግሞ ተነስተንበታል...ሌላው ደግሞ ወድቆ ላይነሳ ሆኗል...የፈተናው አመጣጥ ይለያይ እንጂ የምናስተናግድበት መንገድ ብለያይም...ልዩ ፈተና ግን አልተፈተንም።
ከላይ ከጠቀስኩላችሁ አንድ ፈተና አንስቶ እልፍ ፈተናዎችን ተፈትነናል..እየተፈተንም ነው...ወደ ፊትም ፈተናችን ይቀጥላል።
ፈተናችን ግን ከማ ለማ እና ለምን የሚሉ መልሶችን ሊያገኝ ይገባል።ለዚህ ሁሉ ምን እናድርግ?..
"....እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ!" ክርስቶስ ነበር ያለን።ልጅ ሆነን ትልቅም ሆነን አርጅተንም በሁሉም መልኩ እንደየደረጃችን ትልቅነቱ ሳይዘው ሊረዳን ሁሌም ከእኛ ጋር አለ።

ሰናይ ምሽት

@Mercy_ena_berua
315 viewsedited  19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ