Get Mystery Box with random crypto!

የፀሎት ጊዜያችን (ከ Kaltube የተወሰደ) የግል የፀሎት ጊዜያችን ሳይስተጓጎል በቋሚነት ሲቀጥ | ሜርሲ እና ብዕሯ✍

የፀሎት ጊዜያችን
(ከ Kaltube የተወሰደ)

የግል የፀሎት ጊዜያችን ሳይስተጓጎል በቋሚነት ሲቀጥል መቼም ድንቅ ነገር ነው አንዳንድ ጊዜ ግን ጊዜውን መጠበቃችን ብቻ ሳይሆን ጊዜውን መዋጀታችንንም እርግጠኞች መሆን አለብን! (የፀሎታችንን ማለቴ ነው)

የፀሎት ጊዜን ስናስብ quantity ጥሩ ሆኖ ሳለ quality ግን አብልጦ አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ

Quality ደግሞ ልብ ይጠይቃል! በአካል ብቻ ሳይሆን በሁለንተና present መሆንን ይጠይቃል ! ፀጋው ዙፋን ስር መጥቶ አካል ብቻውን ቢደፋ ልብ ግን ክንፍ አውጥቶ ከጠፋ የፀሎት ሰዓት አልተዋጀም! አፍ ብቻ የባጥ የቆጡን ከሚያነበንብ ልባችን ከውስጠቱ ቢቃትት ነፍሳችን ገስግሳ ከአምላኳ ጋር ንክኪ ብታደርግ ፀሎታችን በርግጥ ውጤታማና effective መሆኑን እኛው ራሳችን ይታወቀናል!

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሌላው የፀሎት ጊዜን የሚዋጅልን ትልቁ ቁምነገር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለን ወዳጅነት ነው! ምን መፀለይ (ፀ- ጠበቅ ብሎ) እንዳለበት የትኛው ጉዳይ ቀዳሚና አንገብጋቢ እንደሆነ መንፈሳዊው ዓለም ላይ ያለውን traffic ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ጥንቅቅ አርጎ ስለሚያውቀው እሱ ራሱ እየመራንና ለመንፈሳችን መለኮታዊ ጉዳዮችን እያቀበለን ስንፀልይ ፀሎት አቀበት አይሆንብንም! የማያታክት የማይሰለች enjoyable experience ይሆንልናል!

ለአንዳንዶቻችን ደግሞ ስለፀሎት ያለንም መረዳት ምናልባት መቀየር ይኖርበት ይሆናል! አንዳንዴ ፀሎት ሳናውቀው የማጉረምረሚያ ቦታ የማማረሪያ አልፎ አልፎም የጭቅጭቅ ቦታ ወይ ደግሞ ማመልከቻ አስገብቶ ስሞታ አሰምቶ መሄጃም ቦታ ሆኖብን
ከሆነ የፀሎት ጊዜያችንን መልሶ ለመዋጀት መንቃት ያስፈልገናል!

"ህብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው" 1ኛ ዮሐ 1:3 እንዲል ህያው ቃሉ ፀሎት በዋነኛነት አማኝ ከአምላኩ ጋር የቅርበት ህብረትና ግንኙነት የሚያደርግበት የወዳጅነት ጊዜና ቦታ ነው መሆን ያለበት!! ነፍስ አምላኳን ተጠምታ በወዳጅዋ ስር እርፍ ለማለት ናፍቃ የምትሄድበት! የአዳኝዋን ብሩህ ፊት አይታ የምትፅናናበት ፍቅር ሰጥታ ፍቅር የምትቀበልበት ቦታ!!

ከፍቶን ለምቦጫችንን ጥለን ሄደን እንኳን "ጌታ ሆይ እወድሃለሁ" ማለት ስንችል ብዙ ነገር ልባችንን አክብዶት መጥተን ስለነገሩ እንኳ በቅጡ ሳናወራ ቶሎ ሚመጣልን "አንተ እኮ ልዩ ነህ" "ስለኔ ደግሞ ታስባለህ! በኔ ላይ ያለህ ዓላማህ መልካም ነው! አምንሃለሁ! እደገፍሃለሁ እጠብቅሃለሁ! ማለት ስንችል በርግጥ ወዳጅነት መስርተናል! ህብረትም ሰምሮልናል!

ጌታ የፀሎት ጊዜያችንን የተዋጀ ያድርግልን!!

ተፃፈ በላሊ
06/28/22
ዶ/ር ላሊ -

@Mercy_ena_berua