Get Mystery Box with random crypto!

#ከስሜ_በፊት ክፍል ሰባት አማኑኤል የመሄድ ሃሳቡን ትቶ የእያንዳንዱን ህይወት ለማጥናት አብሯቸው | ሜርሲ እና ብዕሯ✍

#ከስሜ_በፊት
ክፍል ሰባት

አማኑኤል የመሄድ ሃሳቡን ትቶ የእያንዳንዱን ህይወት ለማጥናት አብሯቸው ቆየ።አራቱም ያለምንም ጥርጣሬ አብረውት ይጓዙ ነበር።የእያንዳንዱ ህመም እየገባው ስሄድ የሚፅፈውም እየጨመረ አስተሳሰቡም እየተለወጠ ሄደ።ጓደኛው ብሩክ በዳንኤል ጥየቃ ሰበብ አንዳንዴ አብሯቸው ያሳልፍ ነበር።ዳንኤል መሉ ለሙሉ መንቀሳቀስ ሲጀምር ሌላ መምጫ ሰበብ ስላጣ አቤልን የሚያገኘው ብቻውን ሆነ።
* * * *
አማኑኤል ውጭ ላይ ቁጭ ብሎ በያዘው እንጨት መሬቱን እየቆፈረ በሃሳብ ሄዷል።ዳንኤል ከአጠገቡ ሄዶ በመቀመጥ አተኩሮ እያየው
"አማኑ ሰሞኑን ሃሳብ አብዝተሃል በሰላም ነው?"
አማኑኤል ቀና ብሎ ተመለከተውና በእጁ የያዘውን እንጨት ከመሬቱ እያሽከረከረ።
"ደህና ነኝ ዳኒ።የእናንተ ጉዳይ እያሳሰበኝ።"
"አንተ ደግሞ እኛ ምን እንሆንና ለእኛ የተፃፈልንን እኛው እንኖራለን።ባይሆን አባትህን ልታገኘው ከጫፍ እንደደረስክ መዓዚ ስትናገር ሰማሁ።ያኔ ስትመጣ በጣም ተረብሸህ ነበር የሃብታም ልጅ እንደሆንክ ያወኩት ወዲያው ነበር።"
አማኑኤልን ሁሉንም ነገር የደረሰበት ስለመሰለው ውስጡ ተረበሸ።
"ማለት....እንዴት አወቅክብኝ!?" ፈራ ተባ እያለ ጠየቀው።
"ድርጊትህ ይገልጥህ ነበር።አንተ ስትናገር ደግሞ አረጋገጥኩ።ባይሆን ፍፁም ሊገባኝ ያልቻለው እኛ ጋር ሆነህ ልትፈልገው መሻትህ ነው።"
"እርሱን አንድ ቀን እነግራችኋለሁ ብዬ አልነበር..."
"እኮ መች!?"
"አባቴን ሳገኘው።" ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ ውስጥ ገባ።
* * * *
"እናትህ ደውለውልኝ ነበር"
አማኑኤል አፉ ላይ የነበረው ውሃ ትን ብሎት ከአፏ መለሰው። ብሩክ ተደናግጦ ከወንበሩ ተነስቶ አጠገቡ ደረሰ።አማኑኤል ጣቶቹን እያነሳ ደህንነቱን አረጋገጠለት።ዳዊት እየተነጫነጨ ወደ ቦታው ተመለሰ።
"ምን....ምን አለችህ?" መለስ ሲልለት ጠየቀው።
"ደህንነትህን ነው የጠየቀችኝ ደግሞ ስልክህ ብዙ ጊዜ ሞክራልህ አይሰራም።'ደውልልኝ' ብላሃለች::"
"ሌላ የነገርካት ነገር አለ!?" በስጋት ጠየቀው።
"አይዞህ ጓደኛዬ ስለምንም ነገር አልነገርኳትም።ለመዝናናት እንደመጣህ ነው የምታውቀው።እስከመቼ ነው ግን በውሸትህ የምትገፋበት?"
"አልዋሸሁም እኮ ቡራ።መልካምን ነገር ነው እያደረግኩ ያለሁት"
"አንተ አበዛሀዋ...በቀላል መንገድ እየተቻለ።አሜርካን ካከለች ሃገር መጥተህ እዚህ ያውም ጎዳና ላይ..."
"ቡራ በቃህ....ድሎት ያለው አልጋዬ ላይ አንድም ቀን በሰላም ተኝቼ አላውቅም።ይሀው ወር ሞላኝ ሰላማዊ እንቂልፍ እየተኛሁ።"
"ካልክ እሺ....እና መች ልትነግራቸው አሰብክ?"
"ከሰሞኑ...አንተ ያልኩህን ስራ አፋጥንልኝ!"

* * * *
አምስቱም ከፍራሹ ላይ ተሰይመው ምግቡን አሰፍስፈው ይጠብቃሉ።መዓዛ ትሪውን መሃከላቸው ላይ እንዳስቀመጠች ባህሩ አፏጨ።አጁን ሊሰድ ሲል መዓዛ በያዘችው ማማሰያ ቀደመችው።ሁሉም ወደ ዳንኤል ዞሩ።
"እኔ ልፀልይ?" ጆሯቸውን ባለማመን ዞረው ተመለከቱት።አማኑኤል ፈገግ ብሎ
"አታፈጡብኝ እንፀልይ...ጌታ አምላክ ሆይ ስለሰጠሀን ስለዚህ ምግብ እናመሰግንሃለን።ስለ ሰጠሀኝ ስለነዚህ ድንቅ ቤተሰቦችም ስምህ ብሩክ ይሁን።
ሁሌም አብረሀን ስላለህ እናመሰግንሃለን።አሜን።"
ዳንኤል ረዘም አድርጎ"አሜንን" አለ።ሌሎቹ ግን አይናቸውን ገልጠው እያዩት ነበር።
"አሁን መብላት ትችላለህ" ባህሩ ግን ፈዞ ነበር።አማኑኤል ፈገግ ብሎ ምግቡን ጠቅልሎ ሲያጎርሰው ነቃ አለ።
እየበሉ በዝምታ ይመለከቱታል።ዳንኤል ብቻውን ይፍለቀለቃል።ከሪም ውስጡ እያረረ:-
"አንተ ነህ አአ የከተብከው?...አንደዛ ባይሆን አትፍነከነክም ነበር።"
"መፀለይ የሃይማኖት መገለጫ አይደለም።እኔ ሁሌም እፀልያለሁ ግን በውስጤ ነው የምፀልየው።"
አለ አማኑኤል በሁለቱ በኩል የሚነሳውን ንትርክ ቀድሞ ለማርገብ።
"አፀላለይህ ግን የእነርሱን ይመስላል።" አለ በአፍንጫው ወደ ዳንኤል እየጠቆመ።
"ደግሞ የአፀላየይም ልዩነት አመጣችሁ።አቦ የማይናገረውን እንብላና የቡና ሰዓቱ ላይ ንትርካችሁን ትቀጥላላችሁ::" ባህሩ በብስጭት ተናገረ።
ተሳስቀው እየተሻሙ መመገብ ጀመሩ።
* * * *
አባቱ ከፊቱ እየቀደመ ሲራመደ አማኑኤል ባባዶ እግሩ ሆኖ ከኋላው ይከተለዋል።
"አባዬ ጠብቀኝ እንጂ!"
አባቱ ፍጥነቱን ጨምሮ ይራመዳል።አማኑኤል እርምጃው ወደ ሩጫ ተቀየረ።አባቱ ግን እጅግ እያራቀው ነበር።አማኑኤል እያለከለከ ጉልበቱን ይዞ ቆመ።
ዝቅ እንዳለ
"አ...ባ...ዬ...እ...ባ...ክ...ህ...ጠ...ብ...ቀ...ኝ"
"አጠገብህ ነኝ እኮ" አማኑኤል ቀና ሲል አባቱ አልነበረም።
"አ....ባ....ዬ"በድንጋጤ ከእንቅልፉ እየጮሀ ተነሳ።ሁሉም ከተኙበት ተደናግጠው ተነሱ።

ይቀጥላል.....

@Mercy_ena_berua