እንኳን ደስ አለን የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሶስተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቆ ውሃ በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ስራ በትናንትናው ዕለት በይፋ መጀመሩ ይታወሳል፡ በአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ከባህር ጠለል በላይ 6 መቶ ሜትር ከፍታ አልፎ የግድቡ ውሃ ወደታችኛው ተፋሰስ አገራት መሄዱን ቀጥሏል። ባለፉት ሁለት ዓመታትም የግድቡ ሙሌት በስኬት መከናወኑም የሚታወስ ነው፡፡ 06/12/2014 819 views08:56