Get Mystery Box with random crypto!

የቅማንት ቡድን መሪን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የታች አርማጭሆ ወረዳ ገለጸ በማዕከላዊ ጎንደርና በ | Mereja Tv

የቅማንት ቡድን መሪን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የታች አርማጭሆ ወረዳ ገለጸ

በማዕከላዊ ጎንደርና በአዋሳኝ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ከክልሉ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ሲገባ እንደቆየ የሚነገረው በቅማንት ስም የተደራጀ ነው የሚባለው ቡድን አልፎ አልፎ ስጋቶችን መደቀኑን የመንግስት ሃላፊዎች ይገልጻሉ፡፡

የታች አርማጭሆ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቢራራ አቸነፍ የቅማንት ቡድን የቅማንት ህዝብን ከወንድም አማራ ህዝብ ለመገንጠልና ለመከፋፈል እንዲሁም ለህወሃት ቡድን መረጃ በማቀበልና አጋር በመሆን የሚሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህ ቡድን የምስጉኑን አርሶ አደር ሃብት ንብረቱን በመዝረፍ ፣ በማገትና በመግደል እየሰራ ያለ ፅንፈኛ ቡድን ነው ሲሉም ሃላፊው ወንጅለዋል፡፡

አቶ ቢራራ አክለውም አሁን ላይ የታችና የላይ አርማጭሆ ወረዳዎች በቅንጅት በመሆን ይህንን ቡድን ለማጥፋትና ሌሎችንም የፀረ ሰላም ሃይሎችን ለማስወገድ በትኩረት እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡

በቀጠናው ቡድኑ ከፍተኛ እርምጃ እየተወሰደበት ነው ያሉት ሃላፊ በቀበሌ የፀጥታ መዋቅሮች እርምጃ የቡድኑ ዋና መሪ ናቸው የተባሉ ሽታው ነጋና ግዛን ሰማ በሚል ስም የተጠቀሱት ታጣቂዎች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በታች አርማጭሆ ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

ከአደረጃጀትና አወቃቀር ጋር በተያያዘ የቅማንት ተወካይ ነን በሚሉ አካላትና በክልሉ መንግስት መካከል ያለው ተቃርኖ እስካሁን መፍትሄ እንዳላገኘ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡