Get Mystery Box with random crypto!

#እቴ_ውቤ እቴ ውቤ ሙሽራዬ/2/ የባሕርየ መመኪያዬ የክብር አክሊል መጽናኛዬ፡፡ ምሥራቅ ሆነሽ | መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች

#እቴ_ውቤ


እቴ ውቤ ሙሽራዬ/2/
የባሕርየ መመኪያዬ
የክብር አክሊል መጽናኛዬ፡፡
ምሥራቅ ሆነሽ ፀሐይን ወልደሽ
ደኅንነት ሰላም በእጅሽ ይዘሽ
ለዲያብሎስ መርዶ ሆነሽ፡፡
ሻማ ሆነሽ ልታበሪ
ድርሺልኝ ስትበሪ፡፡
ሱላማጢስ አንቺ እናቴ/2/
ፈጥነሽ ነይ እመቤቴ
በአንቺ ሊጠግ የአዳም ቁስሉ
ሊጠፋልን ሊከስምልን
ያ የሲኦል ነበልባሉ፡፡
እቴ ውቤ እመቤቴ/2/
ፍጠኚልኝ ነይ በሞቴ
ለእርቃኔ ልትሆኚኝ ልብስ
ለሕመሜ ልትሰጪኝ ፈውስ
ረሀቤም እንዲታገስ
ሕብስት ይዘሽ ሆነሽ መቅደስ
ውዴ ነይ ከሊባኖስ፡፡
ክብር ሰጥቶሽ ህያው ልጅሽ
ወረቅ ለብሰሽ ተጎናፅፈሽ
የምትቆሚ በልጅሽ ቀኝ
እኔ ኃጡኧን አማልጅኝ አክብሪኝ
ውዴ እርሺው ያን ቤትሽን
የቀድሞውን ያባትሽን፡፡
ውቤ ውዴ እመቤቴ/2/
የክብር ማማ ሰገነቴ
መርሕ ፋና ለህይወቴ
ፈጠኚልኝ ነይ በሞቴ/2/


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share