Get Mystery Box with random crypto!

ድንግል አርጋለች . . መጥቁል በተንኮል - ከማይደርስበት ሄሮድስ ሰይፍ ይዞ - ከማይሄድበት ልቧ | መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች

ድንግል አርጋለች
.

.
መጥቁል በተንኮል - ከማይደርስበት
ሄሮድስ ሰይፍ ይዞ - ከማይሄድበት
ልቧ በሀዘን - ከማይጎዳ
ከድካም ዓለም - ከምድር ጓዳ
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች።
.
.

ሰዶም፣ ገሞራ - ከሱባማ
ሱባዮንና - አድያማ
ከእሳት ገብተው - ከነደዱበት
በኃጥአት ምክንያት - ሞትን ካዩበት
የኖህን ዘመን ሰው - በእርጥብ እሳት
ከለበለበው - የግፍ ትኩሳት
ከዚሁ ምድር - ከቅጣት ሰፈር
እንዳይገባት - ለእሷ መደመር
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች።
.
.
በሰማይ ሆነው - ስለሚጣሯት
ሊያይዋት ጓግተው - ተነሽ እያሏት
በህብረ ምሳሌ - በአፈ ነቢያት
ሁሉም ሠራዊት - ሁሉም መላእክት
ድንቅ አቀባበል - እያደረጉ
እሷኑ ሆኖ - የሰማይ ጥጉ
ለአምላክ ማደሪያ - የሚሆን ማደሪያ
ማረፊያ ክፍሏ - ስሙ መጠሪያ
አንክሮ ሆኖ - ለቅዱሳኑ
ለዚህም ደስታ - እንዲፋጠኑ
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች
.
.
የምድሩን ልትስብ - ወደ ከፍታ
ልትጎትተው - ወደ እርፍት ቦታ
ለድል ትንሳዔ - አብነት ሆና
ቶማስ እንዳያት - ከፍላ ደመና
የኛስ መመኪያ - በቀኝ ቆማለች
ሰማይን ሆና - ሰማይ ሄዳለች
በእውነት ድንግል አርጋለች።

(አክሊሉ ደበላ ነሐሴ 16/2009ዓ.ም)

@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share