Get Mystery Box with random crypto!

#ደብረ_ታቦር መለኮት ተገለጦ ብርሃንን አበራ፣ በተቀደሰችው የታቦር ተራራ። የአብ አባትነት የ | መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች

#ደብረ_ታቦር


መለኮት ተገለጦ ብርሃንን አበራ፣
በተቀደሰችው የታቦር ተራራ።
የአብ አባትነት የወልድ ልጅነት፣
በግልጽ ታወቀ ተነገረ በእውነት።
ዮሐንስ ጴጥሮስ ያዕቆብን ጠርቶ
ሙሴን ከመቃብር ከሙታን አሥነስቶ
ከብሔረ ሕያዋን ኤልያስን አምጥቶ
በአምላክነቱ ፍጹም አንጸባርቆ
በሕያው መለኮት በብርሃናት ደምቆ
አብም ተገለጠ በብሩህ ደመና፣
የምወደው ልጄ ክርስቶስ ነውና።
እርሱን ብቻ ስሙት እስከ ዘለዓለም፣
ሕይወትን በእርሱ እንጂ ያለርሱ አትድኑም።
ብሎ ስለልጁ በግለጽ መሰከረ፣
አምላክነቱንም በተግባር ነገረ።

"...ታቦርና አርሞንዔም በስምኽ ደስ ይላቸዋል፤ ክንድኽ ከኀይልኽ ጋራ ነው፤ እጅኽ በረታች ቀኝኽም ከፍ ከፍ አለች።" መዝ ፹፰፥፲፪




@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share