Get Mystery Box with random crypto!

#ደብረ_ታቦር ከደብሮች ሁሉ ልቀሽ እውነትን ብርሃን አጥልቀሽ ተንቀሽ የነበርሽ ተራራ አንቺ የሚስ | መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች

#ደብረ_ታቦር

ከደብሮች ሁሉ ልቀሽ
እውነትን ብርሃን አጥልቀሽ
ተንቀሽ የነበርሽ ተራራ
አንቺ የሚስጥር ስፍራ
የመለኮት ብርሃን በር
የሥሉስ ቅዱስ ሚስጢር
ልቆ ያታየብሽ መንበር
ደብረ ታቦር !!!
ከአድማሳት ከፍ ከፍ ብሎ
ያስምሽ ተረፈ ውሎ
የተዘከረው በአለሙ
ምን ይሆን ወርቅ ስሙ?
ምን አገኘሽ የኔ ታቦር
እንዲያ ተከፍሎ የብርሃንሽ በር
የክብሩ ግርማ የዋጠሽ
እኮ ማነው የረገጠሽ
ጌታሽ ነው አሉ ስሰማ
ከተራራሽ አናት ማማ
የብረሃን ጉንጉን ሻማ
የጎነፀፈሽ በግርማ
ደብረ ታቦር

ከተራሮች አንቺን መርጦ
ከነ አባቱ ተገልጦ
ደጅሽን ሳይንቅ ማክበሩ
እንዴት እንዴት ይሆን ሚስጥሩ?
ይሄንንም አውቆ ዳዊት
ተናግርዋል አሉ በትንቢት
ታቦር ወአርማንኤም በሚል ቅኔ
በስሙ ተደሰቱ የኔ
እያለ ዘመረ በክብር
የዛችን ተራራ ሚስጢር
ያልብ አምላክ ዳዊት
የተናገረው ትንቢት
ለካ ይሄ ኖርዋል ግብ
ደጅሽ በብርሃን ማበቡ
ብሉ በዚያች የብረሃን እልፍኝ
የዘላለም ደስታ ልናገኝ
አስቦ በቅፅጰት እውነቱ
ገርሞትም አይደለ ከስተቱ
የብረሃን ፀዳል ድምቀቱ
እኮ እንደምን አይገርመው
ሙሴ እና ኤለያስ ቆመው
ክብሩን ሲያውጁ እያዩ
ማነዉ የሙሴን አምላክ ሙሴ ባዩ
ሲል ሙሴ ባህር ከፋዩ
የኤልያስንስ ክብር ጌታ
አውርደውት ከሰው ተርታ
ኤለያስ ባዮቹ እነማን ናቸው
ሲል ኤለያስ ገርሙዋቸው
የሥሉስ ቅዱስ ሚስጢር
የተገለጠብሽ መንበር

ደብረ ታቦር

ይሄን ሲያዩ ሃዋርያቱ
በድንጋጤ ሲመቱ
ደግሞ ወርዶ አባቱ
ልጄን ስሙት በማለቱ
በፍረሃት ማእበል ሲንገላቱ
ይሄን ሁሉ ሚስጥር በመታየቱ
በአንቺ አይደለ ታቦር
መገለጡ የሦስትነት ሚስጥር
ጥንትስ ታሪክሽ ተዘክሮ
መቼ ያልቃል ተነግሮ
እንዲያ ድንቅ
እንበል እንጂ ድንቅ!ድንቅ!
የብረሃንሽ ሰንደቅ

ከአድማሳት ልቆ ሲደምቅ
ክብር እንበልሽ ክብር!ክብር!
አንቺ እውነተኛ የሚስጥር በር
የሥሉስ ቅዱስ ነገር
የተገለጠብሽ መንደር

ደብረ ታቦር

ታቦር አንቺ ታድለሻል
የማይቻለውን ችለሻል
ለመሆኑ እንዴት ቻልሺው ታቦር!
ያን እውነተኛ ፍቅር

ከመንበሩ የተሳበ ንጉስ
ከብረሃን ሰረገላው ሲፈስ
መሰረትሽ ሳይናጋ
ባለበት ቆሞ የረጋ
ምን ይሆን ሚስጥሩ የፅናትሽ
በፊቱ ቆመሽ መታየትሽ??
ልብሱ ነጭ ሆኖ በረድ
አብም ከሰማይ ሲወርድ(ድምጽ ስልክ)
ዙርያው በክብር ደመና
ተመልቶ በብርሃን ፋና
ሙሴ ከመቃብር ተጠርቶ
ኤለያስ ከቤሄረ ሄያዋን መጥቶ
በእየሩሳሌም ስለ ሚሆነው
ሲወያዩ ላስተዋለው
ምን ይመስል ይሆን ገፁ
የብርሃን መለኮት መገለፁ
የሥሉስ ቅዱስ ሚስጢር
ልቆ ይታየብሽ መንደር

ደብረ ታቦር

ደግሞ የሃዋርያቱ
የእነዚያ የሦስቱ
ጴጥሮስ ያዕቆብ ዮሃንስ
በድንጋጤ ፈረስ
ሲጋልቡ ርደው
እንደ ቄጤማ ወርደው
ከስሩ የተነጠፈው
ምን ይሆን ምክኒያቱ?
ጴጥሮስ ተሸብሮ
ናላው በድንጋጤ ዞሮ
ለእያንዳንዳቹ በጋር
ሦስት ዳሶችን እንስራ
ያበራሽ ይበራ ስሙ ይግነን
ዛሬም ለእኛ በርሃኑ ይሁን
ገኖ የገነነ በፍቃዱ
በሪ ይሁንልን ሠንገዱ
ክብሩን ከፍ ከፍ ወደ ላይ
ከሰማይ ሰማያት በላይ
እንዲሁም በምድር በቀላይ
የ!!አምላካችን አዱናይ
ክብርሽ ዛሬም ነገም ይነገር
መሆንሽ እውነተኛ የብረሃን በር
የሥሉስ ቅዱስ ሚስጥር
የተገለጠብሽ መንበር
ደብረ ታቦር

@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share