Get Mystery Box with random crypto!

#እኔ_ነኝ ለሞቴ መሞትህን ዘንግቼ በፍቅርህ መዳንን 'ረስቼ ይቅርታህ ደጋግሞ ቢምረኝ በሀጥያት | መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች

#እኔ_ነኝ


ለሞቴ መሞትህን ዘንግቼ
በፍቅርህ መዳንን 'ረስቼ
ይቅርታህ ደጋግሞ ቢምረኝ
በሀጥያት ሁሌ እንደቆሸሽኹኝ

አለሁኝ ከቃልህ እርቄ ወድቄ
ፍቅርን ስትሰብከኝ ጥላቻን አርግዤ
ይቅርታን ስትሰብከኝ ቂም በሆዴ ይዤ
ቸርነት እንዳደርግ ሁሌ ብትመክረኝ
ራስ ወዳድ ቆንቋና ስስታም የሆንኩኝ
ወንድምህን ውደድ ብለህ ብትለኝም
ጥላቻዬ ገፍቶት ወንድምም የለኝም
ከቶ እንዳትጨነቅ ብለህ አጽናንተኸኝ
ዛሬም ጭንቀታም ነኝ ከቶ ተስፋ የለኝ
ማታ ከዳንኪራ ጠዋት ከመቅደስህ
ማዳንህ አጽናንቶ ፍቅርህ ያላደሰኝ
ሰምቶ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ብዬ
ሰው መስዬ የምታይ ሀጥያትን አዝዬ
ሀጥያቴን ሸፍነህ ይቅር ብትለኝም
የወንድሜን ጉድፍ ማየት አልተውኹኝም
ኗሪ መሳይ ከንቱ ቋሚ መሳይ ሟች ነኝ
ከንስሀ ይልቅ ልብሴን የማጠራ
አምሮ ለመታየት ከሰው ልጆች ጎራ
ሞትህ ግን ያልገባኝ አማኝ መሳይ ከንቱ
ሌላ ማንም አይደል እኔ ነኝ አቤቱ!!

ኢይዝራኤል


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share