Get Mystery Box with random crypto!

ሆሣዕና ማለት መድሐኒት ማለት ነው ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ነው፤ “ሆሳእና” ሲባል ትርጒሙ | መፍትሔ ሥራይ ወዓይነ ጥላ (የባህል ህክምና)



ሆሣዕና ማለት መድሐኒት ማለት ነው

ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ነው፤ “ሆሳእና” ሲባል ትርጒሙም “አቤቱ አኹን አድን” ማለት ነው፤ ይኽ በዓለ ሆሣዕና ከ9ኙ ዐበይት የጌታ በዓላት ውስጥ ሲኾን ክንፋቸው ትእምርተ መስቀል የሚሠራው ኪሩቤል ሱራፌል በፍርሀት በረዐድ ኹነው ዘፋኑን የሚሸከሙት ጌታ በትሕትና ኾኖ ጀርባዋ ላይ ትእምርተ መስቀል ባለባት በአህያና በውርንጫይቱ ተቀምጦ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት፣ የዘካርያስ ትንቢት
የተፈጸመበት፣

ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት፣ ሕፃናት በንጹሕ አንደበታቸው ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ብለው ያመሰገኑበት ሕዝቡም ልብሳቸውን እያነጠፉ ቅጠልን እያነጠፉ ጌታችን መድሐኒታችን የተቀበሉበትና ያመሰገኑበት ታላቅ በዓል ነው፡፡

በፆም በጸሎት በትጋት በስግደት ተፀምደን የተቸገሩና የታመሙ ወገኖቻችንን  በመርዳት የሰራነውን ሁሉ ሐጢአት የምንሽርበት ሱባኤ ይሁንልን።

መልካም ሰሙነ ሕማማት


ቴሌ ግራም ቻናላችን
https://telegram.me/mefetheaseray
https://telegram.me/mefetheaseray
https://telegram.me/mefetheaseray

ፌስቡክ ገፃችን
fb.me/etsedebedabe.abyssinia
fb.me/etsedebedabe.abyssinia
fb.me/etsedebedabe.abyssinia

#0911683089
#0915860690