Get Mystery Box with random crypto!

ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ እና ፕሮጀክት ሀረር ኢት | Medical Laboratory

ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ እና ፕሮጀክት ሀረር ኢትዮጵያ ከተሰኘ ሀገር በቀል ድርጅት ጋር በመተባበር ከየካቲት 23-28/2015 ዓ.ም በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተፈጥሮ የከንፈርና የላንቃ ክፍተት ያለባቸውን ህፃናትና አዋቂዎች የነፃ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት ይሰጣል።
እንዲሁም ባሕርዳር ዩንቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ Surgery International ከሚባል ድርጅት ጋር በመተባበር ከአሜሪካ በመጡ ሐኪሞች ከመጋቢት 4 እስከ መጋቢት 9/2015 ዓ.ም በተፈጥሮ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ያለባቸውን ህፃናትና አዋቂዎች የቀዶ ሕክምና ለማድረግ ዝግጁቱን ጨርሷል።
በመሆኑም ችግሩ ያለባችሁ ሰዎች በተገለፁት ቀናት ወደ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመምጣት የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።