Get Mystery Box with random crypto!

የጨጓራ ህመም የጨጓራ በሽታ ያለበት ሰው ላይ፣ የደም ማነስ ካለ እና የሚከሳ ከሆነ፣ ጥሩ | Medical Laboratory

የጨጓራ ህመም

የጨጓራ በሽታ ያለበት ሰው ላይ፣ የደም ማነስ ካለ እና የሚከሳ ከሆነ፣ ጥሩ ምልክት አይደለም።

የጨጓራ ህመም ያለበት ሰው ሁሉ፣ ደሞ የጨጓራ ቁስለት አለበት ማለት አይደለም።

የጨጓራ ቁስለት ሲኖር ፣ የህመም ስሜቱ እና የጉዳት ደረጃው፣ ቁስለቱ እንደወጣበት ቦታ እና እንደ ይዘቱ የተለያየ ነው።

አንድ ሰው ላይ፣ የጨጓራ ቁስለት ባይኖር እነኳን፣ የጨጓራ ህመም ሊፈጠር ይችላል።

የጨጓራ ቁስለት ደሞ፣ ባጣዳፊ መልኩ የሚፈጠር ሳይሆን አብዛኛውን ግዜ ስር ሰዶ የሚፈጠር ቁስለት ነው።

አንዳንዴ ፣የጨጓራ ቁስለት ያለባቸው ሰዎች፣ የህመም ስሜት ላይሰማቸው ይችላል፣ በተቃራኒው ደሞ፣ የጨጓራ ህመም ስሜት የሚሰማቸው አብዛኛዎቹ ታካሚዎች፣ በምርመራ ግዜ የጨጓራ ቁስለት ላይኖራቸው ይችላል።

አንድ ሰው ላይ የጨጓራ ህመም እና የጨጓራ ቁስለት ሊፈጠር የሚችለው፣ በተለያዩ ምክኒያቶች፣ ሆድ የሚያመርተው የአሲድ መጠን የበዛ ከሆነ እና የሆድ ግድግዳ ራሱን ከዚህ አሲድ የሚከላከልበት መንገድ የተዳከመ ከሆነ ነው።

አብዛኛውን ግዜ ፣ በህክምናው አንድ ሰው ላይ የጨጓራ ህመም መኖሩን ለማወቅ አዳጋች አይደለም፣ የህመም ስሜቶቹን በማገናዘብ የጨጓራ በሽታ መኖሩን ለመተንበይ ያስችላል።

ምግብ ከተበላ በኋላ አለመስማማት፣ በተደጋጋሚ ግዜ ማግሳት ፣ ቃር ወይም የደረት ማቃጠል እና ማቅለሽለሽ ፣  የመሳሰሉ የህመም ስሜቶች፣ የጨጓራ ህመም መኖሩን የሚገልፁ ምልክቶች ናቸው።

ከእንብርት በላይ የሚሰማ የሚጎትት የሆድ ህመም መኖር፣  ማቅለሽለሽ እና በተደጋጋሚ ማስመለስ፣ በተለይ ደሞ ደም የሚያስመልስ ከሆነ እና ከፍተኛ እና አጣዳፊ የሆነ የሆድ ህመም ካለ፣ ይህ አይነቱ የህመም ስሜት ጠንከር ያለ የጨጓራ ቁስለት መኖሩን የሚያመላክት ስለሆነ እና፣ እንዲሁም ወዲያውኑ ካልታከመ ለከፋ ጉዳት ስለሚዳርግ፣ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።

እድሜያቸው 45 እና ከዛበላይ የሆኑ ሰዎች፣ የጨጓራ ህመም ስሜት ከታየባቸው፣ እንዲሁም ደሞ ፣በየትኛውም የእድሜ ክልል ላይ ያሉ ሰዎች፣
በተደጋጋሚ ግዜ የሚመጣ ማስመለስ ካላቸው፣
ለመዋጥ የሚቸገሩ እና ሲውጡ ህመም የሚሰማቸው ከሆነ፣
መክሳት ወይም ክብደት መቀነስ ካላቸው፣ እና፣
እንዲሁም የደማነስ የሚታይባቸው ከሆነ፣ የኢንዶስኮፒ ምርመራ የሚያስፈልጋቸው ይሆናል።

የፀጉር እንክብካቤ
(Shampoo & Conditioner)

የፀጉር እንክብካቤ ፣ የፀጉር ንፅህናን ከመጠበቅ ይጀምራል።

ፀጉር ከቆዳ በበለጠ መልኩ በተለያዩ ምክኒያቶች ሊቆሽሽ ይችላል፣ ደረቅ ፀጉር እርስ በእርሱ ሲፋተግ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ስለሚያጠራቅም፣ በቀላሉ ብናኝን የመሳብ አቅም አለው።

በተጨማሪም የራስ ቅል ቆዳ ፍርፋሪ ፣ከፀጉር ስር የሚመነጭ የተፈጥሮ ወዝ እና ላብ ከልክ ያለፈ ሲሆን፣ እንዲሁም ለፀጉር ውበት በምንጠቀማቸው፣ ዘመናዊ እና ባህላዊ ቅባቶች ምክኒያት ፀጉር በቀላሉ ሊቆሽሽ ይችላል።

ታዲያ፣ ፀጉር ሲታጠብ፣ ከትኩስ ውሀ ይልቅ፣ በመጠኑ ለብ ያለ ውሀን መጠቀም ተመራጭ ነው ። ፀጉር እርጥብ እንደሆነ ማበጠር ደሞ፣ የፀጉርን ሰበቃ ስለሚጨምር ፀጉር ከልክ በላይ ሊሳሳብ እና ሊሰባበር ይችላል።

ፀጉር እርጥብ እንደሆነ ለማበጠር ከተፈለገ፣ ለዚህ ተብለው የተዘጋጁ ለየት ያሉ ኮንዲሽነሮችን መጠቀም ያስፈልጋል።

ስለነዚህ ምርቶች በቪዲዮው ላይ አይነታቸውን አብራርቻለሁ።

ፀጉር ላይ የምንጠቀማቸው ሳሙናዎች፣ ጥንካሬያቸው፣ የፀጉሩን አይነት ያማከለ ካልሆነ፣ የፀጉር ቅርፊትን እና የፀጉር ተፈጥሮአዊ ወዝን ከልክ ባለፈ መልኩ ስለሚያነሱ፣ ፀጉርን ሊያገረጡና ውበቱን ሊያሳጡት ይችላሉ።

በተለይ ጨዋማ የሆነ ወይም ፣የጉድጓድ ውሀ ባለበት ቦታ የሚኖር ሰው፣ ለፀጉር ንፅህና፣ የገላ ወይም የልብስ ሳሙናን ባይጠቀም ተመራጭ ነው።

ከዛ ይልቅ ፣ እንደ ፀጉሩ አይነት በተለያየ ጥንካሬ የተዘጋጁ የፀጉር ሻምፖዎችን መጠቀም ይመረጣል።

ገበያ ላይ 11 አይነት የፀጉር ሻምፖዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ። እነዚህ ሻምፖዎች በውስጣቸው የሚጨመርባቸው ግብአት፣ የተጠቃሚውን ትኩረት ለመሳብ ሲባል፣ ከፋብሪካ ፋብሪካ ወይም ከምርት ምርት የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ።

ነገር ግን፣ የትኛውም ፋብሪካ ቢሆን፣ አንድን ሻምፖ ለገበያ ሲያቀርብ፣ በዋነኝነት 5 የዲተርጀንት አይነቶችን ይጠቀማል።

ከነዚህ ውስጥ፣ አንድን ሻምፖ ጠንካራ የሚያስብለው፣ በውስጡ በሚይዘው የ ሰልፌት አዘል ዲተርጀንት ፣አይነት እና መጠን ይሆናል።

ስለተለያዩ የሻምፖ እና የኮንዲሽነር አይነቶች፣ እንዲሁም የትኞቹ ምርቶች ለየትኛው የፀጉር አይነት ተስማሚ እንደሆኑ፣ በቪዲዮው ላይ በምስል የታገዘ መረጃ አስቀምጫለሁ።


@medilabet    @medilabet     @medilabet