Get Mystery Box with random crypto!

የፀጉር እንክብካቤ (Shampoo & Conditioner) የፀጉር እንክብካቤ ፣ | Medical Laboratory

የፀጉር እንክብካቤ
(Shampoo & Conditioner)

የፀጉር እንክብካቤ ፣ የፀጉር ንፅህናን ከመጠበቅ ይጀምራል።

ፀጉር ከቆዳ በበለጠ መልኩ በተለያዩ ምክኒያቶች ሊቆሽሽ ይችላል፣ ደረቅ ፀጉር እርስ በእርሱ ሲፋተግ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ስለሚያጠራቅም፣ በቀላሉ ብናኝን የመሳብ አቅም አለው።

በተጨማሪም የራስ ቅል ቆዳ ፍርፋሪ ፣ከፀጉር ስር የሚመነጭ የተፈጥሮ ወዝ እና ላብ ከልክ ያለፈ ሲሆን፣ እንዲሁም ለፀጉር ውበት በምንጠቀማቸው፣ ዘመናዊ እና ባህላዊ ቅባቶች ምክኒያት ፀጉር በቀላሉ ሊቆሽሽ ይችላል።

ታዲያ፣ ፀጉር ሲታጠብ፣ ከትኩስ ውሀ ይልቅ፣ በመጠኑ ለብ ያለ ውሀን መጠቀም ተመራጭ ነው ። ፀጉር እርጥብ እንደሆነ ማበጠር ደሞ፣ የፀጉርን ሰበቃ ስለሚጨምር ፀጉር ከልክ በላይ ሊሳሳብ እና ሊሰባበር ይችላል።

ፀጉር እርጥብ እንደሆነ ለማበጠር ከተፈለገ፣ ለዚህ ተብለው የተዘጋጁ ለየት ያሉ ኮንዲሽነሮችን መጠቀም ያስፈልጋል።

ስለነዚህ ምርቶች በቪዲዮው ላይ አይነታቸውን አብራርቻለሁ።

ፀጉር ላይ የምንጠቀማቸው ሳሙናዎች፣ ጥንካሬያቸው፣ የፀጉሩን አይነት ያማከለ ካልሆነ፣ የፀጉር ቅርፊትን እና የፀጉር ተፈጥሮአዊ ወዝን ከልክ ባለፈ መልኩ ስለሚያነሱ፣ ፀጉርን ሊያገረጡና ውበቱን ሊያሳጡት ይችላሉ።

በተለይ ጨዋማ የሆነ ወይም ፣የጉድጓድ ውሀ ባለበት ቦታ የሚኖር ሰው፣ ለፀጉር ንፅህና፣ የገላ ወይም የልብስ ሳሙናን ባይጠቀም ተመራጭ ነው።

ከዛ ይልቅ ፣ እንደ ፀጉሩ አይነት በተለያየ ጥንካሬ የተዘጋጁ የፀጉር ሻምፖዎችን መጠቀም ይመረጣል።

ገበያ ላይ 11 አይነት የፀጉር ሻምፖዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ። እነዚህ ሻምፖዎች በውስጣቸው የሚጨመርባቸው ግብአት፣ የተጠቃሚውን ትኩረት ለመሳብ ሲባል፣ ከፋብሪካ ፋብሪካ ወይም ከምርት ምርት የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ።

ነገር ግን፣ የትኛውም ፋብሪካ ቢሆን፣ አንድን ሻምፖ ለገበያ ሲያቀርብ፣ በዋነኝነት 5 የዲተርጀንት አይነቶችን ይጠቀማል።

ከነዚህ ውስጥ፣ አንድን ሻምፖ ጠንካራ የሚያስብለው፣ በውስጡ በሚይዘው የ ሰልፌት አዘል ዲተርጀንት ፣አይነት እና መጠን ይሆናል።

ስለተለያዩ የሻምፖ እና የኮንዲሽነር አይነቶች፣ እንዲሁም የትኞቹ ምርቶች ለየትኛው የፀጉር አይነት ተስማሚ እንደሆኑ፣ በቪዲዮው ላይ በምስል የታገዘ መረጃ አስቀምጫለሁ።


@medilabet @medilabet @medilabet