Get Mystery Box with random crypto!

በነገራችን ላይ ከሁሉም በባሰ ሁኔታ  በኑሮ ውድነት አለንጋ እየተገረፈ ያለ  ከመንግስት ሰራተኛ የ | Medical Laboratory

በነገራችን ላይ ከሁሉም በባሰ ሁኔታ  በኑሮ ውድነት አለንጋ እየተገረፈ ያለ  ከመንግስት ሰራተኛ የመጀመሪያው ''የጤና ባለሞያ'' ነው። ሌሎች እኮ ኑሮአቸውን የሚገፉት አገልግሎት እጅ በእጅ ስለሆነ ነው። ለምሳሌ አንድ ቀያሽ (ሰርቤየር) ደመዎዙ 5480 ነው። ነገር ግን ሁሉንም የሚሰጠውን አገልግሎት የሚከውን እጅ በእጅ ነው ።ጸዳ ያለ ቤት  የተሻለ ኑሮ ይኖራሉ። ለምሳሌ አነሳሁኝ እንጅ  ሁሉም ሴክተር በእጅ መንሻ ነው። ትክክለኛ ህጋዊ አሰራር እስኪመስል ህ/ሰቡም ከፍሎ ጉዳይ ማስፈጸም ነው የሚፈልገው። ለነገሩ የሚፈጸመው ጉዳይም  በትክክለኛው መንገድ ትክክል ስላልሆነ ሁሉም ነገር በገንዘብ ሆኗል።
ወደ ጤና ባለሞያው ስመለስ''  ህጋዊ ባሪያ ነህ ''የተባለ ይመስል ከቀን ሰራተኛ ባነሰ መልኩ እየተሰቃየ በጠኔ ሲገረፍ ይኖራል።
ከ'' ሀኪም ፔጅ'' ሳነብ ያገኘሁት አሳዛኝ ታሪክ  እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ።

በሰፈር የሚያውቁት ደላላ ድል ያለ ሰርግ ሰርጎ ሀኪሙን ጃቢ ብሎ ይጠራዋል ። ነገር ግን የሚዋጣው የአጃቢ መዋጮ 2000 birr  ስለነበር ሀኪሙ ስለለለው  ከአጃቢነት ወደ ተራ ተጋባዥነት ቀይሮ ሲሄድ  ገንዘብ መዋጮ የሚሰበስብ ልጅ አገኘና አዋጣ ሲሉት የተሰበሰበውን የመዋጮ ሊስት ሲመለከት ከሰፈር የሚያውቀው ሊስትሮ እንኳን 1000 ብር አዋጦ ተመለከተው ።በጣም ደነገጠና  500 ብር ብቻ ከኪሱ አለ። ጭንቅ አለውና የተዋረደ መስሎት ሁለንም 500 ብሩን አዋጣው ።ስምህ ማን ልበልህ ሲለው ዶክተር እከሌ ማለቱ ደብሮት  እከሌ ብለህ መዝግብ ብሎ እያስመዘገበ ሳለ ሌላ መዋጮ የሚከፍል ሰው ከተፍ አለና ዶክተር እንዴት ነህ ብር አዋጣህ እንዴ ሲለው ያ መዋጮ ሲመዘግብ የነበረ ሰው ዶክተር ሲለው ተመለሰና እንደገና ስሙንና ያዋጣውን ተመለከተ በአግራሞት። ዶክተሩም ላበት ውጦት ተሸማቆ እና የበታችነት ስሜት ተሰምቶት ወደ ቤቱ አመራ። ወደ ሰርጉም መሄድ አልፈለገም የሚል መረጃ ሳነብ አንጀቴን በልቶት ነበር ።
አንድ ጀማሪ ሀኪም 9056 ደሞዙ ሆኖ
በወር 6400 ብር የተጣራ
በቀን  ሲሰላ  9056/30=301 ብር ይከፈለዋል።  ሶየው እኮ ስሙ የገዘፈ ነው ሃኪም የተባለ ትልቅ ሞያ ።ግን በቀን 301 ብር ይከፈለዋል

የቤት ኪራይ  ሀኪም ስለሆነ ቢያንስ 5000 ብር በላይ ቢያወጣ
የወር ቀለብ  ቤተሰብ ያውም ባይኖረው ብንል   ቁርስ  በትንሹ 70 ብር,ምሳ 80 ብር,ራት 100 ብር  =250 ብር በቀን በማት ነው።
ሌላ የመዝናኛ ፣አልባሳት ማህበራዊ ወጪ ሳንጨምር በድምሩ  250*30=7,500 ያወጣል።
የቤት ኪራይ 5000 ሲደመርበት=7500+5000=12,500 ብር ይሆናል

12,500-6400=6100 ብር   Negative  expenditure

ደግሞ ይህንን ሀኪም CRC/MCC ,ህሙማን አላረካህም እያሉ ቁም ስቅሉን ያሳዩታል። እረ ወዮ !መኖር! አልቻልኩም ብሎ  ሰልፍ ባደረገበት ለውጥ በተባለው ዘመን ጠሚው'' ጤና ባለሞያ ቅድሚያ ገውንህን እጠብ'' ብሎ ሲሳለቅበት  አሜን ብሎ ተቀበለ ። ነገርዬው ጤና ባለሞያው አንድነት ስለለለን ይበለን ያስብላል።

መፍትሄው እንደሀገርም ሆነ እንደ ክልል የስራ ማቆም አድማ በማድረግ የጤና ባለሞያ መኖር እንዳልቻ ለማህበረሸቡ ማስረዳት መቻል አለበት ባይ ነኝ!!

@medilabet