Get Mystery Box with random crypto!

አሜባ (Amebiasis) አሜባ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የሚያጠቃ ረቂቅ ጥገኛ ተዋሲያን ነው፡ | Medical Laboratory

አሜባ (Amebiasis)

አሜባ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የሚያጠቃ ረቂቅ ጥገኛ ተዋሲያን ነው፡፡ አሜባ በዋነኝነት አንጀትን የሚያጠቃና ሲሆን ከአንጀት ውጭም ጉበት፣ልብ እንዲሁም ሳንባን ሊያጠቃ ይችላል፡፡

መንስኤዎቹ

ኢንታሜባ ሂስቶሎቲካ (Entamoeba Histolytica) የተባለ ጥገኛ ትላትል በምንመገበዉ ምግብ እና ዉሃ እንዲሁም ቀጥታ ከተዋህሲያኑ ጋር ባለን ንክኪ አማካኝነት ወደ ሰዉነታችን በመግባት ህመም ያስከስትልል፡፡ይህ ጥገኛ ትልትል በበሽታዉ ከተያዘ ሰዉ ወደ ጤነኛ ሰዉ በቀላሉ ይተላለፋል፡፡

አጋላጭ ሁኔታዎች

የተበከለ ምግብ እና መጠጥ መጠቀም
በምግብ ዝግጅት ወቅት ንጽህን አለመጠበቅ
በፊንጢጣ በኩል የሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነት
በቀዶ ህክምና ወቅት የህክምና እቃዎች መበከል
እርግዝና
ህጻናት ልጆች

ምልክቶቹ

የሆድ ህመም/ቁርጠት
የምግብ ፍላጎት መቀነስ
ደም የቀላቀለ ተቅማጥ
ድካም/የሰዉነት መዛል
ራስ ምታት/ማዞር
ክብደት መቀነስ
ማስማጥ
የፊንጢጣ አካባቢ ህመም መሰማት
ማስመለስ
ትኩሳት

መከላከያ መንገዶች

በምግብን ዝግጅት ወቅት ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ
የሚጠጣ ውሃን አፍልቶ መጠቀም
አትክልትን በደንብ አብስሎ መመገብ
ሽንት ቤት ከተጠቀሙ በኋላ እና ከምግብ ዝግጅት በፊት እጅን በሳሙና መታጠብ
ህጻናት ልጆች የሚጫዎቱበትን ቦታ ንጹህ ማደረግ እና እጃቸዉን ወደ አፋቸዉ እንዳያስገቡ መጠበቅ

@medilabet