Get Mystery Box with random crypto!

#ሕይወተ_ወራዙት / የወጣቶች ሕይወት (በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ) #ክፍል_4 #ግብረ_አውናን(M | መዓዛ ሠናይ

#ሕይወተ_ወራዙት / የወጣቶች ሕይወት

(በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ)

#ክፍል_4

#ግብረ_አውናን(Masterbation)#ተገቢ_ነውን_?

#ግብአውናን የተባለበት ምክንያት አውናን የተባለው ሰው ከሚስቱ ጋር ግንኙነት እየፈፀመ ሳለ ዘሩን ከማህፀን ውጪ ያፈሰው ስለነበር ነው ። ግብረ አውናን/Masterbation (ሴጋ) በመፅሐፍ ቅዱስ ስንመዝነው ተገቢ ነገር አለመሆኑን እንረዳለን ። አንድ ገበሬ ለዘር የሚያስቀረው ዘር ራሱ ከሚመገበው እንኳን የተሻለውን ምርጥ ዘር ነው ። ስለሆነም ከዘር ወቅት በፊት ተጠንቅቆ በጎተራ ያስቀምጠዋል። በዘር ወቅት ደሞ አውጥቶ በመልካም ማሳ ላይ ይዘራዋል እንጂ ያለ ቦታው አይበትነውም ። እንደዚሁም የሰው ዘር ከእህል ዘር ይከብራልና በመልካም ጎተራ ማለትም በሰውነት ተጠብቆ መቆየት አለበት ። ከጋብቻ ቡሃላ ባልና ሚስት ሩካቤ ሲፈፅሙ ደግሞ በመልካምዋ ማሳ በሚስት ማኀፀን መዝራት እንጂ ሆን ብሎ እራስን በራስ በማርካት በየቦታው ማፍሰስ ተገቢ አይደለም ። እራስን በራስ ማርካት /ሴጋ መፈፀም ተገቢ አለመሆኑን የሚያስረዱ በልዩ ልዩ አገባብ የተጠቀሱ ጥቅሶች አሉ

"እንግዲህ በምድር ያሉትን ብልቶቻችሁን ግደሉ እነዚህም ዝሙትና ርኩሰት ፍትወትም ክፋ ምኞትም ፣ ጣዖትን ማምለክ የሆነ መጎምዠት ነው " (ቆላ 3:5) እዚህ ላይ "ብልቶቻችሁን ግደሉ" ሲል ቆርጣችሁ ጣሉ ማለት ሳይሆን አትቀስቅሱ ማለት ነው ። "ደንዝዘውም በመመኘት ርኩሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ " (ኤፌ 4:19) ይህ ጥቅስ ለግብረ አውናንም ሊጠቀስ ይችላል። ምክንያቱም ሴጋ ዝሙትንና ርኩሰትን የመመኘት ዝንባሌ ዋና መገለጫ ነውና ። ሐዋርያው ጳውሎስ በፍትወት ለተቃጠሉ መፍትሄ ሲሰጥ " በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ፤ ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ " ብሏል ። (1ቆሮ 6:9) ስለዚህ በዝሙት ለሚቃጠሉ መፍትሄው #ማግባት እንጂ #ሴጋ መፈፀም አይደለም። ሐዋርያው ማግባትን እንጂ ግብረአውናንን እንደ መፍትሄ አልመከረምና

ሌላው አምላካችን ሥጋ የፍትወቱን ያህል አግኝቶ እንዲረካ ጋብቻን ሲያሰናዳ ከጋብቻ ጋር አብረው የሚሄዱትን ኃላፊነቶች ከመቀበልና ከመሸከም ጋር ነው ። ነገር ግን ሴጋ ምንም አይነት ኃላፊነት ሳይሸከሙ ያንን እርካታ ለማግኘት እንደ መሞከር ይቆጠራል ።የምኞት ቃጠሎን ዘርን በማፍሰስ ለማብረድ መሞከር ስሕተት ነው ። ምክንያቱም 1 ችግር ሲያጋጥም ተቋቁሞ በማለፍ ፈንታ በተሳሳተ ጎዳና በመጓዝ ችግሩን ለማምለጥ መሞከር ሽንፈትንና ደካማነትን የሚያመለክት በመሆኑ ነው ። በዚ ምክንያት ብዙ ወጣቶች ላለመማራቸውና ለሥራ አጥነታቸው ወይም በሕይወታቸው ለገጠማቸው 1 ችግር ተገቢና ጤናማ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ዱርዬነትን ፣ ሌብነትን ፣ ሰካራምነትን፣ ሲጋራ ማጨስንና ጫት መቃምን ፣ በየክለቡ መጨፈርን እንደ አማራጭ ይወስዳሉ

ታዲያ የሽንፈትና የደካማነት ምልክት አይደለምን ? አንዳንድ ሰዎች "1 ሰው ጋብቻ ለመመስረት ዕድሜው ያልደረሰ ወይም ሁኔታዎች ያልፈቀዱለት ከሆነ የጋብቻ ጊዜውን እየተጠባበቀ በዝሙትና በሰዶማዊ ተግባር ከሚሰነካከል ራሱን በራሱ በማርካት ተግባር ቢቆይ አይሻልም ? እስከ ማለት ደርሰው ግብረአውናን/ሴጋ ተገቢ ነገር ለማስመሰል ይጥራሉ። ሁሉም የዝሙት ልዩ ልዩ ገፅታዎች ናቸው ። ሰይጣንም ቢሆን ሐሳቡ እንድንፈፅምለት ከግብረ ሰዶምና ከዝሙት ታንሳለች በማለት ያሳስበናል እንጂ በዚሁ ኃጢአት የተያዙትን ደሞ ያልሰሩት ዝሙትና ግብረ ሰዶም እንዲፈፅሙለት "አንደኛውን ዝሙት ይሻላል ፡ ይህን የመሰለ ኃጢአት እየሰራህ ዝሙት አልሰራሁም ለማለት ነው ? እያለ ተስፋ ለማስቆረጥ እንደሚያምታታቸው መዘንጋት የለብንም።
... ይቀጥላል ...
https://t.me/meazasenay