Get Mystery Box with random crypto!

#ሕይወተ_ወራዙት / የወጣቶች ህይወት (በቀሲስ ህብረት የሺጥላ ) #ክፍል_5 #ከግብረ_አውናን | መዓዛ ሠናይ

#ሕይወተ_ወራዙት / የወጣቶች ህይወት

(በቀሲስ ህብረት የሺጥላ )

#ክፍል_5

#ከግብረ_አውናን (Masterbation) #እንዴት_መላቀቅ_ይቻላል?

#ሀ. ግብረ አውናን እንደ ማር ጠብታ ነው ። የማር ጠብታ ልብስ ላይ የወደቀ እንደሆነ በፍፁም የሚለቅ አይመስልም ፣ ነገር ግን ትንሽ ለቅለቅ ያደረጉት እንደሆነ ወዲያውኑ ይለቃል። ይህ ክፋ ልማድም እንደማር በቀላሉ ባይሆንም ከልብ በመፀፀት በጠንካራ መንፈስ ከተነሱ ሊያስወግዱት ይቻላል። በመጀመሪያ የሚያስፈልገው ከዚ ነገር መቼም መላቀቅ አልችልም ብሎ ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ከፍተኛ ትግልና ጥረት ይጠይቃል ። ስለዚህ ተስፋ መቁረጥ ፈፅሞ አይገባም

#ለ. ሴጋ ልማድ ነው ። ልማድ ደሞ በሌላ ልማድ ይሸነፋል። ጠንክረህ ከተነሳህ ይህን ተግባር በትዝታ ብቻ የምታስብበት ቀን ሩቅ አይሆንም ። ነገር ግን ከዚህ ልማድ ጋር ለመዋጋት ከመነሳትህ በፊት "ይህን ክፋ ልማድ ምን ያህል ከልቤ ጠልቼዋለው ? " በማለት ራስህን ጠይቅ ። መላልሰህ የምትሰናከለው ሳትፀፀት ወይም ሴጋን መተው ስላልፈለክ ሳይሆን ጣዕሙ በልቡናህ ስላለና ጎጂነቱ ዘልቆ ወደልብህ ስላልገባ ነው ። ስለዚህ ይህን ነገር ከልብህ ልትጠላው ይገባል

#ሐ. ይህን ክፋ ልማድ እንደ እሳት የሚያያይዙት የራስህ ተግባርና በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ናቸው ። ከዚህ እኩይ ተግባር መላቀቅ ከፈለክ #ተዐቅቦ ያስፈልግሀል። #ተዐቅቦ ማለት መከልከል መቆጠብ ማለት ነው ። የምትከለከለውም ወደዚህ መጥፎ ሐሳብ ልቡናህን የሚስቡትን ነገሮች ከማየት ፣ ከመስማት፣ ከመንካትና ፣ ከመሳሰሉት ነው ። ስለዚህ የሴቶችን ገላ በፊልምም ፣ በአካልም ቢሆን በምንም መልኩ ከማየት ተቆጠብ። በመዋኛና በመጠመቂያ ቦታዎች ራስህን ጠብቅ የሴት ልጅን መልክና ቅርፅ መርዘህና አተኩረህ አትመልከት ። ስለ ዝሙት የሚያሳስቡ ሥዕሎችን፣ ፅሁፎችን፣ ወሬዎችን ፣ የሴት ገላ የሚያሳዩ የሙዚቃ ክሊፖችን ፣ የወሲብ ፊልሞችን አጥብቀህ ሽሻቸው ።ስራህ ሁሉ አንተው እያራገብክ ለምን ይቃጠላል ? እንዳይሆንብህ

#መ. ዘወትር ልቡናህ የሚጠመድበትን ነገር ፈልገህ አድርግ ። ቦዘኔ አትሁን ትጉህ ሰራተኛ ሁን ።ስራህም አይምሮህን የሚያሰራ ቢዚ የሚያደርግ ይሁን ። ትርፍ ሰአት አይኑርህ ። የሚነበብ ወይም ሌላ የሚሰራ ስራ ፈጥረህ ሥራ

#ሠ. "ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው " የሚለውን የወንጌል ቃል አስብ ። በዚህ ክፋ ልማድ ተጠምደህ ሳለ ለብቻህ መሆንን አትውደድ ። ቢቻልህ አኗኗርህና መኝታህ ከምታፍረውና ከምታከብረው ሰው ጋር ይሁን ። ይህም ጓደኛህ ወይም ከቤተሰብህ አንዱ ሊሆን ይችላል። በፀሎት ከሚረዱህ መንፈሳውያን መምህራን አባቶች ጋር ጊዜ ማሳለፍን ውደድ

#ረ. እንቅልፍ የያዘህ ስለ መሰለህ ብቻ ወደ መኝታህ አትሂድ ። አንዳንዴ ተኝተህ ውለህ እንቅልፍ ያምርሀልና ። ነገር ግን ሰይጣን ሊፈትንህ ከሆነ በምትነኛበት ጊዜ እንቅልፍ ከአይንህ ይርቃል ። ተከትሎም ፈተናው ይመጣና ወደ ዝሙት ህሊናህ ይሳባል ። ከዛ ሴጋ ትፈፅማለህ። ስለዚህ ከመተኛትህ በፊት በደንብ መድከምህንና ቶሎ ማሸለብ መቻልህን መርምረህ ተኛ

#ሰ. ጸሎት ማድረግንም አትርሳ የሚረሳ ነገር አይደለምና ። ስትተኛም በጀርባህ ወይም በሆድህ አትተኛ ። ከዚህ ይልቅ በጎንህ ለመተኛት ሞክር። አመጋገብህ በልክ ይሁን ፣ ፆምን ፁም ፣ ቅዱሳት መፃህፍትን አንብብ። መዝሙርንም አዳምጥ ዘምር

#ሸ. እንዲህ ያለ ፈተና ሲነሳብህ /አድርግ አድርግ ሲልህ / ከቻልክ ስገድ ።ወይም የሆነ እንቅስቃሴ /ስፖርት / ስራ ። ሽንት መሽናትም ጥሩ መፍትሄ ነው አይምሮህ ሽፍት እንዲያደርግ ያደርገዋል። በየጊዜው ፀበል መጠመቅን ቸል አትበል ። የሴት ገላን ሳታይ

#ቀ. ሰውነትህን አትነካካ ቢበላህ እንኳን አትከከው ። ስታክና ስትነካካው በዛው አድርግ አድርግ ሊልህ ይችላልና ። ንፁህ ሁን ፣ ሻወር ውሰድ ፣ ወክ አድርግ ፣ አንብብ ። ከምንም በላይ አጥብቀህ ፀልይ ። ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን ።በቀጣይ የወር አበባን እናያለን

https://t.me/meazasenay