Get Mystery Box with random crypto!

#የወጣቶች_ሕይወት /ሕይወተ ወራዙት (በቀሲስ ህብት የሺጥላ) #ክፍል_3 #ግብረ_አውናን (Mas | መዓዛ ሠናይ

#የወጣቶች_ሕይወት /ሕይወተ ወራዙት
(በቀሲስ ህብት የሺጥላ)

#ክፍል_3

#ግብረ_አውናን (Masterbation) #ምንድነው ?

እግዚአብሔር ለምህረትና ለመቅሰፍት ያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ ግዳጆችን የሚፈፅሙ መላእክት እንዳሉት ሁሉ ሰይጣንም ሰውን በልዩ ልዩ መንገድ እንዲፈትኑ ድርሻ ሰጥቶ ያዘጋጃቸው አጋንንት አሉት ። ከእነርሱም ውስጥ አንዱ #ሰይጣነ_ዝሙት ነው ። ሰይጣነ ዝሙት የሰው ልጆችን የሚፈትንበት መንገድ የተለያየ ነው ። እንደውም አንዳንዶቹ ፈተናዎቹ የዝሙት አይመስሉም

#ፆር_የለመዱ (የሰይጣንን የፈተና ስልት በደንብ ለይተው ያወቁ ) አበው ቅዱሳን ግን ሽንገላ የሞላበትን የሰይጣንን ፈተና አሸንክላ ምን እንደሚመስል መጪ ትውልድ እንዲያውቀው በሕይወታቸው ያዪትንና መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን ፅፈው አስቀምጠዋል ። ለምሳሌ ሰይጣነ ዝሙት የሰውን ልጅ ወደ ዝሙት ተግባር ከሚስብባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ገሢሥ ነው ። #ገሢሥ ማለት ማሻሸት፣ መነካካት ፣ መዳበስ ማለት ነው ። ነብዩ ሕዝቅኤል "ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር " (ሕዝ 23:3) በማለት እንደተናገረው ለዘር የደረሱ ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲላፋና ሲዳሩ ሩካቤ ሳይፈፅሙ ዘራቸው የሚፈስበት ጊዜ አለ ። ይህን ድርጊት እንደ ተድላ በመቁጠር ብዙ ወጣቶች ሆን ብለው ያደርጉታል

በቅዱስ መፅሐፍ "የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር " እንደተባለው ቦታ ሳይመርጡና ሰው ሳይለዩ የሴት ልጅን ገላ በመዳበስ "ግልሙትናን ማፍሰስ " ያሳፍራል ። ይህ መጥፎ ልማድ የተጠናወታቸው ሰዎች ግርግርና በሰው ብዛት የተጨናነቀ ስፍራ የሴቶችን ገላ እንደ ሐሳባቸው ለመነካካት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ሰው ስራቸውን አይቶ እንዳይነቅፋቸው የተለያዪ ዘዴዎችን ይፈጥራሉ። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ምንም ሳያውቁና በእንቅልፍ ልባቸው ያደረጉት ለማስመሰል እንደ ተኛ ሰው እየተገላበጡና እያንኮራፋ በልዩ አጋጣሚ አጠገባቸው የተኛችውን ሴት ገላ ሲዳብሱ ያድራሉ

ይህ ድርጊት ያለ ሩካቤ የወንድ ዘር ከሚፈስባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ነው ። ሌሎች ደግሞ በአድካሚ የጉዞ ወቅት ደጋፊ ፣ በሕመም ጊዜ ደግሞ አስታማሚ ... እየመሰሉ ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አካላት ለመደባበስ የሚሞክሩ ናቸው ። አንዳንዶች ደሞ እነርሱ ፈፅሞ ለመንካት እንዳላሰቡ ነገር ግን የተፈጠረው ሁኔታ እንዲጋፋ ወይም እንዲነካኩ እንዳደረጋቸው ለማስመሰል ይሞክራሉ ። በብዛት እንደዚ የሚያደርጉት ሕዝባዊ ስብሰባዎች በሚደረግባቸው እለታትና መጨናነቅ በሚኖርባቸው ስፍራዎች ነው ። ለምሳሌ እንደ ጥምቀት ፣ መስቀል ፣ ኤግዚብሽኖች ፣ የሞሉ ሚኒባሶች ሀይገሮች ባሶችና ባቡሮች መጥቀስ ይቻላል

ሌሎች ደግሞ ውጫዊ ይዘታቸው ሲታይ በዚህ ዓይነት ዘርን በማፍሰስ የመርካት ተግባር የማይጠረጠሩ አይነት ናቸው ። ለምሳሌ እድሜያቸው በጣም የገፋ ፣ በአስተሳሰብ የበሰሉ ፣ በአለባበስና በምጣኔ ሀብት የተከበሩ የሚመስሉ ወይም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ አቋምና መልካም ስም የያዙ ናቸው ። እንደዚ ያሉት ሰዎች የሌሎችን ህዋሳት ለመነካካት የሚያደርጉት ጥረት "ይህን አስበው አይደለም " እየተባለ ብዙ ጊዜ በበጎ ይተረጎምላቸዋል

ሌላው ዝንባሌያቸው ደግሞ ታዳጊ ህፃናትን ማባለግ ነው ። በቅጡ ጡት ያላጎጠጎጡ ሕፃናትም እንኳን የእነዚህ ሰዎች የጥቃት ሰለባዎች ናቸው ። ህፃናቱ እነዚህ ሰዎች ምን እያደረጉ እንደሆነ አያስተውሉም ፣ አያውቁም ፣ ቢያውቁም አይቃወሟቸውም አይከሷቸውም ። ወይም በትንሽ ነገር ሊባበሉና ሊታለሉ ይችላሉ ።ሕፃናቱን ያጫወቱና ያሳሳቁ በመምሰል ሲታገሉና ሲላፋ በፍትወት እየተቃጠሉ ልብሳቸውን በዘር ጭቃ የሚለውሱትን ወንዶች ቁጥር ቤት ይቁጠረው

... ይቀጥላል
https://t.me/meazasenay